ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ 4ጂ (Home 4G/WTTx) ገመድ አልባ ብሮድባንድ ኢንተርኔት ለመኖሪያ ቤት አገልግሎት አቀረበ፣ የሽያጭ ማዕከላቱን ለደንበኞች ምቹ እንዲሆኑ ማሻሻያ አደረገ::

ዘመኑ የደረሰባቸውን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ለደንበኞቹ በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የሚታወቀው ኩባንያችን በመደበኛ ባለገመድ ኢንተርኔት አገልግሎት ላይ ከፍተኛ የዋጋ ቅናሽ በማድረግ እና ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ስራዎችን በማከናወን የደንበኞቹን ፍላጎት ለማርካት ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም መደበኛ ባለገመድ ኢንተርኔት አገልግሎት ተደራሽ ባልሆነባቸው ቦታዎች ላይ በአማራጭነት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል 4ጂ (Home 4G/WTTx) ገመድ አልባ ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ለመኖሪያ ቤት ያቀረበ ሲሆን ይህ አገልግሎት ደንበኞች በመኖሪያ አካባቢያቸው ወይም በመረጡት ቦታ ተወስኖ 4ጂ ኤል.ቲ.ኢ/ጂ.ኤስ.ኤም የሞባይል ኔትዎርክን በመጠቀም ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የኢንተርኔት አገልግሎት በተመጣጣኝ ዋጋ በቤት ውስጥ ማግኘት የሚያስችል አማራጭ ነው፡፡

አዲሱን 4ጂ (Home 4G) ገመድ አልባ ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት በሙከራ ደረጃ በተወሰኑ የሽያጭ ማዕከሎቻችን ከአገልግሎት መስጫ ቀፎ (Device) ጋር በተመጣጣኝ ዋጋ መስጠት የጀመርን ሲሆን በቅርቡ በስፋት 4ጂ (4G LTE) አገልግሎት በሚገኝባቸው አካባቢዎች መስጠት እንደምንጀምር እንገልጻለን፡፡

ከዚህ ባሻገር ክቡራን ደንበኞቻችን በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በሚገኙ የሽያጭ ማዕከሎቻችን ምቹ እና የተሻለ ተሞክሮ እንዲያገኙ ለማስቻል የደንበኛ ማስተናገጃ እና መጠበቂያ ቦታዎች ምቹ የማድረግ፣ የተለያዩ ቀፎዎችን ከበቂ መረጃ ጋር በአማራጭ ማግኘት የሚችሉባቸውን ማሳያዎች በማመቻቸት፣ ውጫዊ ገጽታቸው በቀላሉ እንዲለዩ እና አመላካች ምልክቶች እንዲኖራቸው የማስቻል እንዲሁም ከአካል ጉዳተኝነት ጋር አብረው ለሚኖሩ ደንበኞቻችን ተደራሽ የማድረግ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

ከዚሁ ጎን ለጎን በአዲስ አበባ በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና በ16 የሪጅን ጽ/ቤት መገኛ ዋና ከተሞች ደንበኞች አገልግሎቶቻችንን ከመግዛታቸው በፊት ተሞክሮ ማግኘት የሚችሉባቸው የሙከራ ቦታዎችን /Experience Zone/ ያካተቱ ፕሪሚየም የሽያጭ ማዕከላትን እንደ አዲስ አደራጅተን አገልግሎት መስጠት መጀመራችንን በደስታ እንገልጻለን፡፡

በተጨማሪም በቀጣይም ሁሉንም የሽያጭ ማዕከሎቻችንን በአዲስ መልኩ የማደራጀቱን ሥራ በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ እና ተደራሽነታችንን በማስፋት ፈጣን አገልግሎት ከምቹ መስተንግዶ ጋር ለክቡራን ደንበኞቻችን የምናቀርብ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ እያረጋገጥን ክቡራን ደንበኞቻችንም በአዲስ መልክ ስራ በጀመሩት የሽያጭ ማዕከሎች በምቾት እንድትስተናገዱና በተመጣጣኝ ዋጋ አዲስ በቀረበው 4ጂ (Home 4G) ገመድ አልባ ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚ እንድትሆኑ በታላቅ ፍቅር እና አክብሮት እንጋብዛለን፡፡

               ኢትዮ ቴሌኮም

       መጋቢት 15 ቀን 2014 ዓ.ም

 

Ethio telecom Launches 4G Home Wireless Broadband Internet Service; It rebrands its Sales Centers for Customer Convenience

Ethio telecom launches a high network capacity 4G Home Wireless Broadband internet service which is a GSM/4GLTE based broadband access solution with affordable price. The 4G home wireless broadband internet service uses the existing GSM/ 4G LTE mobile Network as an option of fixed broadband internet service so as to provide them alternative high speed capacity broadband connection at their preferred areas where wired broadband internet services are inaccessible.

In line with this, the company has launched the 4G Home Wireless Broadband internet service at testing level in some sales centers by supplying 4G Wi-Fi device with affordable price; while it will fully and widely commence the service in the near future in areas where 4G LTE services have already been deployed.

Similarly, Ethio telecom rebrands and restructures its sales centers with high standards so as to deliver best services for the customers in various parts of the country in addition to providing its customers with the latest technologies at affordable prices.

Rebranding & restructuring sales centers of the company have been undertaken across the country, specially by making internal structure improvements and modifying customer hosting and waiting rooms, adjusting newly launched presale service testing places or experience zone; making the sales centers more convenient for the people living with disabilities as well as making the external parts of the building easily identifiable and accessible by the customers so as to bring about best customer experience and enable them get enjoyable serves at a comfortable and attractive environment.

Thereby, premium business centers have been rebranded and commenced providing services for the enterprise customers in six zonal offices of Addis Ababa as well as in 16 cities of the regional offices. On top of this, the company will finalize the rebranding and restructuring of the remaining sales centers within a reasonable time frame to maximize the access of its branded sales centers for the customers so as to provide them with fast and convenient services.

Consequently, our company would sincerely invite its esteemed customers to get served in our newly rebranded and well-furnished sales centers with comfort and purchase the 4G home wireless broadband internet service with affordable price.

               Ethio telecom                                     March 24, 2022 

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives