የሞባይል የአየር ሰዓት እና ጥቅል ክሬዲት አገልግሎት የሞባይል የአየር ሰዓት ክሬዲት አገልግሎት አገልግሎቱ ለቅድመ ክፍያ የሞባይል ደንበኞች የሞባይል አየር ሰዓትን በማንኛውም ጊዜ እና ቦታ በብድር እንዲያገኙ ያስችላል።የሞባይል ጥቅል ክሬዲት አገልግሎትለቅድመ ክፍያ ሞባይል ደንበኞች የሞባይል ድምጽ ወይም የዳታ ጥቅሎችን በማንኛውም ጊዜ እና ቦታ በብድር እንዲያገኙ ያስችላል። የሞባይል የአየር ሰዓት እና የጥቅል ክሬዲት አገልግሎት የሚጠቀሙባቸው ሁኔታዎች: ያለዎት ቀሪ ሂሳብ ዝቅተኛ በሚሆንበት ጊዜየአየር ሰዓት መሙያ አማራጭ በአቅራቢያዎ በማይገኝበት ጊዜ ወይምየአየር ሰዓት መሙያ ገንዘብ ለጊዜው በማያገኙበት ጊዜ የሞባይል የአየር ሰዓት እና የጥቅል ክሬዲት አገልግሎቱን መጠቀም የሚችሉ ደንበኞች የአገልገሎት ጊዜው ያላለፈ የቅድመ ክፍያ የሞባይል አገልግሎት ደንበኞችየአገልግሎት ቁጥራቸው ያልተቋረጠ ወይም በተለያየ ምክንያት ያልተዘጋበፊት የወሰዱትን የአየር ሰዓት ብድር ሙሉ በሙሉ የከፈሉለሦስት ወራት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በደንበኝነት የቆዩ ደንበኞች እና በወር በትንሹ የ15 ብር የአየር ሰዓት የሚሞሉ የሞባይል ጥቅል ክሬዲት አገልግሎት የዳታ ጥቅል ክሬዲት ዕለታዊ የዳታ ጥቅል ክሬዲት 75 ሜ.ባ በ5 ብር 200 ሜ.ባ. በ12 ብር ሣምንታዊ የዳታ ጥቅል ክሬዲት 600 ሜ.ባ. በ38 ብር 1 ጊ.ባ በ56 ብር ወርሀዊ የዳታ ጥቅል ክሬዲት 1 ጊ.ባ. በ60 ብር 2 ጊ.ባ. በ105 ብር የድምፅ ጥቅል ክሬዲት ዕለታዊ የድምፅ ጥቅል ክሬዲት 20 ደቂቃ የሀገር ውስጥ ጥሪ በ5 ብር 45 ደቂቃ የሀገር ውስጥ ጥሪ በ10 ብር ሣምንታዊ የድምፅ ጥቅል ክሬዲት 70 ደቂቃ የሀገር ውስጥ ጥሪ በ15 ብር 130 ደቂቃ የሀገር ውስጥ ጥሪ በ25 ብር ወርሃዊ የድምፅ ጥቅልክሬዲት 185 ደቂቃ የሀገር ውስጥ ጥሪ በ50 ብር 375 ደቂቃ የሀገር ውስጥ ጥሪ በ95 ብር የሞባይል ጥቅል ክሬዲት አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን የሚያስችሉ ሁኔታዎች በሞባይል አገልግሎት ተጠቃሚነት የቆይታ ጊዜ ያለፉት 3 ወራት የአየር ሰዓት ፍጆታ መጠቀም የሚችሉት የዳታ እና የድምፅ ጥቅል ክሬዲት ዳታ (በሜ.ባ) ድምፅ (በደቂቃ) ቢያንስ 3 ወራት >= 15 75 20 >= 25 75 ወይም 200 20 ወይም 45 >= 60 75፣ 200 ወይም 600 20፣ 45 ወይም 70 >= 100 75፣ 200፣ 600 ወይም 1ጊ.ባ (ሳምንታዊ) 20፣ 45፣ 70 ወይም 130 >= 200 75, 200,600, 1ጊ.ባ (ሳምንታዊ/ወርሃዊ) 20፣ 45፣ 70፣ 130 ወይም 185 >= 400 75,200 ,600 ,1 ጊ.ባ. (ሳምንታዊ/ወርሃዊ) ወይም 2 ጊ.ባ 20፣ 45፣ 70፣ 130፣ 186 ወይም 375 የሞባይል የአየር ሰዓት አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን የሚያስችሉ ሁኔታዎች ተመዝግበው በደንበኝነት የሚጠበቅብዎት ቆይታ ጊዜ በወር መሙላት የሚጠበቅብዎት አማካኝ የገንዘብ መጠን በብር መጠቀም የሚችሉት የድምፅ ጥቅል ክሬዲት ቢያንስ 3 ወራት ≥15 5 ≥25 5፣10 ≥60 5፣10፣15 ≥100 5፣10፣15፣25 ≥200 5፣10፣15፣25፣50 ≥400 5፣10፣15፣25፣50፣100 በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች የአየር ሰዓት ክሬዲት አገልግሎት ምንድን ነው?የአየር ሰዓት ክሬዲት የቅድመ ክፍያ ሞባይል አገልግሎት ተጠቃሚዎች የሞባይል የአየር ሰዓት በማንኛውም ጊዜ እና ቦታ በክሬዲት እንዲሞሉ የሚያስችል አገልግሎት ነው። አገልግሎቱን እንዴት መጠቀም እችላለሁ?አገልግሎቱን ለማግኘት እባክዎ የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙየሚፈልጉትን የሞባይል ጥቅል ክሬዲት አገልግሎት ለማግኘት A ፣ L ፣ ወይም C ብለው ወደ 810 አጭር የጽሑፍ መልዕክት ይላኩ፡፡ ከዚያም የተፈለገውን የሞባይል ጥቅል ክሬዲት ለማግኘት ዝርዝሩን ይከተሉ።በአጭር ቁጥር *810# ላይ ይደውሉ እና የሚፈለገውን የጥቅል ክሬዲት ለማግኘት ቀጥሎ የሚመጣውን ትዕዛዝ ይከተሉ ምን ዓይነት የክሬዲት አገልግሎቶችን ማግኘት እችላለሁ?የአየር ሰዓት እናየጥቅል ክሬዲት አገልግሎቶችን ማግኘት ይችላሉ፡፡ በክሬዲት አገልግሎት ያገኘሁትን የአየር ሰዓት/ጥቅል ለሌሎች ማስተላለፍ እችላለሁ?አዎ፣ የአየር ሰዓት ቀሪ ሂሳብ ብቻ ማስተላለፍ ይችላሉ። የጥቅል ክሬዲት አገልግሎት ምንድን ነው?የጥቅል ክሬዲት አገልግሎት የቅድመ ክፍያ ሞባይል ደንበኞች የሞባይል ድምጽ ወይም የዳታ ጥቅሎችን በማንኛውም ጊዜ እና ቦታ በክሬዲት በቀላሉ እንዲገዙ የሚያስችል አገልግሎት ነው። የአየር ሰዓት/የጥቅል ክሬዲት አገልግሎት ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች ምንድን ናቸው?በኢትዮ ቴሌኮም ኔትዎርክ ላይ ቢያንስ ለሶስት ወራት የቆዩ የቅድመ ክፍያ ሞባይል ደንበኛ መሆን እንዲሁም በወር ቢያንስ የ15 ብር የአየር ሰዓት መሙላት።· አገልግሎቱ ያልተቋረጠ የቅድመ ክፍያ ሞባይል አገልግሎት ደንበኛ መሆንበአገልግሎት ጊዜ ማነስ ምክንያት በተቋረጠ፣ በጥፋተኝነት በተመዘገበ ወይም የአገልግሎት ጊዜው ባለፈ የሞባይል ቁጥር የክሬዲት አገልግሎቱን ማግኘት አይችሉም፡፡ቀደም ሲል የወሰዱትን የክሬዲት መጠን ሙሉ በሙሉ ከፍሎ ማጠናቀቅ አገልግሎቱን ለማግኘት ብቁ መሆኔን እንዴት ማረጋገጥ እችላለሁ?*810# ይደውሉ ወይም በአጭር የጽሑፍ መልዕክት A፣ L፣ C ብለው ወደ 810 ይላኩ።ለእርዳታ ከዝርዝሩ 5 ቁጥርን ይጠቀሙ፡፡· አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ ለማረጋገጥ 1 ቁጥርን ያስገቡ፡፡የማሳወቂያ መልዕክት ይደርስዎታል። ክሬዲቱን እንዴት መክፈል እችላለሁ?በቀጣይ የአየር ሰዓት ሲሞሉ ወይም ከሌሎች ደንበኞች የአየር ሰዓት ሲላክልዎ መክፈል የሚጠበቅብዎ የሂሳብ መጠን እንዲቆረጥ ይደረጋል፡፡ የተሞላው የገንዘብ መጠን የክሬዲት መጠኑን ለመክፈል በቂ ካልሆነ፣ ክሬዲትዎን ሙሉ በሙሉ እስኪሸፈን በቀጣይነት ከሚሞሏቸው ላይ ተጨማሪ መጠን ይቀንሳል። የአየር ሰዓት/የጥቅል ክሬዲት አገልግሎት እንዴት መጠየቅ እችላለሁ?የቴሌብር የሞባይል መተግበሪያ በመጠቀም - የቴሌብር ሞባይል መተግበሪያ ተጠቃሚ ከሆኑ ለአየር ሰዓት/ጥቅል ግዢ የሚውል ከ1 እስከ 250 ብር የሚደርስ የክሬዲት መጠን ማግኘት ይችላሉ። ለበለጠ መረጃ እባክዎን https://www.ethiotelecom.et/telebirr/buy-airtime/ ይጎብኙበአጭር ቁጥር - *810# በመደወል መመሪያዎቹን ይከተሉ ወይምበአጭር የጽሑፍ መልዕክት - A፣ L፣ ወይም C ብለው ወደ 810 የፅሁፍ መልዕክት በመላክ መመሪያዎቹን ይከተሉ የአየር ሰዓት ክሬዲት ወይም የጥቅል ክሬዲት አገልግሎት ክፍያ ስንት ነው?በቀጣይ የአየር ሰዓት ሲሞሉ ወይም ከሦስተኛ ወገን የአየር ሰዓት ሲላክልዎ 10 በመቶ የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላሉ። ያልተከፈለ ቀሪ የክሬዲት መጠንን እንዴት ማወቅ እችላለሁ?በአጭር ቁጥር - *810# ይደውሉ --> ለእርዳታ 5 ቁጥርን ይምረጡ፣ ያለብዎትን የዕዳ ቀሪ ሂሳብ ለማረጋገጥ 2 ቁጥርን ያስገቡ። ወይምበአጭር ጽሑፍ መልዕክት - A፣ L፣ ወይም C ብለው ወደ 810 መልዕክት ይላኩ --> ለእርዳታ 5 ቁጥርን ይምረጡ፣ የዕዳ ቀሪ ሂሳብን ለማረጋገጥ 2 ቁጥርን ይጠቀሙ። ከዚህ ቀደም ያልተከፈለ ክሬዲት እያለብኝ ተጨማሪ ክሬዲት ማግኘት እችላለሁ?አይችሉም፤ በመጀመሪያ የሚጠበቅብዎትን የክሬዲት መጠን ሙሉ በሙሉ ከፍለው ማጠናቀቅ ይጠበቅብዎታል።