የቴሌብር የአዲስ ዓመት ኤክስፖ ማበረታቻ ስጦታ ደንብ እና ሁኔታዎች

  • ደንበኞች አዲስ ዓመትን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ውስጥ ከቴሌብር ተመዝጋቢ ነጋዴዎችዕቃዎችን እና የመግቢያ ትኬቶችን በቴሌብር ሲገዙ የ5% ተመላሽ የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ ያገኛሉ።
    • ደንበኞች ተመላሽ በሚደረግላቸው 5% ኤሌክትሮኒክ ገንዘብ የአየር ሰዓት እና ጥቅል ለራሳቸው ወይም ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መግዛት ያስችላቸዋል።
    • በአንድ ጊዜ እስከ 5,000 ብር ግብይት የሚፈጽም ደንበኛ የ5% ተመላሽ የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ ማበረታቻ ብቁ ይሆናል።
    • ነባር ወይም አዲስ የቴሌብር ተመዝጋቢዎች ማበረታቻውን ማግኘት ይችላሉ።
  • ደንበኞች የመግቢያ ትኬቶችን ለራሳቸው ወይም ለሌላ ሰው በቴሌብር መተግበሪያ ወይም በቴሌብር አጭር ቁጥር (*127#) መግዛት ይችላሉ፡፡
  • ደንበኞች ለግብይት የቴሌብር መተግበሪያን ወይም የቴሌብር አጭር ቁጥርን (*127#) መጠቀም ይችላሉ።
  • ኤግዚቢሽኑ እስኪጠናቀቅ ድረስ አንድ ደንበኛ እስከ 500ብር የኤሌክትሮኒክ ተመላሽ ገንዘብ ማግኘት ይችላል፡፡
  • ነባር ወይም አዲስ የቴሌብር ተመዝጋቢ ነጋዴዎች ዕቃዎቻቸውን በኤግዚቢሽን ማዕከሉ ውስጥ መሸጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • የነጋዴ የመሸጫ ቁጥርን (code) በመጠቀም ከኤግዚቢሽን ማዕከል ውጭ ዕቃዎችን መሸጥ የተከለከለ ነው።
  • አንድ ነጋዴ ለሚያከናውነው ግብይት የ0.5%  የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ በስጦታ የሚያገኝ ሲሆን፣ ስጦታው የሚታሰበው በቀን እስከ 25,000 ብር ለሚደርስ ሽያጭ ይሆናል፡፡
  • ነጋዴዎች የ0.5% ተመላሽ የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ ስጦታ ሲያገኙ የማሳወቂያ አጭር የጽሑፍ መልዕክት የሚደርሳቸው ይሆናል።
  • ነጋዴዎች የሚያገኙት ስጦታ በኤግዚቢሽኑ ወቅት በሚሸጧቸው አጠቃላይ ትኬቶች እና ዕቃዎች ቁጥር ይወሰናል፡፡
  • ነጋዴዎች የሚያገኙትን ተመላሽ የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ የአየር ሰዓት እና ጥቅል ለራሳቸው ወይም ለሌሎች ለመግዛት ያስችላቸዋል።
  • ነጋዴዎች ተመላሽ ገንዘብ ለማግኘት በማሰብ የራሳቸውን ምርት መግዛት የለባቸውም፡፡
  • እያንዳንዱ ነጋዴ በኤግዚቢሽኑ ላይ ግብይት እንዲያከናውን በተሰጠው የግብይት መለያ ቁጥር (QR code) ብቻ ማከናወን አለበት።
  • ነጋዴዎች ማንኛውንም ግብይት በቴሌብር ቻናል (በቴሌብር መተግበሪያ ወይም በቴሌብር አጭር ቁጥር (*127#) ከደንበኞች ክፍያ መቀበል አለባቸው።

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives