ኩባንያችን ዘመኑ ያፈራቸውን የቴሌኮም መሠረተ ልማቶች በመገንባት እና ተደራሽ ከማድረግ ባሻገር ተቋማት የሚያስፈልጋቸውን የዲጂታል አገልግሎቶች በማቅረብ አስተማማኝ የቴክኖሎጂ አጋር ለመሆን እና የዲጂታል ኢትዮጵያን ራዕይ ለማሳካት በርካታ ስትራቴጂያዊ ሥራዎችን ተግባራዊ የማድረግ ጉዞውን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ኩባንያችን ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና ሸገር ከተማ አስተዳደር ጋር የአገልግሎት አሰጣጥን የሚያዘምኑ፣ ዓለም የደረሰበትን የቴክኖሎጂ መሰረተ-ልማቶችን እና የዲጂታል ሶሉሽኖችን ለማቅረብ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈራርሟል፡

ኩባንያችን ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጋር በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የዞን፣ የወረዳና የቀበሌ አስተዳደር ቢሮ ሥራዎችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችና የዲጂታል ሶሊሽኖች የታገዙ በማድረግ የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፋናን ለማሳደግ እንዲሁም የተገልጋዮች የአገልግሎት እርካታን ለመጨመር የሚያስችል ስምምነት ፈጽሟል።

ስምምነቱ የኦሮሚያ ክልልን የዲጂታላይዜሽን ራዕይ ለማሳካት የሚያስችሉ ስማርት ቢሮዎችና ካምፓሶችን፣ በተመረጡ ከተሞች የስማርት ትራፊክ መብራቶችን፣ ስማርት የመማሪያ ክፍሎችን እንዲሁም የማዕድን፣ የግብርና፣ የትራንስፖርት፣ የሎጂስቲክስ፣ የጤና፣ የመሬት አስተዳደር እና መሰል ልዩ ልዩ ዘርፎችን ስማርት ለማድረግ የሚያስችል ይሆናል፡፡በተጨማሪም ይህ ስምምነት የክልሉን የተለያዩ የአስተዳደር ቢሮዎችን አሰራር ለማዘመን የሚያስችሉና የዜጎችን የዕለት ተዕለት የኑሮ እንቅስቃሴ የሚያሻሽሉ የዲጂታል መሰረተ ልማቶችን ለመገንባት እና የአገልግሎት ክፍያዎችን ማለትም የመዘጋጃ ቤት የገቢ ግብር፣ የኪራይ የገቢ ግብር፣ የኢንቨስትመንት የገቢ ግብር እና የመሳሰሉ የአገልግሎት ክፍያዎችን በቀላሉ በቴሌብር ለመፈጸም ያስችላል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ ኩባንያችን ከሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ጋር የተለያዩ ቢሮዎች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን በቀላሉ ለማስተሳሰር የሚያስችል የዋይድ ኤሪያ ኔትዎርክ (WAN-Wide Area network infrastructure) የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎችን ለማከናወን የሚያስችል የውል ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን፣ ስምምነቱ የሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ስራዎችን ለመከታተል የሚያስችል የሲሲቲቪ (CCTV) ካሜራ የመሰረተ ልማት ግንባታ የታገዙ በማድረግ የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፋናን ለማሳደግ እንዲሁም የተገልጋዮች የአገልግሎት እርካታን ለመጨመር የሚያስችል የዲጂታል ሶሉሽኖች አቅርቦት እና መሰል የቴክኒክ ድጋፎችን የሚያካትት ይሆናል፡፡

ኩባንያችን ከዚህ ቀደም የኦሮሚያ ገቢዎቸ ቢሮ የግብር አሰባሰብ ሂደትን በቴሌብር በቀላሉ እንዲሰበሰብ በማድረግ ክልሉ ገቢውን በወቅቱ እንዲሰበስብ ከማስቻሉ በተጨማሪ ግብር ከፋዩ ህብረተሰብ ጊዜ እና ወጭ በማዳን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ይታወቃል።

ኩባንያችን የኢትዮጵያን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እውን ለማድረግ ባለው ጽኑ ፍላጎትና ቁርጠኝነት የአገልግሎት አሰጣጥን በማዘመንና ዘልማዳዊ አሰራሮች ላይ ሥርነቀል ለውጥ እንዲመጣ በማድረግ፣ ለማህበረሰባችን የዕለት ተዕለት የኑሮ እንቅስቃሴ መሻሻል፣ የቢዝነስ አጋሮቻችን የአሰራር ሥርዓት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዲታገዝ በማድረግ ምርታማነታቸውን ለመጨመር እንዲሁም ሁሉም ደንበኞቻችን ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ እያከናወናቸው ያሉ ሥራዎችን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

 

ህዳር 28 ቀን 2016 ዓ.ም

ኢትዮ ቴሌኮም

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives