የቴሌብር የአዲስ ዓመት ኤክስፖ ማበረታቻ ስጦታ ደንብ እና ሁኔታዎች
- ደንበኞች አዲስ ዓመትን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ውስጥ ከቴሌብር ተመዝጋቢ ነጋዴዎችዕቃዎችን እና የመግቢያ ትኬቶችን በቴሌብር ሲገዙ የ5% ተመላሽ የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ ያገኛሉ።
- ደንበኞች ተመላሽ በሚደረግላቸው 5% ኤሌክትሮኒክ ገንዘብ የአየር ሰዓት እና ጥቅል ለራሳቸው ወይም ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መግዛት ያስችላቸዋል።
- በአንድ ጊዜ እስከ 5,000 ብር ግብይት የሚፈጽም ደንበኛ የ5% ተመላሽ የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ ማበረታቻ ብቁ ይሆናል።
- ነባር ወይም አዲስ የቴሌብር ተመዝጋቢዎች ማበረታቻውን ማግኘት ይችላሉ።
- ደንበኞች የመግቢያ ትኬቶችን ለራሳቸው ወይም ለሌላ ሰው በቴሌብር መተግበሪያ ወይም በቴሌብር አጭር ቁጥር (*127#) መግዛት ይችላሉ፡፡
- ደንበኞች ለግብይት የቴሌብር መተግበሪያን ወይም የቴሌብር አጭር ቁጥርን (*127#) መጠቀም ይችላሉ።
- ኤግዚቢሽኑ እስኪጠናቀቅ ድረስ አንድ ደንበኛ እስከ 500ብር የኤሌክትሮኒክ ተመላሽ ገንዘብ ማግኘት ይችላል፡፡
- ነባር ወይም አዲስ የቴሌብር ተመዝጋቢ ነጋዴዎች ዕቃዎቻቸውን በኤግዚቢሽን ማዕከሉ ውስጥ መሸጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የነጋዴ የመሸጫ ቁጥርን (code) በመጠቀም ከኤግዚቢሽን ማዕከል ውጭ ዕቃዎችን መሸጥ የተከለከለ ነው።
- አንድ ነጋዴ ለሚያከናውነው ግብይት የ0.5% የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ በስጦታ የሚያገኝ ሲሆን፣ ስጦታው የሚታሰበው በቀን እስከ 25,000 ብር ለሚደርስ ሽያጭ ይሆናል፡፡
- ነጋዴዎች የ0.5% ተመላሽ የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ ስጦታ ሲያገኙ የማሳወቂያ አጭር የጽሑፍ መልዕክት የሚደርሳቸው ይሆናል።
- ነጋዴዎች የሚያገኙት ስጦታ በኤግዚቢሽኑ ወቅት በሚሸጧቸው አጠቃላይ ትኬቶች እና ዕቃዎች ቁጥር ይወሰናል፡፡
- ነጋዴዎች የሚያገኙትን ተመላሽ የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ የአየር ሰዓት እና ጥቅል ለራሳቸው ወይም ለሌሎች ለመግዛት ያስችላቸዋል።
- ነጋዴዎች ተመላሽ ገንዘብ ለማግኘት በማሰብ የራሳቸውን ምርት መግዛት የለባቸውም፡፡
- እያንዳንዱ ነጋዴ በኤግዚቢሽኑ ላይ ግብይት እንዲያከናውን በተሰጠው የግብይት መለያ ቁጥር (QR code) ብቻ ማከናወን አለበት።
- ነጋዴዎች ማንኛውንም ግብይት በቴሌብር ቻናል (በቴሌብር መተግበሪያ ወይም በቴሌብር አጭር ቁጥር (*127#) ከደንበኞች ክፍያ መቀበል አለባቸው።