- ይህ የአገልግሎት አይነት የቴሌብር ደንበኞች በቴሌብር አካውንት ያላቸው ቀሪ የሂሳብ መጠን በቂ ባልሆነበት ጊዜ ክሬዲት አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል አገልግሎት ነው፡፡
- ደንበኞች በሚፈቀደው ዝቅተኛ እና ከፍተኛ የክሬዲት መጠን መካከል ማንኛውንም መጠን መበደር ይችላሉ።
የቴሌብር እንደኪሴ አገልግሎት ለማግኘት ብቁ የሚያደርጉ መስፈርቶች
- የደንበኛ የመበደር አቅም ደንበኛው ባደረገው የ6 ወር የቴሌብር የገንዘብ እንቅስቃሴ እና በቴሌኮም አጠቃቀም ይወሰናል።
- በተጨማሪም ከታች ያሉት የቴሌብር ግብይቶች እና የገንዘብ ልውውጥ የደንበኛ የብድር አቅምን ለማስላት የሚውሉ ይሆናል።
- ለእርስዎ ወይም በስጦታ የአየር ሰዓት መሙላት ወይም ጥቅል
መግዛት (በራስ አገዝ ወይም ከወኪሎች) - ዕቃ ወይም አገልግሎት ግዢን መፈጸም
- ለእርስዎ ወይም የሌላ ደንበኛ ቢል ክፍያ (በራስ አገዝ ወይም
ከወኪሎች) ማከናወን - ለእርስዎ ወይም የሌላ ደንበኛን የፍጆታ አገልግሎት ክፍያ (በራስ አገዝ ወይም ከወኪሎች) መፈፀም
- ከውጭ አገር ገንዘብ መቀበል
- የጅምላ ክፍያ (ደሞዝ፣ ሴፍቲኔት…) መፈፀም
- የትኬት ክፍያ መፈፀም
- ለገንዘብ ማሰባሰቢያ የእርዳታ ክፍያ መፈፀም
- የቁጠባ አገልግሎት
- የቴሌኮም ፍጆታ (ድምጽ፣ ዳታ ወይም መልዕክት) መፈፀም
- ለእርስዎ ወይም በስጦታ የአየር ሰዓት መሙላት ወይም ጥቅል
• ከቴሌኮም አገልግሎት ፍጆታ በተጨማሪ ቢያንስ አንድ የቴሌብር አገልግሎት መጠቀም ይኖርብዎታል፡፡
• የ6 ወራት ግብይት ወይም አጠቃቀም ለብቁነት መስፈርት የሚቆጠር ይሆናል።
• በሚፈቀደው ዝቅተኛ እና ከፍተኛ የክሬዲት መጠን መካከል ማንኛውንም መጠን መበደር ይችላሉ።
የቴሌብር እንደኪሴ ማስጀመሪያ መስፈርቶች
- 18 አመት እና ከዚያ በላይ
- አገልግሎት የሚሰጥ የኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርድ መያዝ
- የቴሌብር እና የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቶችን እንደ ዳታ/ድምጽ/አጭር የጽሁፍ መልዕክት መጠቀም ይኖርብዎታል፡፡
- ለመመዝገብ በአጭር ቁጥር (*127#) ወይም በቴሌብር መተግበሪያን ይጠቀሙ፡፡
- የቴሌብር የደንበኝነት ቆይታ 3 ወር እና ከዛ በላይ መሆን ይኖርበታል፡፡
መስፈርቶቹን በመጠቀም ነጥቡ እንዴት እንደሚሰራ
ስኮሪንግ ባንድ ሬንጅ | የብድር መጠን ገደብ | ||
ዝቅተኛ | ከፍተኛ | ዝቅተኛ | ከፍተኛ |
0 | 650 |
0 |
0 |
651 | 660 | ||
671 | 680 | ||
681 | 690 | ||
691 | 700 | ||
701 | 710 | ||
711 | 720 | ||
721 | 730 |
1 | 5 |
731 | 740 | 50 | |
741 | 750 | 100 | |
751 | 760 | 200 | |
761 | 770 | 300 | |
771 | 780 | 400 | |
781 | 790 | 500 | |
791 | 800 | 600 | |
801 | 810 | 700 | |
811 | 820 | 800 | |
821 | 830 | 1000 | |
831 | 840 | 1200 | |
841 | 850 | 1500 | |
851 | 860 | 1500 |
በቴሌብር
የሞባይል መተግበሪያ
እንዴት አገልግሎቱን ማስጀመር እና መጠቀም እንችላለሁ?
አገልግሎቱን ለማስጀመር
- የፋይናንስ አገልግሎት የሚለውን ይጫኑ
- ቴሌብር እንደኪሴ የሚለውን
ይምረጡ - ደንብ እና ሁኔታዎችን በማንበብ የ √ ምልክት በመጫን መስማማትዎን ይግለጹ
- ለማስጀመር የሚለውን ይጫኑ
አገልግሎቱን ለመጠቀም
- ቀሪ ሂሳብዎ አነስተኛ ሆኖ የተለያዩ አገልግሎቶችን ሲጠቀሙ ለሚደርስዎት የክሬዲት ክፍያ መጠቀም እንደሚፈልጉ የሚጠይቀውን ማሳወቂያ መስማማትዎን ይግለጹ
የወሰዲትን ክሬዲት ለመክፈል
- የቴሌብር አካውንትዎ ላይ ገንዘብ ተቀማጭ ያድርጉ
1. የውል ስምምነት
ይህ ስምምነት (ከዚህ በኋላ "ደንቦች እና ሁኔታዎች" የሚባል) የክሬዲት ክፍያ አገልግሎትን በተመለከተ አጠቃላይ ደንብ እና ሁኔታዎች ያካትታል፡፡
እነዚህ ደንቦችና ሁኔታዎች እንዲሁም ከዚህ ጋር የተያያዙ ማሻሻያዎች እና ለውጦች በክሬድት ደንበኛው ተነበው ተቀባይነት ሲያገኙ (ይሲማሙ የሚለውን ምርጫ ሲጫኑ) ሥራ ላይ ይውላሉ፡፡
2. ትርጓሜ
በዚህ የደንቦች እና ሁኔታዎች መረጃ ውስጥ የተዘረዘሩ ቃላት እና አባባሎች የሚከተለውን ትርጉሜ ይይዛሉ፡
- " የቴሌብር እንደኪሴ ክሬዲት ክፍያ አገልግሎት" ማለት ለግለሰብ ደንበኞች በኤሌክትሮኒክ ገንዘብ አነስተኛ መጠን ያለው ክሬዲት የሚያገኙበት የአገልግሎት አይነት ነው።
- “የክሬዲት ክፍያ” ማለት ከታች በተቀመጡ ደንብ እና ሁኔታዎች መሰረት በኢትዮ ቴሌኮም ለደንበኞች የሚቀርብ የክሬዲት አገልግሎት ነው፡፡
- “የግለሰብ ደንበኛ” ማለት በስሙ አነስተኛ የቁጠባ አካውንት ያለው የቴሌብር ደንበኛ ነው።
- "አንተ" "አንቺ" ወይም "የአንተ" ማለት ደንበኛውን ለማለት ነው።
- “ኤ-ገንዘብ” ማለት እኩል መጠን ያለው ጥሬ ገንዘብን የሚወክል ደንበኛው የሚመለከተው የቴሌብር የኤሌክትሮኒክስ የገንዘብ ዋጋ ነው።
- "ዋና መጠን" ማለት መጀመሪያ እንደመነሻ ከኢትዮ ቴሌኮም የተወሰደ የክሬዲት መጠን ነው፡፡
- “ደንበኛ” ማለት በስሙ በቴሌብር አካውንት ለክሬዲት ክፍያ የተመዘገበ የቴሌብር ተመዝጋቢ ነው።
- "አንተ" "አንቺ" ወይም "የአንተ" ማለት ደንበኛውን ለማለት ነው።
- "ዋና ገንዘብ" ማለት በመጀመሪያ በክሬዲት የወሰዱት የገንዘብ መጠን ማለት ነው።
- "የግብይት ክፍያ" የአገልግሎት ክፍያ፣ የቅጣት እና ሌሎች ለክሬዲት ክፍያ አገልግሎት የሚከፈሉ ክፍያዎችን ያጠቃልላል፡፡
- “የአገልግሎት ክፍያ” ማለት የክሬዲት ክፍያ አገልግሎትን ለመጠቀም በደንበኞች የሚከፈል የክፍያ መጠን ነው።
- "የቅጣት ክፍያ" ማለት ለክሬዲት የመጨረሻ መክፍያ ቀነ ገደቡ አልፎ ክፍያው ሲፈጸም የሚከፍል ተጨማሪ የክፍያ መጠን ነው፡፡
- "የመጨረሻ ክፍያ ቀን" ማለት የክሬዲት መመለሻ የጊዜ ገደብ (ገባሪ የክሬዲት ጊዜ) ያላለፈ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን ክሬዲት ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ 30 ቀናትን የሚያካትት ነው፡፡
- "ቀነ ገደቡ ያለፈ" ማለት የክሬዲት መመለሻ ቀነ ገደቡ ያለፈ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
- "የተበላሸ ብድር" ማለት ክሬዲት ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በ90 ቀናት ውስጥ ያልተከፈለ ክሬዲት ሲሆን በወቅቱ ባለመመለሱ እንደ ተበላሸ ብድር መሆኑን የሚያሳይ ጊዜ ነው፡፡
3. ደንብ እና ሁኔታዎችን ስለመቀበል
- የክሬዲት ክፍያ አገልግሎትን ለመጠቀም ከማመልከትዎ በፊት እነዚህን ደንብ እና ሁኔታዎች በጥንቃቄ በማንበብ የክሬዲት ክፍያ ሂሳብ አጠቃቀም እና መመሪያን አንብበው ይስማሙ፡፡
- በእነዚህ ደንቦችና ሁኔታዎች ካልተስማሙ እባክዎን ከዝርዝር መምረጫ ውስጥ ሰርዝ የሚለውን ይጫኑ፤
- ደንቦችና ሁኔታዎችን እንዳነበቡ፣ እንደተረዱና እንደተቀበሉ የሚቆጠረው፡-
- “ይስማሙ” የሚለውን አማራጭ ሲጫኑ ደንብ እና ሁኔታዎችን በማንበብ ተረድተው ለማክበር መስማማትዎን እንዳረጋግጡ ወይም ክሬዲት ክፍያን ለመጠቀም እንደተስማሙ ይወሰዳል።
- ደንብ እና ሁኔታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በኢትዮ ቴሌኮም እና በዳሽን ባንክ ሊሻሻሉ ወይም ሊለወጡ የሚችሉ ሲሆን በቴሌብር ፖርታል ወይም ድህረ ገጽ ላይ ከተለቀቁበት ዕለት ጀምሮ በደንበኛው ላይ ተግባራው ይደረጋሉ፡፡
- የክሬዲት ክፍያ አገልግሎትን በኤሌክትሮኒካዊ መንገድ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ለመተግበር እና የክሬዲት ክፍያ አገልግሎትን በኤሌክትሮኒካዊ መንገድ በቴሌብር ሲስተም ለመጠቀም ተስማምተዋል።
4. የክሬዲት ክፍያ አገልግሎትን ለማስጀመር
የክሬዲት ክፍያ አገልግሎትን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ለማስጀመር ቢያንስ፡-
- 18 አመት እና ከዚያ በላይ
- አገልግሎት የሚሰጥ የኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርድ መያዝ
- የቴሌብር እና የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቶችን እንደ ዳታ/ድምጽ/አጭር የጽሁፍ መልዕክት የሚጠቀሙ
- የቴሌብር የደንበኝነት ቆይታ 3 ወር እና ከዛ በላይ መሆን አለበት
- ለመመዝገብ በዩኤስኤስዲ (*127#) ወይም በቴሌብር መተግበሪያ መጠቀም ይችላሉ፡፡
- ለተሳካ ምዝገባ የማሳወቂያ አጭር የፅሁፍ መልዕክት ይደርስዎታል፡፡
5. የክሬዲት ክፍያ አገልግሎት ለማግኘት መሰረታዊ መስፈርቶች
- የደንበኛ የመበደር አቅም ደንበኛው የክሬዲት ክፍያ አገልግሎት ለመጠቀም ጥያቄ ካቀረበበት ቀን በፊት ባደረገው የ6 ወር የቴሌብር የገንዘብ እንቅስቃሴ እና በቴሌኮም አጠቃቀም ይወሰናል። ከታች ያሉት የቴሌብር ግብይቶች እና የገንዘብ ልውውጥ የደንበኛ የብደር አቅምን ለማስላት ይውላሉ።
- ለእርስዎ ወይም ለስጦታ የአየር ሰዓት መሙላት ወይም ጥቅል መግዛት (በራስ አገዝ ወይመ ከወኪሎች)
- ዕቃ ወይም አገልግሎት በመግዛት ግብይት መፈጸም
- ለእርስዎ ወይም የሌላ ደንበኛ ቢል ክፍያ (በራስ አገዝ)
- ለእርስዎ ወይም የሌላ ደንበኛ የፍጆታ አገልግሎት ክፍያ (በራስ አገዝ)
- ከውጭ አገር ገንዘብ መቀበል
- የጅምላ ክፍያ (ደሞዝ፣ ሴፍቲኔት…)
- የትኬት ክፍያ
- ለገንዘብ ማሰባሰቢያ የእርዳታ ክፍያ
- የቁጠባ አገልግሎት
- የቴሌኮም ፍጆታ (ድምጽ፣ ዳታ ወይም መልዕክት)
- ከቴሌኮም አገልግሎት ፍጆታ በተጨማሪ ቢያንስ አንድ የቴሌብር አገልግሎት መጠቀም ይጠበቅብዎታል፡፡
- የ6 ወራት ግብይት ወይም አጠቃቀም (አንፃራዊ ወር) ለብቁነት ይቆጠራል።
6. የክሬዲት መጠን እና ክፍያ
- በሚፈቀደው ዝቅተኛ እና ከፍተኛ የክሬዲት መጠን መካከል ማንኛውንም መጠን መበደር ይችላሉ።
- ሌላ ክሬዲት ለማግኘት መጀመሪያ ቀድመው የወሰዱትን ክሬዲት መክፈል ይጠበቅብዎታል፡፡
- ያለብዎትን ክሬዲት በከፊል ወይም በሙሉ መክፈል ይችላሉ።
- የክሬዲት መክፈያ ማብቂያ ቀነ ገደብ ቡድሩን ከወሰዱበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 30 ቀናት ውስጥ ይሆናል።
- ያለብዎትን የሰላሳ (30) ቀን ክሬዲት በአንድ ቀን ውስጥ ከከፈሉ የወሰዱትን የብድር መጠን 6% ሲሆን ከዚያ በኋላ ሲከፍሉ በቀን 138% የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላሉ፡፡
- ከ30 ቀን በኋላ ለሚከፍሉ የወሰዱትን የብድር መጠን ወይም በከፊል ተከፍሎ ባልተከፈለ ቀሪ ገንዘብ ላይ በቀን 2 % በመቶ የቅጣት ክፍያ እንዲከፍሉ ታሳቢ ይደረጋል።
- የክሬዲት ክፍያ የሚፈጸመው ማንኛውንም የገንዘብ መጠን ወደ ኢ-ገንዘብ አካውንታቸው ገቢ ሲሆን በቀጥታ በመቀነስ ነው።
- በጉርሻ የሚያገኙት ገንዘብ ለክሬዲት ክፍያ አይውልም፡፡
- ይህ የክሬዲት አገልግሎት የሚሰጠው ኢትዮ ቴሌኮም ከዳሸን ባንክ ጋር በመተባበር ነው፡፡ ለክሬዲት አገልግሎት የሚውለውን ገንዘብ የሚያቀርበው ዳሸን ባንክ ሲሆን ይህን ገንዘብ በባለቤትነት የሚቆጣጠረው ዳሸን ባንክ ነው፡፡ የተበላሸ ወይም ቀነ ገደቡ ያለፈ ብድር በሚከሰትበት ጊዜ ባንኩ ጉዳዩን ወደ መደበኛ ፍርድቤት የመውሰድና የመክሰስ ሙሉ መብት አለው፡፡ ከፍርድቤት ውጭ ያሉ አማራጮች የመጠቀም መብት አለው፡፡