በቴሌብር ይክፈሉ
በማንኛውም ቦታ እና ጊዜ ቴሌብርን በመጠቀም የኢትዮ ቴሌኮም ሂሳብዎን (bill) ለመክፈል ወይም ትኬቶችን ለመግዛት (ለምሳሌ፡- አንድነት ፓርክ) በጣም አመቺ ነው።
የቴሌብር አካውንትዎን በመጠቀም የተለያዩ የድርጅት የአገልግሎት ክፍያዎችን በቀላሉ በማንኛውም ጊዜና በየትኛውም ቦታ ሆነው ለመክፈል ቀላል አማራጭ ነው፡፡ በተለይም የውኃ፣ የመብራ፣ የጋዝ፣ የኢንሹራንስ እና የትምህርት ክፍያዎችን በቀላሉ ለመክፈል ያስችሎታል።
- ለሂሳብ አስተዳደር
ትምህርት ቤቶች የሂሳብ ዝርዝር መረጃ በቀላሉ በማዘጋጀት ለሪፖርት እና ለውሳኔ መጠቀም እንዲችሉ ይረዳል፡፡ በተጨማሪም ወላጆች/አሳዳጊዎች እጅግ ቀላል እና አስተማማኝ በሆነ መልኩ ክፍያ ለመፈፀም ያስችላቸዋል፡፡
- የተማሪዎችን መረጃ ለማስተዳደር
የተማሪዎችን መረጃ ማለትም ምዝገባ፣ አቴንዳንስ፣ ውጤት እና የስነ-ምግባር መከታተያ የሚኖረው ሲሆን የተማሪዎችን ወቅታዊ መረጃ እንዲያገኙ ያግዛል፡፡
- የመማሪያ ክፍል አስተዳደር
የክፍለ ጊዜያት መርሃ ግብር፣ የቤት ስራ፣ ፈተና እና ስለሚወስዱት የትምህርት ዓይነቶች መረጃ ስለሚያካትት ከተማሪዎች እና ወላጆቻቸው/አሳዳጊዎቻቸው ጋር የተቀናጀ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር ያግዛል፡፡
- የተግባቦት አገልግሎት
ወላጆች/አሳዳጊዎች ስለልጆቻቸው ለማወቅ ከመምህራኖች ጋር መረጃ እንዲለዋወጡ የሚያስችል ሲሆን የተማሪዎችን የውጤት ሪፖርት እንዲሁም ወሳኝ መርሃ ግብሮች ሲኖሩ በአጭር የፅሁፍ መልዕክት ለወላጆች/አሳዳጊዎች እንዲደርሳቸው ያደርጋል፡፡
በቴሌብር ክፍያዎን እንዴት መፈጸም ይችላሉ?
- ከአማራጩ ውስጥ ሂሳብ ለመክፈል” የሚለውንይምረጡ;
- “ለራስ” የሚለውን ይምረጡ ወይም “ለሌላ” (ለሌላ ሰው) የሚለዉን ይምረጡ
- የተቀባዩንስልክቁጥርያስገቡ/ ይምረጡ
- የሚከፍሉትን የገንዘብ መጠን ይምረጡ/ያስገቡ
- የሚስጥር ቁጥር (PIN) ያስገቡ
- ክፍያ መፈጸምዎን ያረጋግጡ
“ትኬት ይግዙ” የሚለውን አማራጭ ይምረጡ
o የትኬት አይነት ይምረጡ
o የቲኬቶችን ቁጥር ያስገቡ
o የመግቢያ ቀን እና ሰዓት ያስገቡ
o ለማረጋገጥ የሚስጥር ቁጥር (PIN) ያስገቡ
.
- *127# ይደውሉ
- # በማስገባት ወደ ቀጣይ ይሂዱ
- 7 ቁጥርን (ብሔራዊ ሎተሪ) ይምረጡ
- 1ቁጥርን (አድማስ ሎተሪ ብር 3) ይምረጡ
- ለማረጋገጥ 1 ቁጥርን ያስገቡ
- የሚስጥር ቁጥርዎን በማስገባት ክፍያዎን ይፈጽሙ (የማረጋገጫ አጭር የፅሁፍ መልዕክት ይደርስዎታል)
ማስታወሻ፡-
- ክፍያውን እንዳጠናቀቁ ማረጋገጫ መልዕክት ከ127 እንዲሁም የሎተሪ ቲኬት ቁጥርዎ ከ605 የደርስዎታል ፡፡
- እድልዎን ለማስፋት ከአንድ በላይ ሎተሪ መግዛት ይችላሉ፡፡
- በአጭር መልዕክት የደረስዎትን የሎተሪ ቁጥርዎን በጥንቃቄ ያኑሩ
የነዳጅ ክፍያዎን በቴሌብር መተግበሪያ ይክፈሉ
- ለግብይት ለመክፈል የሚለውን ይጫኑ
- የሻጭ ቁጥር የሚለውን በመምረጥ የሻጭ ቁጥር፣ ኦፕሬተር መለያ ቁጥር፣ የገንዘብ መጠን በማስገባት ይቀጥሉ የሚለውን ይጫኑ
- የሚስጥር ቁጥር ያስገቡ
- ለግብይት ለመክፈል ሚለውን በመጫን ክፍያዎን ይፈጽሙ
የነዳጅ ክፍያዎትን በቴሌብር አጭር ቁጥር *127# ይክፈሉ
- *127# ይደውሉ
- # በማስገባት ወደ ቀጣይ ዝርዝር ማውጫ ይሂዱ
- 9 ቁጥርን ግብይት ለመክፈል የሚለውን ይምረጡ
- 1ቁጥርን ግብይት ለመክፈል የሚለውን ይምረጡ
- የሻጭ መለያ ቁጥር ያስገቡ
- የብር መጠን ያስገቡ
- ለማረጋገጥ 1ቁጥርን ይጫኑ
- የሚስጥር ቁጥርዎን አስገብተው ክፍያዎትን ይፈጽሙ
ማስታወሻ:- የሻጭ መለያ ቁጥር ማለት የአገልግሎት ሰጪው ማደያ የመክፈያ መለያ ቁጥር ነው
አመታዊ የግብር ክፍያዎን ባሉበት ቦታ ሆነው በቀላሉ በቴሌብር መተግበሪያ ይክፈሉ
- በቴሌብር ለመክፈል የሚለውን ይምረጡ
- የአገልግሎት ክፍያ የሚለውን ይምረጡ
- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የሚለውን ይምረጡ
- የክፍያ ማዘዣ ቁጥር በማስገባት ይቀጥል የሚለውን ይጫኑ
- የክፍያ ዝርዝር መረጃዎችን በማረጋገጥ ይቀጥል የሚለውን ይጫኑ
- የሚስጥር ቁጥርዎን በማስገባት ክፍያዎን ይፈጽሙ (የማረጋገጫ አጭር የፅሁፍ መልዕክት ይደርስዎታል)
አመታዊ የግብር ክፍያዎትን በቀላሉ በቴሌብር ይክፈሉ (*127#)
- *127# ይደውሉ
- 4 ቁጥርን ይምረጡ (ለግብር ክፍያ)
- 1 ቁጥርን ይምረጡ (አዲስ አበባ)
- የክፍያ ማዘዣ ቁጥርዎን ያስገቡ፣
- የክፍያ ዝርዝር መረጃዎን በማየት ለማረጋገጥ 1 ቁጥርን ያስገቡ፣
- የክፍያ ምክንያት ያስገቡ፣
- የሚስጥር ቁጥርዎን በማስገባት ክፍያዎን ይፈጽሙ (የማረጋገጫ አጭር የፅሁፍ መልዕክት ይደርስዎታል)
አካውንት ለመክፈት
- የቴሌብር ሱፐርአፕን መጠቀም ይኖርብዎታል
- መተግበሪያዎች የሚለውን ይምረጡ
- የትምህርት ቤት ክፍያ የሚለውን መተግበሪያ ይጫኑ
- “Create Account” የሚለውን በመምረጥ ለተማሪው አካውንት ይፍጠሩ
በቴሌብር ሱፐርአፕ ክፍያ ለመፈፀም
- ክፍያ የሚለውን ይምረጡ
- የትምህርት ክፍያ የሚለውን ይጫኑ
- በቴሌብር የትምህርት ቤት ክፍያ የሚለውን ይምረጡ
- ከትምህርት ቤቱ የሚሰጥዎትን የክፍያ ቁጥር በማስገባት ይቀጥሉ
- የመጣልዎትን መረጃ በማየት “ይቀጥሉ” የሚለውን ይጫኑ
- የሚስጥር ቁጥርዎን በማስገባት ቀጥሎ “ይክፈሉ” የሚለውን ይጫኑ
በአጭር ቁጥር ክፍያ ለመፈፀም
- *127# ይደውሉ
- #ን በመጫን ወደ ቀጣይ ማውጫ ይሂዱ
- 8ን በመጫን በቴሌብር ለመክፈል የሚለውን ይምረጡ
- #ን በመጫን ወደ ቀጣይ ማውጫ ይሂዱ
- 7ን በመጫን በቴሌብር የትምህርት ቤት ክፍያ ይምረጡ
- 1ን ይምረጡ
- የክፍያ ቁጥር ያስገቡ
- ለማረጋገጥ 1ን ያስገቡ
- የሚስጥር ቁጥርዎን በማስገባት ይጨርሱ