- ደንበኞች መጠየቅ የሚችሉት ትንሹ የመጠባበቂያ የኃይል አቅርቦት 5 ኪሎ ዋት ሲሆን ትልቁ ደግሞ 15 ኪሎ ዋት ነው፡፡
- ይህ የኃይል አቅርቦት ለድርጅት እና ለግለሰብ ቪአይፒ ደንበኞች የቀረበ ነው፡፡
- ለ5 ኪሎ ዋት መጠባበቂያ ኃይል ሞጁል ተጨማሪ 5 ባትሪዎች እና 1 የኃይል መቆጣጠሪያ ሞጁል መግዛት ይቻላል፡፡
- ለ10 ኪሎ ዋት መጠባበቂያ ኃይል ሞጁል ተጨማሪ 4 ባትሪዎች በተጨማሪነት መግዛት ይቻላል፡፡
- ለ15 ኪሎ ዋት መጠባበቂያ ኃይል ሞጁል ተጨማሪ 6 ባትሪዎች በተጨማሪነት መግዛት ይቻላል፡፡
- የኢትዮ ቴሌኮም በኩል የቀረቡ መገልገያዎችን ለመቀየር ከዚህ በታች በተጠቀሱት የመቀየሪያ/የጥገና የዋስትና ጊዜ ውስጥ ብቻ ይሆናል፡፡
- ኢንቨርተር- ለ10 ዓመት
- መጠባበቂያ ሳጥን፣ ፓወር እና ባትሪ ሞጁል-ለ5 ዓመት
- የላቀ ኃይል ማከማቻ (Intelligent electric quantity collector)--ለ1 ዓመት
- መገልገያዎቹ በደንበኛ የአያያዝ ጉድለት፣ በአጠቃቀም ችግር እና ሆን ተብሎ የተፈጠረ ከሆነ በዋስትና የማይስተናገድ ይሆናል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ የድርጅት አገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችንን ይጎብኙ!