የቴሌብር አገልግሎቶች

ልዩ የቴሌብር ጥቅል 

ብዙ ይጠቀሙ ትንሽ ይክፈሉ! ጥቅሉን በቴሌብር መተግበሪያ ብቻ ያገኛሉ 

ገንዘብ መላክ እና መቀበል

በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል ለሚኖሩ ቤተሰቦችዎ፣ ጓደኞችዎ ወይም ለሚወዷቸው ሰዎች  የቴሌብር አገልግሎት ተጠቃሚ ሆኑም አልሆኑም ገንዘብ በፍጥነት ለመላክ ያስችልዎታል።

የአየር ሰዓት ለመግዛት

የተመዘገቡ ደንበኞች የቴሌብር አካውንታቸውን በመጠቀም ለሞባይል ስልካቸው በቀላሉ የአየር ሰዓት መሙላት ይችላሉ።

በቴሌብር ይክፈሉ

በማንኛውም ቦታ እና ጊዜ ቴሌብርን በመጠቀም የኢትዮ ቴሌኮም ሂሳብዎን (bill) ለመክፈል ወይም ትኬቶችን ለመግዛት (ለምሳሌ፡- አንድነት ፓርክ) በጣም አመቺ ነው።

የቴሌብር ሱፐርአፕ መተግበሪያን ለማውረድ ኪው አር ኮዱን በስልክዎ ያንሱ!

       ዓለም አቀፍ የገንዘብ መቀበል ወይም መላክ አገልግሎት

ደንበኞች ውጭ ሀገር ከሚኖሩ ቤተሰቦቻቸዉ፣ ጓደኞቻቸው፣ ዘመዶቻቸዉ ወይም ወዳጆቻቸው  የሚላክላቸውን ገንዘብ በሞባይል ስልካቸው በቀላሉ መቀበል ይችላሉ።

ብዙ ክፍያዎችን በአንዴ በቴሌብር ይክፈሉ

በማንኛውም ጊዜ የሰራተኞችዎን ደሞዝ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ክፍያዎችን በአንዴ በቀላሉ በመክፈል ጊዜዎንና አላስፈላጊ ወጪዎን ይቆጥቡ።

በቴሌብር አማካኝነት ይለግሱ

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በቀላሉ በቴሌብር አማካኝነት ገንዘብ ይለግሱ፣ የብሄራዊ ኩራታችን አካል ይሁኑ!

ጥሬ ገንዘብ ማውጣት

ቴሌብር ደንበኞች ከአካውንታቸው በየትኛውም ቦታ የቴሌብር ህጋዊ ውክልና ካላቸው ወኪል አገልግሎት ሰጪዎች ወይም ከኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከላት ገንዘብ ለማውጣት  ያስችላቸዋል።

ተቀማጭ ገንዘብ

ቴሌብር ገንዘብዎን ተመጣጣኝ ወደ ሆነ የኤሌክትሮኒክ ገንዘብለመለወጥየሚያስችልዎ አማራጭ ሲሆንይህም የቴሌብር አካውንትዎን ወይም የኪስቦርሳዎን የገንዘብ መጠን ይጨምርልዎታል።

ለዕቃዎች እና አገልግሎቶች ይክፈሉ

ለገዟቸው ዕቃዎች እና ለሚያገኟቸው አገልግሎቶች በማንኛውም ጊዜ እና ቦታ ስካን (Scan) በማድረግ በቴሌብር አካውንትዎ ሂሳብዎን በቀላሉ ይክፈሉ።

ቴሌብርን በመጠቀም የሞባይል ጥቅሎችን ሲገዙ እንደጥቅሉ አይነት

ቴሌብርን ለምን ምርጫዎ ያደርጉታል?

  • ተደራሽነቱ

    የትም መሄድ ሳይጠበቅብዎት በአቅራቢያዎ ባሉ ተወካዮቻችን አገልግሎቱን በማንኛውም ሰዓት ማግኘት ያስችልዎታል፡፡

  • ፈጣን መሆኑ

    ገንዘብ ለማስቀመጥ፣ ለማስተላለፍ እንዲሁም በፈለጉ ጊዜ ክፍያ ለመፈፀም ይረዳል፡፡ ማረጋገጫም ወዲያውኑም ይደርስዎታል፡፡

  • አስተማማኝነቱ

    ቴሌብር አስተማማኝ በሆነ ሲስተም የሚጠበቅ እና የሚተማመኑበት (በእጅዎት የሚይዙት ገንዘብ ስለማያስፈልጎት ከስርቆት ስጋት ነፃ ያደርግዎታል)

  • ምቹ መሆኑ

    የባንክ የሂሳብ ደብተር እንዲሁም ገንዘብ በእጅዎት መያዝ ሳያስፈልግ፣ በሞባይል ስልክዎት ብቻ ተጠቅመው ግብይት ለመፈጸም ያስችልዎታል፡፡

  • ሁለገብነቱ

    የሞባይል ስልክዎት በመጠቀም ገንዘብ ለማስቀመጥ፣ ለመቀበል፣ ለመላክ፣ ለማውጣት እና ለማስተላለፍ ይረዳል፡፡

  • ቀላልነቱ

    ገንዘብ በእጅዎ መያዝ ሳይኖርብዎት እጅዎት ላይ ባለ ስልክ በቀላሉ ማንኛውንም አገልግሎት ያገኛሉ፡፡

የቴሌብር ቁጥራዊ መረጃዎች

+ 0 ትሪሊዮን
የገንዘብ ዝውውር ዋጋ (በብር)
+ 0 ሚሊዮን
ጠቅላላ የደንበኛ ብዛት (እስከ መጋቢት 2016)
+ 0 ሺህ
ወኪሎች
+ 0 ሺህ
ነጋዴዎች
0 ባንኮች
ከባንኮች ወደ ቴሌብር አካውንት ማስተላለፍ
0 ባንኮች
ከቴሌብር ወደ ባንኮች አካውንት ማስተላለፍ

የቴሌብር ቢዝነስ አጋሮቻችን

ስለ ቴሌብር አገልግሎት ተደጋግመው የሚጠየቁ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

  • የኢትዮ ቴሌኮም የቴሌብር አገልግሎት የሞባይል ቁጥርዎን ተጠቅመው ገንዘብ ለማስቀመጥ፣ ለመቀበል፣ ለማስተላለፍ፣ ለማውጣት፣ ለመላክ፣ የጥቅል አገልግሎት ለመግዛት፣ ወርሃዊ የአገልግሎት ክፍያዎችን /ቢል/ ለመክፈል፣ የአየር ሰዓት ለመግዛት፣ ትኬት ለመግዛት፣ የአየር ሰዓት ወይም የጥቅል አገልግሎት ለመላክ እና የምርትና አገልግሎት ክፍያዎችን ለመፈጸም የሚያስችልዎት እጅግ ዘመናዊ የሆነ የሞባይል የክፍያ ሥርዓት ነው፡፡በቴሌብር በቀላሉ ከጥሬ ገንዘብ ነፃ የሆኑ ግብይቶችንና ዓለም አቀፍ የገንዘብ ልውውጦችንም ለማካሄድ ይችላሉ።በተጨማሪም የቴሌብር የሞባይል መተግበሪያን በመጠቀምና የQR ኮዱን በማንሳት (scan) በማድረግ በሱቆችና መደብሮች ክፍያ ለመፈጸም ወይም ሸቀጦችንና አገልግሎቶችን ባሉበት ቦታ ሆነው በኦንላይን (Online) ለመግዛት ወይም በአቅራቢያዎ በሚገኙ የቴሌብር ወኪሎች በአካል በመሄድ ገንዘብ ለመቀበል ያስችልዎታል።
  • ባሉበት ቦታ ሆነው የሞባይለ ስልክዎን በመጠቀም በቀላሉ በቴሌብር ግብይት ለማከናወን ምቹ አማራጭ ነው፡፡ ጥሬ ገንዘብ ይዞ መጓዝ ወይም በአካል መሄድ ሳይጠበቅብዎ፣ እጅዎ ላይ ባለው የሞባይል ስልክዎ ግብይት ይፈጽሙ።

የአየር ሰዓት መሙያ አገልግሎት የቴሌኮም አገልግሎቶችን ብቻ ለመግዛት የሚያገለግል ሲሆን የቴሌብር አገልግሎት ግን የቴሌኮም አገልግሎቶችን ከመግዛት በተጨማሪ ገንዘብ በኤሌክትሮኒክስ ለመላክና ለመቀበል እንዲሁም ሌሎች በርካታ ግብይቶችን ለማከናወን ያስችላል።

የቴሌብር አገልግሎት ደንበኞች የባንክ አካውንት ሳይስፈልጋቸው የሞባይል ስልካቸውን ብቻ በመጠቀም የተለያዩ የፋይናንስ አገልግሎቶችን በቀላሉና ያለምንም ስጋት በእጅ መዳፍ ላይ ልዩ ልዩ ስራዎችን ለመከወን የሚያስችል አገልግሎት ነው፡፡ የቴሌብር ደንበኞቻችን የሚከተሉትን አገልግሎቶች በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፡፡

  • ጥሬ ገንዘብ ለማስቀመጥና ለማውጣት
  • ገንዘብ ለመላክና ለመቀበል፣
  • የአየር ጊዜ እና የሞባይል ጥቅሎችን ለመግዛት፣
  • ትኬቶችን ለመግዛት (ለምሳሌ፡- አንድነት ፓርክ)፣
  • በተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያዎች ላይ ለመሳተፍ (እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላሉ የድጋፍ ገንዘብ ለማሰባሰብ)
  • በተለያዩ አካባቢዎች ከሚገኙ ሱቆችና መደብሮች ለሚገዙ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ግዢ ክፍያ ለመፈጸም
  • ከደንበኞች ክፍያዎችን ለመቀበል ወዘተ የመሳሰሉት ይገኙበታል።

  • ማንኛውም የኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ስልክ ደንበኛ የሆነ፣
  • የቴሌብር አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን የውል ስምምነት ለመፈጸም የሚችል እድሜው 18 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ፣
  • የሞባይል ቁጥር፣ የቅርብ ጊዜ ፎቶና ሕጋዊ የመታወቂያ ካርድ ያለው ሰው፣

የቴሌብር አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን በሚከተሉት ሁለት መንገዶች መመዝገብ ይችለሉ።

  1. ሙሉ ምዝገባ፡-
  • በአቅራቢያዎ የሚገኘውን ህጋዊ የቴሌብር ወኪል ወይም የኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከላት በመሄድ፣
  • አሁን በሚገለገሉበት የኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ስልክ ቁጥር እና በመታወቂያ ካርድዎ
  1. በራስ ለመመዝገብ፡-
  • *127# ላይ በመደወል እና የሚሰጡ ትዕዛዞችን በመከተል፣
  • የቴሌብር የሞባይል መተግበሪያን ከጎግል-ፕሌይ ወይም አፕ-ስቶር (Google play & app store) በማውረድ መመዝገብ፣
  • የደንበኛዎን ይወቁ(Know Your Customer - KYC) መረጃ በማስገባት ወይም የኢትዮ ቴሌኮም ፈጣን ምዝገባ (Quick registration) ከሲስተም የመረጃ ቋት ወይም ፍይል በሞባይል አገልግሎት ቁጥርዎ አማካኝነት ወደ ሞባይል መተግበሪያው የሚገባውን መረጃ ትክክለኛነት በማረጋገጥ መመዝገብ ይችላሉ።
  • የደንበኛዎን ይወቁ /KYC/ ሙሉ ምዝገባ ለማጠናቀቅ በአቅራቢያዎ የሚገኘውን የቴሌብር ወኪል ወይም የኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከል መጎብኘት ይችላሉ።
  • በቴሌብር መተግበሪያ የሚመዘገቡ ደንበኞች መታወቂያ ካርዳቸውን እና የቅርብ ጊዜ ፎቶቸውን በሲስተሙ ላይ በመጫን ሙሉ ለሙሉ ለመመዝገብ ይችላሉ።
  • የተለያዩ የግብይት እና የሂሳብ ዝውውር ገደቦች በኢትዮጰያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሠረት ተግባራዊ ይሆናሉ።

  • ለቴሌብር አገልግሎት ምዝገባ ምንም ዓይነት ክፍያ አይከፈልም።

  • አዎ፣ በተለያዩ የአገልግሎት ስልክ ቁጥሮች ከአንድ በላይ አካውንቶች ሊኖሩዎት ይችላሉ።
  • ቀሪ ሂሳብ እና የግብይት ገደቦች በኢትዮጰያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሠረት ተግባራዊ ይደረጋሉ።

ወደ ቴሌብር አካውንትዎ በሚከተሉት መንገዶች አማካኝነት ገንዘብ ተቀማጭ ማድረግ ወይም ማስገባት ይችላሉ፡፡

    • ወደ ሕጋዊ የቴሌብር ወኪል ወይም የኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከላት በአካል በመሄድ፣
    • ከቴሌብር ሲስተም ጋር ከተገናኘው የባንክ ሂሳብዎ በማስተላለፍ፣
    • ከቴሌብር አገልግሎት ጋር የተገናኙ የአጋር ባንኮች ስም ዝርዝር በድረ-ገፃችን (www.ethiotelecom.et/telebirr ) ላይ ይገለጻሉ።

  • በቴሌብር ለሚከናወን እያንዳንዱ ግብይት ማሳወቂያ በ127 የአጭር የጽሑፍ መልዕክት ወዲያውኑ ይላክልዎታል።
  • ለአየር ሰዓት ለሞሉበት እና ለአገልግሎት (bill) ክፍያዎች ተጨማሪ የክፍያ በደንበኞች አገልግሎት (994) የማረጋገጫ መልዕክት ይደርስዎታል።

  • የቴሌብር ወኪሎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠውን መስፈርት በማሟላት ለክቡራን ደንበኞቻችን የቴሌብር አገልግሎት እንዲሰጡ በኢትዮ ቴሌኮም የተፈቀደላቸው አጋር ድርጅቶች ናቸው።
  • ወኪሎች ደንበኞችን ያስተምራሉ፣ ይመዘግባሉ፣ ገንዘብ የማስቀመጥና የመክፈል እንቅስቃሴዎችን ይሠራሉ፡፡ በተጨማሪም የአየር ሰዓት ይሸጣሉ፣ ላልተመዘገቡ ደንበኞች ገንዘብ ያስተላልፋሉ፣ የአገልግሎት ክፍያዎችን (pay bills) ይከፍላሉ እነዲሁምደንበኞችን ወክለው የተለያዩ ተግባራትን ያከናውናሉ።
  • ወኪሎች ለደንበኞች ለሚሰጧቸው ሁሉም አገልግሎቶች/ግብይቶች የአገልግሎት ክፍያ (ኮሚሽን) ይሰጣቸዋል።

በቴሌቢር አፕ ተጠቅመህ የአየር ሰአት፣ ፓኬጅ እና/ወይም ለጓደኛህ/ጓደኛህ ለመላክ ሽልማት/ማበረታቻ መጠቀም ትችላለህ ወይም *127# በመደወል።

የቴሌቢር አፕን በመጠቀም - የአየር ሰአት ሲሞሉ ወይም ፓኬጅ ሲገዙ በፒን መግቢያ ገጹ ላይ አንድ አማራጭ የሚመረጥ ይመስላል። ጉርሻውን ለመጠቀም እና ለመቀጠል “የሽልማት ሒሳብ” ላይ ምልክት ያድርጉ።

*127# USSD ሜኑ በመጠቀም *127# ይደውሉ እና ለቀጣዩ ገጽ # ምረጥ እና "Redeem incentive" የሚለውን ምረጥ እና አሰራሩን ተከተል።

ኢትዮቴል የክሬዲት አገልግሎት ለቴሌብር ደንበኛ የአየር ሰዓት ወይም ጥቅል ለመግዛት የሚሰጥ የብድር አገልግሎት ነው።

  • አገልግሎቱ ለሁሉም የቴሌብር ደንበኞች ይገኛል። የዱቤ እሴቱ የአየር ሰዓት/ጥቅል ለመግዛት እና/ወይም ለሌሎች እንደ ስጦታ ለመላክ ይጠቅማል።
  • የተበደረው መጠን ማውጣት አይቻልም።
  • የኢትዮቴል ክሬዲት መጠን በአማካይ ወርሃዊ የግብይት ዋጋ እና እስከ 250 ETB ባለው ክልል ላይ በመመስረት ይወሰናል። ስለ ኢትዮቴል የብድር አገልግሎት ብቁነት መስፈርት ለበለጠ መረጃ እባክዎን https://www.ethiotelecom.et/telebirr/buy-airtime ይጎብኙ
  • ለክሬዲት ምንም ቋሚ ስያሜ የለም. ማንኛውንም መጠን በብቁ ክልል ውስጥ ብዙ ጊዜ መበደር ይችላሉ።
  • የተበደረው የአየር ጊዜ ክሬዲት ጥሬ ገንዘብ ሲያስገቡ ወይም በቴሌብር ክፍያ ሲቀበሉ በራስ ሰር ይቀነሳል።
  • ኢትዮ ቴሌኮም ከእያንዳንዱ የተበደረ የአየር ሰአት/ፓኬጅ 10% ያስከፍላል።

  1. ቴሌቢር USSDን በመጠቀም
      • ደረጃ 1፡ *127# ይደውሉ
      • ደረጃ 2፡ ከምናሌው ውስጥ # (ቀጣይ) ምረጥ
      • ደረጃ 3፡ የኢትዮቴል የብድር አገልግሎትን ይምረጡ
      • ደረጃ 4፡ የአየር ጊዜ ክሬዲት ገደብ መጠይቅን ይምረጡ
      • ደረጃ 5፡ ፒንዎን ያስገቡ
      • በመጨረሻም፣ የእርስዎ ጠቅላላ ክሬዲት፣ የሚገኝ እና ጥቅም ላይ የዋለው የብድር ገደብ ይታያል
  2. የቴሌቢር መተግበሪያን በመጠቀም - አጠቃላይ የሚፈቀደው፣ የሚቀረው እና የተበደረው መጠን የአየር ሰዓት/የጥቅል ክሬዲት አገልግሎት ስንጠይቅ ይታያል።

  • በአቅራቢያዎ የሚገኝ የቴሌብር ሕጋዊ ወኪል አድራሻን በቀላሉ ለማወቅ ድረ-ገጻችን (et) ይጎብኙ፡፡
  • የቴሌብር የሞባይል መተግበሪያ ላይ በመግባት በአቅራቢያዎ የሚገኝ የቴሌብር ወኪልን አድራሻ ማወቅ ይችላሉ
  • በአካባቢዎ ያሉ የቴሌብር ብራንድ ያላቸው ወኪሎችን ይጎብኙ፣
  • በመንገድ ላይ የሚያገኙትን ማንኛውም ሰው የቴሌብር ወኪሎች የሚገኙበትን ቦታ ይጠይቁ፣
  • የኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከላትን ለማግኘት በአካባቢዎ የሚገኙ ማንኛውንም ነዋሪ ይጠይቁ።

ሁኔታ 1፡- ለቴሌብር አገልግሎት ያልተመዘገቡ ደንበኛ ከሆኑ

  • አዎ፣ የቴሌብር አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን ላልተመዘገቡ ደንበኞች በአቅራቢያዎ በሚገኝ የቴሌብር ወኪል አማካኝነት ወይም የኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከል በመሄድ ገንዘብ መላክ ይቻላሉ።
  • የተቀባዩን ሞባይል ስልክ ቁጥር እና የርስዎን መታወቂያ ለወኪሉ በመስጠት/በማሳየት መላክ ይችላሉ፡፡
  • ተቀባዩ ከቴሌብር ወኪል የተላከለትን ገንዘብ ከቴሌብር ወኪል ወይም ከኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከል ለማውጣት የሚያስችል የቫውቸር ኮዱ (ቁጥር) እና የገንዘቡን መጠን የሚገልጽ የማሳወቂያ መልዕክት ከቴሌብር ወኪል ይላክለታል፡፡
  • የቴሌብር ወኪሉን/ሱቁን ለቀው ከመሄድዎ በፊት የገንዘብ ዝውውሩ መጠናቀቁን ወይም ገንዘቡ መላኩን ማረጋገጥ ይኖርብዎታል፡፡
  • የገንዘብ መላኪያ የአገልግሎት ክፍያ (Over the counter) በቴሌብር ሲስተም አማካኝነት ተቀናሽ ወይም ተፈጻሚ ይደረጋል።

ሁኔታ II፡-  የቴሌብር ተመዝጋቢ ደንበኛው ከሆኑ

  • ለቴሌብር አገልግሎት ለተመዘገበ ደንበኛ *127# ላይ በመደወል ወይም የቴሌብር ሞባይል መተግበሪያን በመጠቀም ገንዘብ መላክ ይችላሉ።
  • የተቀባዩን የሞባይል ስልክ ቁጥር እና የሚላከውን የገንዘብ መጠን ማስገባት ይኖርብዎታል፡፡
  • ተቀባዩ ገንዘቡን ከቴሌብር ወኪል/ከኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከል ለመቀበል የሚያስችል የገንዘብ መጠን እና የቫውቸር (code) ቁጥር የሚገልጽ ማሳወቂያ መልዕክት ከቴሌብር እንዲደርሰው ይደረጋል።
  • ገንዘቡ ስለመላኩ ማረጋገጫ አጭር መልእክት ከቴሌብር ወዲያውኑ ይደርስዎታል፡፡
  • የገንዘብ መላኪያ የአገልግሎት ክፍያ በቴሌብር ሲስተም አማካኝነት ተቀናሽ ወይም ተፈጻሚ ይደረጋል።

  • በአቅራቢያው ወደ ሚገኝ የቴሌብር ወኪል በመሄድ፣ የሞባይል ቁጥሩንና ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ በማቅረብ፣
  • በአቅራቢያው ወደ ሚገኝ የኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከል በመሄድ እና የሚፈለገውን የደንበኛዎን ይወቁ /know your customer – KYC/ መስፈርት በማሟላት ነው።
  • በአጭር ቁጥር (USSD) ወይም በቴሌብር ሞባይል መተግበሪያ አማካኝነት በራስዎ መመዝገብ ይችላሉ።

  • ለጊዜው ገንዘብ መላክ የሚቻለው በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኝ ማንኛውም ቤተሰብ እና ወዳጅ ዘመዶች ብቻ ነው።
  • ነገር ግን ከየትኛውም ዓለም ክፍል በአጋሮቻችን በኩል ከቤተሰቦችዎ ወይም ጓደኞችዎ የሚላክልዎትን ገንዘብ መቀበል ይችላሉ። ዓለም አቀፍ ገንዘብ የሚያስለላልፉ አጋሮቻችን ዝርዝር በድረ-ገፃችን (www.ethiotelecom.et/telebirr) የሚገለጽ ይሆናል።

  • ወኪሎቻችን፣ አጋሮቻችን እና ደንበኞቻችን የሚስጥር ቁጥራቸውንና የይለፍ ቃላቶቻቸውን ምስጥራዊነት መጠበቅና ማረጋገጥ አለባቸው።
  • በተጨማሪም በቴሌብር ውስጥ ያለው ገንዘብ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ምክንያቱም፡-
  • ደህንነቱ ለማንም በማይጋራ የሚስጥር ቁጥር የተጠበቀ በመሆኑ፣
  • ዘመናዊ የሞባይል ገንዘብ መፍትሄ እንዲተገበር በመደረጉ፣
  • አጠራጣሪ እና የማጭበርበር ድርጊቶችን መለየት እንዲሁም አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ የሚያችል የአሰራር ሥርዓት የተዘረጋ በመሆኑ፣
  • የማጭበርበር እና አጠራጣሪ የገንዘብ ዝውውርን በተመለከተ የሪፖርት እና ክትትል ፖሊሲዎች እና መመሪያዎች በመኖራቸው፣
  • ጠንካራ የገንዘብ ዝውውር እና የፀረ-ሽብርተኝነት የፋይናንስ ፖሊሲዎች በመተግበራቸው፣
  • አጋሮቻችን እና ሠራተኞቻችን በእነዚህ ፖሊሲዎች እና መመሪያዎች ላይ ስልጠና እንዲወስዱ በመደረጉና ወደፊትም እንዲሰለጥኑ የሚደረግ በመሆኑ፣
  • ለማጭበርበር ድርጊቶች ምንም አይነት ምዕረት የሚባል ነገር አለመኖሩ፣
  • ጠንከራ የፋይናንስ ቁጥጥር ሥርዓት እንዲዘረጋ በመደረጉ ነው፡፡

  • የቴሌብር አገልግሎት በአምስት ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ፣ በኦሮምኛ፣ በሶማሊኛ፣ ትግርኛ እና እንግሊዝኛ እየተሰጠ ይገኛል።
  • ከእነዚህ ቋንቋዎች መካከል በመረጡት ቋንቋ መጠቀም ይችላሉ።
  • ቋንቋ ለመቀየር *127# ላይ በመደወል የሚመጡ ትዕዛዞችን ይከተሉ።
  • የቋንቋ ለውጥ ስለማድረግዎ አጭር ጽሑፍ መልዕክት ማሳወቂያ ይደርስዎታል።
  • ቋንቋ ለመቀየር፡-
  • *127# ላይ ይደውሉና ቀጣይ ትዕዛዞችን ይከተሉ፣
  • የቴሌብር ሞባይል መተግበሪያን በመጠቀም የሚመጡ ቀጣይ ትዕዛዞችን ይከተሉ፣
  • ወደ 127 ይደውሉና ቀጣይ ትዕዛዞችን ይከተሉ ወይም
  • ²CH² የሚል አጭር መልዕክት ወደ 127 በመላክ፣ ቀጣይ ትዕዛዞችን ይከተሉ፡፡
  • ቋንቋ ስለመቀየርዎ የማሳወቂያ አጭር ጽሑፍ መልዕክት ይደርስዎታል።

  • በጭራሽ፣ ሲም ካርድዎ ወይም የሞባይል ስልክ ቁጥርዎ ቢጠፋብዎ የሞባይል ገንዘብ አካውንትዎን አያጡም፣
  • ማንም ሰው የእርስዎን ቴሌብር አካውንት መክፈትና መጠቀም አይችልም፡፡ ምክንያቱም የእርስዎ የቴሌብር አካውንት ማንም ሊያውቀው በማይችለው በባለስድስት አሃዝ የሚስጥር ቁጥር የተጠበቀ ነው።
  • የጠፋብዎትን የሞባይል ሲም ካርድዎን እንዳወጡ የቴሌብር አካውንትዎን ድጋሜ መጠቀም ይችላሉ።
  • ለቴሌብር ልዩ መለያው የሞባይል አገልግሎት ቁጥርዎ በመሆኑ ስልክ ቁጥርዎንና የሚስጥር ቁጥርዎን በመጠቀም አገልግሎቱን እንደገና መጠቀም ይችላሉ።

  1. የሚስጥር መለያ ቁጥርዎን/የይለፍ ቃልዎን እንደገና ለማስጀመር ወደ ቴሌብር የጥሪ ማዕከል ወይም 127 በመደወል፣
  2. የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞቻችን የሚስጥር መለያ ቁጥርዎን/የይለፍ ቃልዎን በድጋሜ ለማስጀመር ትክክለኛው ሰው መሆንዎን ለማወቅ በቴሌብር ሲስተማችን ውስጥ ያለው መረጃ እርስዎ ከሚሰጡት ምላሽ ጋር በጥንቃቄ በማመሳከር እና በማረጋገጥ ስራ ይሰራሉ።
  3. ከዚያ በኃላ የሚጥር ቁጥርዎን ለመሙላት የሚያስችል ጊዜያዊ አጭር የይለፍ ቃል በ127 እንዲደርስዎት ይደረጋል፡፡

    • አዎ፣ ከጥሪ ማዕከል ባለሙያዎቻችን ጋር በመነጋገር እና ገንዘብ የላኩበትን መለያ ቁጥር በማሳወቅ በ48 ሰዓታት ውስጥ ተመላሽ ይደረግልዎታል፡፡

    ለምሳሌ፡- በመለያ ቁጥር 8E320N1XB4 የተደረገን የቴሌብር የገንዘብ ዝውውር አጭር መልእክት ይመልከቱ፡፡

    • የግብይት መለያ ቁጥርዎን በ30 ሴኮንድ ውስጥ ወደ 126 ቴሌብር አጭር የአገልግሎት ቁጥር በመላክ በስህተት የላኩትን ገንዘብ በራስዎ ማስመለስ ይችላሉ፡፡
    • ገንዘቡ የሚመለሰው በሶስተኛ ወገን አካውንት ውስጥ ካለ ብቻ ነው፡፡
    • በተጨማሪም ገንዘቡ በሚከተሉት ሁኔታዎች ተመላሽ ሊደረግ ይችላል፡-
    • ወደ ተሳሳተ ቁጥር ከተላከ
    • የተሳሳተ የገንዘብ መጠን ወደ ትክክለኛ ቁጥር ከተላከ
    • ለአገልግሎት ክፍያ የተሳሳተ የገንዘብ መጠን ሲፈጽሙ
    • የተሳሳተ የገንዘብ መጠን ለአየር ሰዓት ሲከፍሉ
    • ለነጋዴ እቃዎች/አገልግሎቶች ግዢ የተሳሳተ ክፍያ ሲፈጸም፡-
    • ነጋዴውን በማነጋገር
    • ለተመላሽነቱ ቴሌብር በደንበኛውና በነጋዴው መካከል ስለተፈጠረው ስህተት የማግባባት ስራ ይሰራል፡፡
    • ተመላሽ ማድረግ የሚችለው ነጋዴው ብቻ ነው፡፡

  • እንደ የአገልግሎት ዓይነቱ ነፃ እና የክፍያ አገልግሎቶች አሉ።
  • የታሪፍ ዝርዝሮችን ለማወቅ ድረ-ገጻችን (et) ይጎብኙ

  • የሚስጥር መለያ ጥያቄዎችንለመቀየር :
    1. አጭር ቁጥር በመጠቀም:
      •  *127# ይደውሉ
      • ከዝርዝሩ ውስጥ ማይ አካውንት የሚለውን ምረጡ
      • አካውንት አስተዳደር የሚለውን ይምረጡ
      • ጥያቅና መልስ የሚለውን ይምረጡ
      • የመረጡትን የጥያቄ ቁጥር ይምረጡ
      • መልስህን አስገባ
      • ቁጥር 1 በማስገባት መልስዎን ያረጋግጡ (እሺ)
      • የእርስዎን ፒን ቁጥር ያስገቡ፣ ከዚያ ከ127 ኤስኤምኤስ ይደርስዎታል።
    2. ቴሌብር የሞባይል መተግበሪያን በመጠቀም፡-
      • መጀመሪያ ይግቡ፣ ከዚያ የእኔ አካዉንት ይምረጡ >የደህንነት ጥያቄን ይምረጡ>የእርስዎን ፒን ቁጥር ያስገቡ> የመረጡትን ጥያቄ ምረጥ እና መልሱን አስገቡ ከዛ አረጋግጥ የሚለውን ይምረጡ > መጨረስ የሚለውን ይምረጡ እና ከ127 አጭር መልዕክት ይደርስዎታል።

  • የማንኛውንም ደንበኛ ምስጢር ቁጥር ከደንበኛው እውቅና ውጪ መቀየር ህጋዊነት አይኖረውም