ረጅም የቆይታ ጊዜ የሞባይል ጥቅል
ለሩብ ዓመት ወይም ዓመታዊ የሞባይል ጥቅል ይመዝገቡ! አገልግሎታችንን በቅናሽ ይጠቀሙ!
ደንብ እና ሁኔታዎችን ለማንበብ እዚህጋ ይጫኑ
- ሁሉም የቅድመ ክፍያ ሞባይል፣ የድህረ ክፍያ ሞባይል እና የሀይብሪድ ሞባይል አገልግሎት ደንበኞች የረጅም የቆይታ ጊዜ ሞባይል ጥቅል በማንኛውም ሰዓት መመዝገብና አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ለረጅም የቆይታ ጊዜ ጥቅል ሲመዘገቡ የመረጡትን ጥቅል ዋጋ አንድ ጊዜ ብቻ የሚከፍሉ ይሆናል፡፡
- ለሩብ ዓመት ወይም ለ 90 ተከታታይ ቀናት ፕላን በሽያጭ ማዕከላችን ለሚመዘገቡ ደንበኞች ሁለት ዓይነት የጥቅል መልቀቂያ አማራጮች ያሉ ሲሆን
- ሁሉም የጥቅል አገልግሎቶቹ በአንድ ጊዜ እስከ አገልግሎት ማብቂያ ድረስ የሚለቀቁ ሲሆን ሌላኛው ደሞ
- የተጠቀሱትን የጥቅል አገልግሎቶች የአገልግሎት ቀነ ገደቡ እስኪያልቅ ድረስ በየወሩ ከፋፍሎ የሚቀርብ ሲሆን ያልተጠቀሙት ቀሪ ጥቅል ካለ ወደ ቀጣይ ወር የሚተላለፍ ይሆናል፡፡
- የቅድመ ክፍያ ሞባይል ተጠቃሚዎች በአጭር ቁጥር *999#፣ በማይ ኢትዮቴል መተግበሪያ እና የሽያጭ ማዕከላችን በመቅረብ መመዝገብ ይችላሉ፡፡ የድህረ ክፍያ ሞባይል ተጠቃሚዎች አገልግሎቱን በሽያጭ ማዕከሎቻችን በአካል በመቅረብ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የግለሰብም ሆነ የድርጅት ደንበኞች የረጅም የቆይታ ጊዜ ሞባይል ጥቅል አገልግሎት መመዝገብ ይችላሉ፡፡
- ደንበኞች የረጅም ጊዜ ጥቅልን ለራሳቸው መግዛት ወይም ለወዳጅ ዘመዶቻቸው በስጦታ መላክ ይችላሉ
- አንዴ ለረጅም የቆይታ ጊዜ ጥቅል ከተመዘገቡ ተመላሽ ሂሳብ መጠየቅ ወይም ወደ ሌላ የረጅም የቆይታ ጊዜ ጥቅል አማራጭ መቀየር አይፈቀድም፡፡
- ለረጅም የቆይታ ጊዜ የሞባይል ጥቅል ለመመዝገብ እየተጠቀሙበት ያለው ሲም ካርድ የሚሠራ መሆን አለበት፡፡
- የሞባይል ድምጽ እና የአጭር ጽሁፍ ጥቅሉ ለሀገር ውስጥ የጥሪና መልዕክት አገልግሎት ብቻ የሚውል ይሆናል፡፡
- ከገዙት ጥቅል ውጭ እንዲሁም አጭር ቁጥር ሲጠቀሙ መደበኛው የአገልገሎት ታሪፍ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
- ሁሉም ዋጋዎች የተጫማሪ እሴት ታክስን ያካትታሉ፡፡