ለቴሌብር አገልግሎት ይመዝገቡ

 ለቴሌብር አገልግሎት ይመዘገቡ የ15 ብር ስጦታ ያግኙ!

የቴሌብር አካውንት በቴሌብር የሞባይል መተግበሪያ ሲከፍቱ 100 ሜ.ባ ነጻ የዳታ ስጦታ ያገኛሉ፡፡

የቴሌብር ደንበኝነት ደረጃዎች እና የመመዝገቢያ መስፈርቶች

ደረጃ 1 ደንበኞች

የደረጃ 1 አካውንት ደንበኞች ማስቀመጥ የሚገባቸው ከፍተኛው የገንዘብ መጠን 5,000 ብር ሲሆን፣ በቀን እና በወር የሚያከናውኑት የገንዘብ ግብይት እንቅስቃሴ መጠን ገደብ የለውም፡፡

     የምዝገባ መስፈርቶች

  • የአመልካቹ ሙሉ ስም ወይም የአካውንት ስም
  • የአመልካቹ የትውልድ ቦታና ቀን
  • የአመልካቹ የሞባይል ቁጥር
  • አመልካቹ በቅርቡ የተነሳው ፎቶ
  • አመልካቹ አሁን የሚኖርበት አድራሻ
  • አመልካቹ ከዚህ በፊት የቴሌብር አካውንት ባለው ሰው መተዋወቅ ወይም መቅረብ አለበት
  1. ደረጃ 2 እና 3 ደንበኞች

 

የደረጃ 2 አካውንት ደንበኞች ማስቀመጥ የሚገባቸው የገንዘብ መጠን የተነሳ ሲሆን ደንበኞች  ያልተገደበ የገንዘብ ግብይት እንቅስቃሴ ማከናወን ይችላሉ፡፡

     

የምዝገባ መስፈርቶች

  • የአካውንቱ ባለቤት መታወቂያ
  • የአመልካቹ ሙሉ ስም ወይም የአካውንት ስም
  • የአመልካቹ የትውልድ ቀን
  • የአመልካቹ የሞባይል ቁጥር
  • አመልካቹ በቅርቡ የተነሳው ፎቶ
  • አመልካቹ አሁን የሚኖርበት አድራሻ

  • የንግድ ፈቃድ
  • የሞባይልቁጥር
  • የሲምካርድመለያወይምሴሪያልቁጥር
  • አድራሻ (የመኖሪያቦታ፣ዋናከተማ፣መንገድ፣ፖስታሳጥንቁጥር)

  • አጭር ቁጥር
  • የድርጅቱ ስም
  • ክልል
  • አድራሻ (ከተማ፣ ዋና ከተማ)
  • የፖስታ ሳጥን ቁጥር

ü  የፈራሚው ስምü  የፈራሚው የሞባይል ቁጥርü  የፈራሚው ኢ-ሜይል

  • የንግድ ፈቃድ
  • የሞባይል ቁጥር
  • የሲም ካርድ መለያ ወይም ሴሪያል ቁጥር
  • አድራሻ
  • የህጋዊ ወኪሉ መታወቂያ
  • ኦሪጅናል የፍቃድ ሰነድ
  • የምዝገባ ቅጽ
  • የውክልና ደብዳቤ
  • የተወካይ መታወቂያ
  • የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር

ለግለሰብ የቴሌብር ደንበኝነት ምዝገባ ከዚህ በታች የተጠቀሱትና የታደሱ መታወቂያዎች ተቀባይነት አላቸው፡፡

  • ህጋዊ የቀበሌ መታወቂያ
  • ህጋዊ ጉዞ ሰነድ ወይም ፓስፖርት
  • ህጋዊ የግብር ከፋይነት መታወቂያ
  • ህጋዊ የመንጃ ፈቃድ
  • የተማሪ መታወቂያ
  • የሰራተኛ መታወቂያ

የቃላት ትርጉም

  • ቴሌብር፡- ሞባይል ስልክ ቁጥርን በመጠቀም ግብይት መፈጸም፣ ገንዘብ ማስቀመጥ፣ መላክ፣ መቀበል እና የተለያዩ የአገልግሎት ክፍያዎችን ለማከናወን የሚያስችል አገልግሎት ነው።
  • ዋና ወኪል (Master Agent)- የቴሌብር አገልግሎትን ለመስጠት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ህጋዊ ስምምነት ያለውና ኢትዮ ቴሌኮምን ወክሎ ወይም የውክልና አገልግሎት ለደንበኞች የሚሰጥ አካል ወይም ድርጅት ሲሆን ኢትዮ ቴሌኮምን ወክሎ ለወኪሎች አገልግሎት ለመስጠት የውል ስምምነት ማከናወን ይጠበቅበታል፡፡
  • ወኪል፡- የኤጀንሲ የቢዝነስ አገልግሎትን ለማስተባበር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የውል ስምምነት ያለውና የኢትዮ ቴሌኮም ስምና ውክልና መመሪያዎችን ተከትሎ እንዲሁም በሌሎች አግባብነት ባላቸው ህጎች መሰረት አገልግሎት የሚሰጥ አካል ወይም ተቋም ነው።
  • ገንዘብ ማስገባት፡- ይህ ሂደት ተጠቃሚው አካል ገንዘቡን በኤሌክትሮኒክ የግብይት ሥርዓት ወደ አካውንቱ በማስገባት ያለውን የተቀማጭ ገንዘብ መጠን መጨመር ነው።
  • ገንዘብ ማውጣት፡- ተጠቃሚው አካል በቴሌብር ያከማቸውን ገንዘብ ለአገልግሎት ክፍያ በማዋል ወይም ወደ ሌላ አካውንት በማስተላለፍ የነበረውን ተቀማጭ ገንዘብ መጠን መቀነስ ወይም መጨረስ ነው፡፡
  • የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ፡- ተቀማጭ የተደረገው የገንዘብ ዋጋ ወይም እሴት በተጠቃሚው አካል ተቀባይነቱን ለማረጋገጥ የሚከተሉትን ሁኔታዎች ሲያሟላ ነው።
  • የኢትዮጵያንብርበሚጠቀሙአካላትተቀባይነቱሲረጋገጥ
  • ገንዘቡህጋዊካደረገውአካልይልቅሰዎችእንደመገበያያነትለመጠቀምሲቀበሉት
  • በኢትዮጵያብርከሚከናወንየኤሌክትሮኒክገንዘብጋርእኩልዋጋሲኖረው
  • በኤሌክትሮኒክመሳሪያገንዘቡንማስቀመጥሲቻል

ለቴሌብር አገልግሎት እንዴት መመዝገብ ይቻላል?

ለቴሌብር አገልግሎት ስልክዎን በመጠቀም በሞባይል መተግበሪያ ወይም በቴሌብር አጭር ቁጥር ወይም በአቅራቢያዎ በሚገኝ የኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከል እንዲሁም በህጋዊ ወኪሎች ወይም በአጋር የባንክ ቅርንጫቾች መመዝገብ ይችላሉ፡፡

  • አዲስ አካውንትየሚለውን ይምረጡ
  • ፈጣን አካውንት ይክፈቱ ወይም በራስ አገዝ አካውንት ይክፈቱ የሚለውን ይምረጡ
  • የሞባይል ቁጥርዎን ያስገቡና ማረጋገጫ ቁጥር ያግኙ የሚለውን ይጫኑ
  • ቀጥሎ ባለ 6 አሃዝ የማረጋገጫ ቁጥር በአጭር የፅሁፍ መልዕክት ይደርስዎታል
  • የደረስዎትን የማረጋገጫ ቁጥር ያስገቡና ይቀጥሉ የሚለውን ይጫኑ
  • ከታች የተዘረዘሩትን የግል መረጃዎች ይሙሉ
    • ማዕረግ
    • የመታወቂያ አይነት
    • የመታወቂያ ቁጥር
    • ስም፤ የአባት ስም፤ የአያት ስም
    • ጾታ
    • የትውልድ ቀን
    • መጠቀም የሚፈልጉበት ቋንቋ
  • የግል መረጃዎን ሞልተው ካረጋገጡ በኋላ ያስገቡ የሚለውን ይጫኑ
  • በመቀጠል በአጭር ፅሁፍ መልዕክት የሚስጢር መለያ ቁጥር (PIN) ይደርስዎታል
  • የደረስዎትን የሚስጥር መለያ ቁጥር (PIN) በመጠቀም ይግቡ የሚለውን ይጫኑ
  • አገልግሎቱን ለማስጀመር የሚስጢር መለያ ቁጥሩን በአዲስ ይቀይሩ (የራስዎትን የሚስጥር ቁጥር ይጠቀሙ) ከዚያም ለመጨረስ የሚለውን ይጫኑ
  • የቴሌብር አካውንትዎ በተሳካ ሁኔታ መጀመሩን የሚገልፅ አጭር የፅሁፍ መልዕክት ይደርስዎታል፡፡
  • ወደ *127# ይደውሉ
  • ለመመዝገብ 1 ቁጥርን ይላኩ
  • የተላከልዎትን የግብዣ መለያ ቁጥር ሲያስገቡ ወይም የ # ሲልኩ ወደ ቀጣይ ገጽ ያልፋሉ 
  • በድጋሜ *127# ይደውሉ
  • ለማስጀመር ዜሮ (0) ይላኩ
  • ቋንቋ ይምረጡ
  • በ 127 የደረስዎትን የሚስጢር ቁጥር በማስገባት በራስዎ አዲስ የሚስጢር ቁጥር ይቀይሩ
  • ከዚያም የቴሌብር አካውንትዎ በተሳካ ሁኔታ መጀመሩን የሚገልፅ አጭር የፅሁፍ መልዕክት ይደርስዎታል፡፡

አገልግሎቱን እንዲሰጥ ህጋዊ ፈቃድ በተሰጠው ወኪል ወይም በሽያጭ ማዕከላችን ለመመዝገብ:

    • በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ ወኪል ወይም የኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከል በአካል በመቅረብ
    • አገልግሎት ላይ ያለ የስልክ ቁጥርዎን እና የራስዎ ስለመሆኑ ለወኪሉ ማረጋጫ በማቅረብ (ማንነትዎን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ)

) የቴሌብር የሞባይል መተግበሪያን በመጠቀም

  1. የመተግበሪያው የመጀመሪያ ገፅ ላይ ከታች በቀኝ በኩል የሚገኘውን “የኔ አካውንት” የሚለውን ይክፈቱ
  2.  “ጓደኛ ለመጋበዝ” የሚለውም ይምረጡ
  3. የጓደኛዎን የሞባይል ቁጥር በማስገባት ላክየሚለውን ይምረጡ

) አጭር ቁጥር በመጠቀም ለመጋበዝ

  1. ወደ *127# ይደውሉ
  2. # ምልክትን በማስገባት ጓደኛ ለመጋበዝ የሚለውን (ቁጥር 9) ይምረጡ
  3. የጓደኛዎትን የሞባይል ስልክ ቁጥር ያስገቡ
  4. የሚስጥር ቁጥርዎትን ያስገቡ
  5. እሺ የሚለውን በመምረጥ ያስገቡትን ስልክ ያረጋግጡ

  የማረጋገጫ መልዕክት በ 127 ይደርስዎታል፡፡

ለአዲስ ተመዝጋቢዎች

  • ለአገልግሎት ሲመዘገቡ የ15 ብር ስጦታ ያገኛሉ።
  • ባገኙት ስጦታ ለሞባይል አየር ሰዓት መሙላት ወይም ወደ ሌላ ሰው ማስተላለፍ ይችላሉ።
  • የ15 ብር ስጦታው የቴሌብር አገልግሎት ላስጀመሩ ደንበኞች ብቻ ይሰጣል።
  • ለ 2ኛ ወይም 3ኛ ጊዜ ተደጋጋሚ ምዝገባ የማበረታቻ ስጦታ አይኖርም

70 ሜባ ነፃ እንተርኔት

  • የቴሌብር የሞባይል መተግበሪያን አውርደው ለአገልግሎቱ ሲመዘገቡ 70 ሜ.ባ. የኢንተርኔት አገልግሎት ስጦታ ያገኛሉ፡፡
  • የኢንተርኔት ስጦታ አካዉንት ወደ ተከፈተበት ስልክ ቁጥር ይገባል፡፡
  • ደንበኞች፣ ወኪሎች፣ ነጋዴዎች እና ዋና ወኪሎች የቴሌብር ማመልከቻ ደብዳቤን በነጻ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።

 የአየር ሰዓት ሲሞሉ

  • ቴሌብርን አጭር ቁጥር 127/ መተግበሪያ ተጠቅመው የአየር ሰዓት ሲገዙ እስከ 5 ቀናት የሚያገለግል 10% የአየር ሰዓት ስጦታ

 የሞባይል ጥቅል ሲገዙ

  • ቴሌብር የሞባይል መተግበሪያን በመጠቀም ለሚገዙ ጥቅሎች 10% ስጦታ ይሰጣል።
  • ስጦታው የተገደበ ጥቅል ለሚገዙ ደንበኞች ብቻ ያገለግላል፡፡

 

1. ስምምነቱ
1.1. የሚከተሉት ደንብና ሁኔታዎች የቴሌብር የላቀ መተግበሪያ (Super-app) እና አገልግሎቶች አጠቃቀምን በተመለከተ ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡ ይህን የላቀ መተግበሪያ ለመጠቀም የሚከተለሉትን ደንብና ሁኔታዎችን ማንበብ፣ መረዳት እና መቀበል ይኖርብዎታል፡፡
1.2. እባክዎ በመተግበሪያው የሚቀርቡ አገልግሎቶችን ለመጠቀም የሚያስችሉ ፖሊሲ፣ ደንቦችና እና ግዴታዎችን ለማወቅ እንዚህን ደንብና ሁኔታዎች በጥንቃቄ ያንብቡ፡፡
2. የስምምነቱ ዓላማ
2.1. የዚህ ሰምምነት ዓላማ የኢትዮ ቴሌኮም (ቴሌብር) ደንበኞች መተግበሪያውን ለመጠቀም፣ በቴሌብር የሚቀርቡ አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚያስችላቸውን ደንብና ሁኔታዎን ለመቆጣጠር ነው፡፡
3. የቴሌብረ የላቀ መተግበሪያ (telebirr Super App)
3.1. ይህ የቴሌብር የላቀ መተግበሪያ ደንበኞች የቴሌብር አገልግሎቶችን ማለትም የክፍያ አገልግሎቶች (ለንግድ እና አገልግሎቶች ክፍያ፣ ለመንግስታዊ አገልግሎቶች ክፍያ እና የማህበራዊ ኋላፊነት)፣ የፋይናንሻል አገልግሎቶች (አነስተኛ ብድር፣ ቁጠባ እና ከተቀማጭ በላይ መጠቀም)፣ ዓለምአቀፍ ኃዋላ፣ በአገር ውስጥ ገንዘብ ማስተላለፍ፣ ተቀማጭ ማድረግ እና ገንዘብ ወጪ ማድረግ፣ ምዝገባ፣ እንዲሁም የቴሌብር ሂሳብዎን ለማወቅ ፣ የሂሳብ መግለጫ እና የደንበኝነት መረጃዎን መመልከት ያስችላል፡፡
4. የኢትዮ ቴሌኮም ደንብና ሁኔታ
4.1. ኢትዮ ቴሌኮም የደንበኞችን ፍላጎት ለማርካት የተለያዩ የቴሌብር አገልግሎቶችን ያቀርባል፡፡
4.2. ኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች በሚጠቀሙት መተግበሪያ እና የሚቀርቡ አገልግሎቶችን በተለመከተ የመከታተለል እና የመቆጣጠር እንዲሁም አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ የመውሰድ መብት አለው፡፡
4.3. ኢትዮ ቴሌኮም ያቀረበውን የቴሌብር የላቀ መተግበሪያ እና የመጠቀሚያ ገፅታዎችን/ዓይነቶችን እንዲሁም ከዚህ ጋር ተያይዞ ያሉትን ደንብና ሁኔታዎች የማሻሻል፣ ለየት ማድረግ እና የማስተካከል ምቱ የተጠበቀ ነው፡፡ የሚደረጉ ለውጦችንም በኢትዮ ቴሌኮም ድረ-ገፅ እና ማህበራዊ ሚዲያወች ላይ የሚገለፁ ይሆናል፡፡
5. የደንበኞች መብትና ግዴታ
5.1. ደንበኞች መተግበሪያውን ከፕሌይ ስቶር ወይም ከአፕስቶር ማውረድ እና በሞባይል ስል ወይም በታብሌታቸው ላይ መጫን ይችላሉ፡፡
5.2. ደንበኞች መተግበሪያውን በኢትዮ ቴሌኮም ለፈቀደው ዓላማ ብቻ መጠቀም ይኖርባቸዋል፡፡
5.3. ደንበኞች የላቀ መተግበሪያውን ከኢትዮ ቴሌኮም ደንብና ሁኔታዎች በተፃራሪ ያለአግባብ ሲጠቀሙ ከተገኙ ኩባንያው መተግበሪያውን በቀጣይ እንዳይጠቐሙ ሊያግድ ይችላል፡፡
5.4. ደንበኞችየይለፍ ቃላቸውን እና የአካውንት ዝርዝር መረጃቸውን ለማንም ሰው ማጋራት ወይም መስጠት የለባቸውንም፡፡
5.5. ደንበኞች ያልተፈቀደለት ሰው የይለፍ ቃላቸውን እና አካውንታቸውን ይጠቀምበታል ብለው ከተጠራጠሩ፣ ስልካቸው ከተሰረቀባቸው ወይም ከጠፋባቸው ወደ 127 በመደወል ለኩባንያን ማሳወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
5.6. ኢትዮ ቴሌኮም እንደአስፈላጊነቱ ደንበኞች የቴሌብር የላቀ መተግበሪያ ከመጠቀማቸው በፊት የቴሌብር ተጠቃሚ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ተጨማሪ መረጃዎችን እንዲያስገቡ ሊጠይቅ ይችላል፡፡
5.7. ተጨማሪ መረጃዎች የሚባሉት ለአንድ ጊዜ የሚያገልግል የይለፍ ቃል፣ ማንነትን ለማወቅ የሚያስችል አሻራ፣ የሚስጥር ጥያቄዎች ወይም የሚስጥር መለያዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
5.8. ደንበኞች የቴሌብር የላቀ መተግበሪያ የሚቀርቡ ምርትና አገልግሎቶችን ለመጠቀም እንዚህን ደንብና ሁኔታዎች እንዲሁም የኢትዮ ቴሌኮም የአሠራር ፖሊሲን እዲቀበሉ ይጠየቃሉ፡፡
6. ሚስጥር መጠበቅን በተመለከተ
6.1. ኢትዮ ቴሌኮም የደንበኞችን ዳታ እና ምስጦር ያከብራል፣ ይጠብቃል፡፡
6.2. ሆኖም ኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቶቹን እና ምርቶቹን ለማቅረብ ለማሻሻል የደንበኞችን ዳታ ለመጠቀም ይችላል፡፡
7. ማሻሻያዎች
7.1. ኢትዮ ቴሌኮም እነዚህን ደንብና ሁኔታዎች እንደአስፈላጊነቱ በየጊዜው የመጨመር ወይም የማሻሻል መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
7.2. እነዚህ ደንብና ሁኔተዎች በኢትዮጵያ ሕግ መሰረት የሚተዳደሩ ይሆናል፡፡
7.3. እነዚህ ደንብና ሁኔታዎች www.ethiotelecom.et. ላይ ይገኛሉ፡፡