5ጂ ሞባይል ጥቅል
New Year
New Speed, New Convenience, New Lifestyle
ደንብና ሁኔታዎች
- የድርጅት ደንበኞች የ5ጂ አገልግሎትን በቅድመ ክፍያ፣ ድህረ ክፍያ እንዲሁም የሀይብሪድ ሲም ካርድ በመጠቀም አገልግሎቱን በነጠላ ወይም በጅምላ ማግኘት ይቻላል፡፡
- የቅድመ ክፍያ ደንበኞች የአየር ሰዓተ በመጠቀም፣ በጥሬ ገንዘብ እንዲሁም ቴሌብርን ተጠቅመው መግዛት ይችላሉ፡፡
- መጠንን መሰረት ያደረጉት ጥቅሎች ዋጋ እና የጥቅል ሀብት ለአንድ ጊዜ ወይም በየወሩ በቋሚነት መግዛት ይቻላል፡፡
- ፍጥነትን መሰረት ያደረጉት ጥቅሎች በድህረ ክፍያ አማራጭ በየወሩ በቋሚነት በነጠላ እንዲሁም ለጅምላ ሽያጭ የቀረቡ ናቸው፡፡
- የ5ጂ ደንበኞች ከ5ጂ ኔትወርክ ሽፋን ውጭ በሚሆኑበት ጊዜ የ4ጂ ኔትወርክን በመጠቀም የገዙትን የዳታ ጥቅል መጠቀም ይችላሉ፡፡
- አገልግሎቱን ለማግኘት በአቅራቢያዎ የሚገኙ የኢትዮ ቴሌኮም ሽያጭ ማዕከላትን መጎብኘት ይኖርቦታል፡፡
- ለ5ጂ ከሽያጭ በኋላ ያሉ አገልግሎቶች ማለትም ከቅድመ ክፍያ ወደ ድህረክፍያ/ሀይብሪድ ለመቀየር፣ ከድህረ ክፍያ ወደ ቅድመ ክፍያ ለማዞር፣ ከ2ጂ/3ጂ/4ጂ ወደ 5ጂ ለማሳደግ፣ ሲም ካርድ በድጋሜ ለማውጣት፣ የባለቤት ለውጥ እና የመሳሰሉት አገልግሎቶች ከ4ጂ አገልግሎት ተመሳሳይ በሆነ ዋጋ የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡
- ደንበኞች ሲም ካርዳቸውነ ከ5ጂ ወደ 4ጂ ፍጥነት ዝቅ በሚያደርጉበት ጊዜ የገዟቸው ጥቅሎች በ4ጂ ኔትወርክ የሚጠቀሙ ይሆናል፡፡
- ያልተገደበ 4ጂ ጥቅል የገዙ ደንበኞች 5ጂ የሚያስጠቅም መገልገያ ቢኖራቸውም ሲም ካርዱ 5ጂ እስካልሆነ ድረስ የ5ጂ ኔትወርክ መጠቀም አይችሉም፡፡
- ደንበኞች የቢሮ አድራሻቸውን መቀየር ከፈለጉ በቅድሚያ የቦታ ለውጥ ለማድረጋቸው በማሳወቅ ከክፍያ ነፃ በመሆነ መንገድ ይስተናገዳሉ፡፡
- መጠንን መሰረት ያደረገ ጥቅል የገዙ ደንበኞች ጥቅላቸውን ከቀነ ገደቡ በፊት ቀድመው ከጨረሱ በ 0.4 ሣንቲም ክፍያ አገልግሎቱን ማግኘት መቀጠል ይችላሉ፡፡
- ደንበኞች ለአገልግሎት ሲመዘገቡ ለመጀመሪያው ወር እንዲሁም አገልግሎቱን ሲያቋርጡ ወርሃዊ ክፍያ እና የጥቅል መጠን አገልግሎቱን ለሚያገኙበት ቀናት ብቻ ተሰልቶ የሚጠቀሙ እና የሚከፍሉ ይሆናል፡፡
- መጠንን መሰረት ያደረገ የ5ጂ ጥቅል ወደ ሌላ ጥቅል መቀየር እንዲሁም ወደ ሌላ የ5ጂ የአገልግሎት ቁጥር ማስተላለፍ ይቻላል፡፡
- ሁሉም ዋጋዎች ተ.እ.ታን ያካትታሉ፡፡