አሻምቴሌ

አገልግሎቶቻችንን ደጋግመው በመጠቀም ያግኙ!

አሻምቴሌ
  • አገልግሎቶቻችን ደጋግመው የሚጠቀሙ ደንበኞቻችን ከእኛ ጋር በመቆየታቸው የምንሸልምበት አሰራር ነው፡፡ ለአገልግሎቱ ይመዝገቡ! ነጥቦችን ይሰብስቡ! እንዳጠራቀሙት የነጥብ ብዛት የአየር ሰዓት እና ጥቅል መግዛት፣ ወርሃዊ የአገልግሎት ሂሳብ መክፈል እንዲሁም የድምፅ ጥሪ ማድረግ፣ ዳታ መጠቀም እና መልዕክት መላክ ወዘተ ይችላሉ፡፡ ረዘም ላለ ጊዜ የኢትዮ ቴሌኮም ኔትወርክን በመጠቀም ብዙ ነጥብ ከሰበሰቡ የስልክ ቀፎዎች፣ ታብሌቶች እና ላፕቶፖችን ያገኛሉ፡፡

 

Ashamtele

መስፈርቶቹ ምንድናቸው?

የሞባይል አገልግሎትን መጠቀም

ቅድመ ክፍያ ደንበኞች የአሻምቴሌ ነጥብ ለማግኘት
  • ለቅድመ ክፍያ አገልግሎት ደንበኞች ብር 2.5 እና ከዚያ በላይ በቀን ውስጥ መጠቀም

  • ለድህረ ክፍያ ደንበኞች ትንሹ ወርሃዊ የአገልግሎት ክፍያ 75 ብር

የቴሌብር አገልግሎቶችን መጠቀም

  • ሁሉም የቴሌብር ደንበኞች የአሻምቴሌ ተጠቃሚ ይሆናሉ
    • 1 ብር የአየር ሰዓት ሲሞሉ 2 ነጥብ ያገኛሉ)
  • ቴሌብርን ተጠቅመው ግብይት መፈፀም
    • ለሁሉም ክፍያዎች ያገለግላል
  • አንድ የአሻም ነጥብ = ከ4  ሳንቲም ወይም ከ0.04 ብር ጋር እኩል ነው

አሻም ቴሌን እንዴት እንመዝገብ?

  1. መተግበሪያውን በመክፈት በቀኝ በኩል ከላይ ካለው የማውጫ ዝርዝር ውስጥ አሻም ቴሌ የሚለውን ይምረጡ፡፡
  2. “ለመመዝገብ” የሚለውን ይምረጡ
  3. በመቀጠል “አረጋግጥ” እንዲሁም “ይቀጥሉ” የሚለውን በመጫን ይምረጡ፡፡

  1. *999# በመደወል ለአሻም ቴሌ 3 ቁጥርን ይምረጡ
  2. ለመመዝገብ 1 ቁጥር ያስገቡ

  1. ከአሻም ቴሌ ማውጫ ዝርዝር ውስጥ “ነጥብ ለማስተላለፍ” የሚለውን ይምረጡ
  2. የሚያስተላልፉትን የነጥብ ብዛት ይፃፉ
  3. የሚያስተላልፉበትን ስልክ ቁጥር በማስገባት ይላኩ፡፡

  1. *999# በመደወል ለአሻም ቴሌ 3 ቁጥርን ይምረጡ
  2. ነጥብ ለማስተላለፍ 2 ቁጥርን ያስገቡ
  3. *ስልክ ቁጥር*የነጥቡን መጠን# ፅፈው ይላኩ

  1. ከአሻም ቴሌ ማውጫ ዝርዝር ውስጥ “በነጥብ ለመግዛት” የሚለውን ይምረጡ
  2. የተለያዩ ዕለታዊ፣ ሳምንታዊ እና ወርሃዊ ጥቅል በነጥብዎ ለመግዛት ከፈለጉ “ጥቅል ለመግዛት” የሚለውን ይምረጡ

ወይም

  1. ወደ ደቂቃ፣ ዳታ እና አጭር የፅሁፍ መልዕክት ለመቀየር እንዲሁም ቢል ለመክፈል/የአየር ሰዓት ለመግዛት ከፈለጉ “Multiple Redeem” የሚለውን ይምረጡ፡፡

  1. *999# በመደወል ለአሻም ቴሌ 3 ቁጥርን ይምረጡ
  2. ነጥብ ለመቀየር 3 ቁጥርን ያስገቡ

  • ከአሻም ቴሌ ማውጫ ዝርዝር ውስጥ “የደንበኝነት ደረጃና ነጥብ ለማወቅ” የሚለውን ይምረጡ፡፡

  1. *999# በመደወል ለአሻም ቴሌ 3 ቁጥርን ይምረጡ
  2. # በማስገባት ቀጥሎ 4 ቁጥርን ይምረጡ

  • ከአሻም ቴሌ ማውጫ ዝርዝር ውስጥ “የገዙትን አገልግሎት ቀሪ መጠን ለማወቅ” የሚለውን ይምረጡ፡፡

  1. *999# በመደወል ለአሻም ቴሌ 3 ቁጥርን ይምረጡ
  2. # በማስገባት ቀጥሎ 5 ቁጥርን ይምረጡ

በአሻምቴሌ ነጥቦች ምን ማግኘት ይቻላል?

በአሻምቴሌ መቀየር የሚችሉት የጥቅል መጠን

 የቆይታ ጊዜበአሻምቴሌ ነጥብ መቀየር የሚችሉት 
 ዕለታዊ125 ነጥብ100 ሜ.ባ
 125 ነጥብ25 ደቂቃ
 250 ነጥብ50 ደቂቃ
 625 ነጥብ625 ሜ.ባ
   
 ሣምንታዊ500 ነጥብ110 ደቂቃ
 600 ነጥብ375 ሜ.ባ
 1225 ነጥብ1 ጊ.ባ
   
 ወርሃዊ875 ነጥብ125 ደቂቃ
 1250 ነጥብ1 ጊ.ባ
 2500 ነጥብ2 ጊ.ባ

በአሻምቴሌ መቀየር የሚችሉት የስልክ ቀፎዎች እና ሌሎች መገልገያዎች

የመገልገያ አይነቶች የቀፎ ሞዴል
  የስልክ ቀፎዎች  ባለቁልፍ ስልክ
 አነስተኛ ሞዴል
 መካከለኛ ሞዴል
  ዘመናዊ ሞዴል
  ታብሌት      የተለያየ ሞዴል
  ላፕቶፕ
  ስማርት ሰዓቶች
  የጆሮ ማዳመጫ
  ሌሎችም

ማስታወሻ፡ የአሻምቴሌ ነጥቦችን እንዴት ወደተጠቀሱት ነጥቦች መቀየር እችላሉ

1. ወደሚቀርብዎት የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት መስጫ ማዕከላት በመቅረብ በነጥብዎ ለመቀየር የሚችሏቸውን በሽያጭ ላይ የሚገኙ መገልገያዎች እና የዋጋ መረጃ ይጠይቁ
2. ደንበኞችን የሚፈልጉትን መገልገያ ዋጋ በ0.04 በማካፈል ያላቸው የአሻምቴሌ ነጥብ በቂ እንደሆነ ማወቅ ይችላሉ፡፡
3. ደንበኞች በነጥባቸው ለመቀየር ወይም ማጠራቀማቸውን ለመቀጠል የመወሰን ሙሉ መብት አላቸው፡፡

ማስታወሻ
ለሞባይል ቀፎዎች፣ ታብሌቶች እና ላፕቶፖች የሚያስፈልጉ ነጥቦች እንደገበያው ዋጋ ሊቀያየሩ ይችላሉ።

  • ሁሉም የቅድመ ክፍያ፣ ድህረ ክፍያ እንዲሁም ሀይብሪድ ሞባይል አገልግሎት ተጠቃሚዎች አሻምቴሌ ሎያሊቲ ፕሮግራም ለመጠቀም ብቁ ናቸው፡፡
  • ፕሮግራሙ የሚተገበረው በአገልግሎት ቁጥር እንጂ በአካውንት ቁጥር አይደለም፡፡
  • አሻምቴሌ ለመመዝገብ እና ለማስተዳደር ደንበኞች ማይ ኢትዮቴል የሞባይል መተግበሪያን መጠቀም እንዲሁም ወደ *999# መደወል ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • ደንበኞች የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያላለፈ ነጥቦችን የአሻምቴሌ ፕሮግራም ተጠቃሚ ለሆኑ ደንበኞች ያለምንም ገደብ መላክ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ነጥቦቹ አባል ላልሀነ ደንበኛ መላክ አይቻልም ፡፡
  • አገልግሎት እንዳይሰጥ የታገደ ነጥብ ወደ ሌሎች ማስተላለፍ እና መጠቀም አይቻልም፡፡
  • የሞባይል ቁጥሩ ላይ የባለቤትነት ለውጥ ከተደረገ ነጥቦቹም አብረው ይዛወራሉ፡፡
  • አገልግሎት መስጠት ባቋረጠ የሞባይል ቁጥር የአሻምቴሌ ነጥቦችን መጠቀም አይቻልም፡፡
  • የነጥቦች ከፍተኛው የአገልግሎት ዘመን 12 ወራት ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ደንበኛ 10 ነጥቦች ሚያዚያ 1 ቀን 2014 ዓ.ም ቢኖረው የነጥቦቹ የአገልግሎት ጊዜ ማብቂያ ሚያዚያ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ይሆናል፡፡
  • ከ1 ብር በታች ተጠቅመው ከሆነ በቀጣይ ከሚጠቀሙት አገልግሎት የብር መጠን ጋር ተደምሮ ነጥብ የሚያገኙ ይሆናል፡፡
  • ኢትዮ ቴሌኮም በነፃ ወይም በስጦታ የሚያቀርባቸው አገልግሎቶች ነጥብ ለመሰብሰብ አያስችሉም፡፡
  • 1 የአሻምቴሌ ነጥብ ከ 2 ሣንቲም ጋር እኩል ሲሆን ተ.እ.ታ ያካተተ ነው፡፡
  • ደንበኞች አገልግሎቱን ሲያቋርጡ የሰበሰቡት ነጥብም ይቋረጣል፡፡
  • አሻምቴሌ ከመጀመሩ እንዲሁም ደንበኛው ለአገልግሎቱ ከመመዝገባቸው በፊት የተጠራቀመን ወርሃዊ የአገልግሎት ክፍያ መክፈል ነጥቦችን አያስገኝም፡፡

ነጥብ የሚሰላበት እና ለአገልግሎት ቁጥሮች የሚደርሰው በሚከተሉት መመሪያዎች መሰረት ነው:

  1. ቅድመ ክፍያ ሞባይል:
    • ለድምፅ፣ ለአጭር መልዕክት እና ዳታ 1 ብር ሲጠቀሙ = 1 ነጥብ
    • በየ24 ሰዓታት ያገኙት ነጥብ መረጃ ይላክልዎታል፡፡
    • የጥቅል ተጠቃሚዎች ያልተገደበ ጥቅልን ጨምሮ ነጥብ የሚሰላው ጥቅሉን በገዙበት የብር መጠን ይሆናል (1 ብር = 1 ነጥብ)
    • ጥቅል በስጦታ ሲላክ ላኪው የጥቅሉን ዋጋ ከፋይ እስከሆነ ድረስ ነጥብ ይሰጠዋል፡፡
    • የአየር ሰዓት ወደ ሌላ ሰው ሲተላለፍ ነጥብ የማይያዝ ሲሆን ነገር ግን ተቀባዩ ሲጠቀምበት ነጥብ ይሰበስባል፡፡
    • አጭር/ልዩ ቁጥሮችን ሲጠቀሙ ነጥብ አያገኙም፡፡
    • በቀን ቢያንስ የ2.5 ብር አገልግሎት መጠቀም ይጠበቃል፡፡
  2. ለድህረ ክፍያ ሞባይል፡
    • ወርሃዊ ቢል ሲከፍሉ 1 ነጥብ በ1 ብር ያገኛሉ፡፡
    • ነጥብ ሲሰላ ለአጭር/ልዩ ቁጥሮች የተጠቀሙትን አያካትትም
    • ወርሃዊ የአገልግሎት ክፍያዎ ቢያንስ 75 ብር መሆን ይኖርበታል
    • ወርሃዊ ሂሳቡን የሚከፍለው ሌላ ደንበኛ ከሆነ ነጥቦቹ ወደ ተጠቃሚው ይላካሉ፡፡

 

  1. የአየር ሰዓት በቴሌብር ሲሞሉ
    • 1 ብር ሲሞሉ 2 ነጥብ ያገኛሉ
    • በየ24 ሰዓታት ያገኙት ነጥብ መረጃ ይላክልዎታል፡፡
    • ለሌሎች ደንበኞች አየር ሰዓት ከተሞላ ለገዢው/ከፋዩ ነጥብ ይላካል
  2. ለነጋዴዎች በቴሌብር ከከፈሉ
    • ለነጋዴዎች በቴሌብር 10 ብር ሲከፍሉ 1 ነጥብ ይሰበስባሉ፡፡