ፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ

ፋይዳ(ብሔራዊ መታወቂያ)

ዲጂታል መታወቂያ ለአካታች ዲጂታል ኢኮኖሚ!

የዲጂታል መታወቂያ ዓይነት ሲሆን የነዋሪዎችን የባዮሜትሪክ (የጣት አሻራ፣ የአይን አይሪስ እና የፊት ምስል) እንዲሁም የግል መረጃዎችን በመሰብሰብ አንድን ግለሰብ ልዩ በሆነ መልኩ እንዲታወቅ የሚያስችል ነው፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም መሪ የዲጂታል ሶሉሽን አቅራቢ ድርጅት በመሆኑ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ራዕይ በአጋርነት ለማሳካት እና ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን የማድረግ ራዕይ ለማፋጠን በዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ፣ በመታወቂያ ህትመትና ስርጭት፡ ማንነትን በማረጋገጥ (Authentication) ስራዎች ላይ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡

ፋይዳ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን የግለሰቦች፣ የንግዱን ዘርፍ እና የዜጎችን ችግሮች በቋሚነት ይቀርፋል፡፡

ለግለሰቦች

  • ማንነታቸውን በህጋዊ መንገድ ያላረጋገጡ ግለሰቦች መሰረታዊ የዜግነት መብቶቻቸውን አለማግኘት
  • የዜጎችን ፍላጎት ያላገናዘበ አገልግሎት አሰጣጥ
  • የተገልጋዮች ግላዊ መረጃዎች በአግባቡ ስለማያዙ ዜጎች ለዝርፍያና ለሌሎች አደጋዎች ተጋላጭ መሆን
  • ማንነትን ለማረጋገጥ ሰነዶችን ማገላበጥ የሚጠይቅ በመሆኑ የተጓተተ የአገልግሎት አሰጣጥ መኖር

ለነጋዴዎች

  • የተቋማት በተንዛዛ ሂደት ቅልጥፍና የጎደለው አገልግሎት አሰጣጥ መኖር
  • የተለያዩ የንግድ ጥናቶች በመረጃ እጥረት ምክንያት ትክክለኛውን የወደፊት አደጋ በመተንበይ የቅድመ መከላከል ስራ ለመስራት መቸገር
  • አገልግሎት ተጠቃሚዎች የተሳሳተ የማንነት መረጃ ይዘው ሲመጡ ለማጣራት መቸገር እና በዚህም ምክንያት የተቋማት መጭበርበር መበርከት
  • የማንነት ማረጋገጫዎች የመገልገያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መሆን አለመሆኑን ለማጣራት ሰነድ ማገላበጥ የሚጠይቅ መሆን የሰው ሀይል እና የጊዜ ብክነት መኖር

ለዜጎች

  • ማንነትን ማረጋገጥ አስቸጋሪ በመሆኑ ዜጎች ከማህበራዊ ተቋማት ማግኘት የሚገባቸውን አገልግሎቶች ለማግኘት መቸገር
  • በመረጃ እጥረት ምክንያት ያልተገባ የአገልግሎት አሰጣጥ መኖር
  • አጭበርባሪዎች ሀሰተኛ የማንነት መረጃዎችን በማዘጋጀት ለትክክለኛ ዜጎች መሰጠት የነበረበትን አገልግሎት ለራስ ጥቅም ማዋል
  • አብዛኛው የወቀረት ሂደትን የሚከተሉ አሰራሮች ከፍተኛ የሆነ የሰው ሀይል እንዲሁም ማስተካከያዎችን መፈለግ

እነዚህንና መሰል ችግሮች በፋይዳ ይቀረፋሉ!

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ህጋዊ ነዋሪ በሙሉ ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ብቁ ነው። በመተዳደሪያ አዋጁ መሰረት በህጋዊ መልኩ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር፣ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው ወይም የሌለው የተፈጥሮ ሰው እንዲሁም በሀገሪቱ ህግ መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ወይም የሚሰራ የውጭ ሀገር ዜጋ ይካተታሉ፡፡

  • ዕድሜያቸው ከ 5 ዓመት በላይ የሆኑ ልጆች መመዝገብ ይችላሉ
  • ከ 5 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት, በቅርቡ ልዩ የምዝገባ ፕሮግራም የሚጀመር ይሆናል
  • ኢትዮጵያዊ እና ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ የነዋሪነት ማረጋገጫ ያላቸው
  • የመኖሪያ አድራሻ ማረጋገጫ ሰነድ ያላቸውም ሆነ የሌላቸው
  • ኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪነታቸው “በአዋጁ መሰረት” የተሰጠ
  • የት እንደሚኖሩ ምንም ዓይነት ሰነድ የሌላቸው ሰዎች የዲጂታል መታወቂያ ያለው ሰው እንደ ምስክር ይዞ በመቅረብ መመዝገብ ይችላሉ።

 

·       የቀበሌ መታወቂያ

·       ፓስፖርት

·       የልደት ሰርተፊኬት

·       የትምህርት ማስረጃ

·       የንግድ ምዝገባ ወይም የንግድ ፈቃድ ሰርተፊኬት

·       የጋብቻ ሰርተፊኬት

·       መንጃ ፈቃድ

·       የባንክ አካውንት ደብተር

·       የመኪና ሊብሬ

·       የቤት ካርታ

·       የሙያ ፈቃድ ማስረጃ

·       የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር/ መታወቂያ (ፎቶ ያለው)

·       የምርጫ ካርድ/መታወቂያ (የተመራጭነት/የመራጭነት ማስረጃ/መታወቂያ)

·       የጤና መድህን መታወቂያ

·       የጡረታ መታወቂያ

·       የሥራ ፈላጊ መታወቂያ

·       የተማሪነት መታወቂያ

·       ዕድር ደብተር

·       የእቁብ ደብተር

·       የህፃናት ማሳደጊያ ተቋማት የሚሰጡ በፎቶ የተደገፈ ደብዳቤ

·       የዲፕሎማት መታወቂያ(ኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ መሆኑን የሚያመለክት)

·       የዲያስፖራ ነዋሪነት ማረጋገጫ /Yellow card/ ( ኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ የሆነ)

·       የስደተኛ ካርድ ወይም ከስደትና ስደት ተመላሽ አገልግሎት የሚሰጠው ማስረጃ

·       የሥራ ፈቃድ መታወቂያ ( ለውጭ ሃገር ዜጎች)

·       የአለም አቀፍ ተቋማት የሰራተኛ መታወቂያ

·       በማንኛውም የመንግሥት አካል የሚሰጥ መታወቂያ

·       የቀበሌ ስራ አስኪያጅ የሚሰጠው ማረጋገጫ

·       ፈቃድ ያላቸው ማንኛውም የፋይናንስ ተቋማት የሚሰጥ የማንነት ማስረጃ

·       የነዋሪነት ፍቃድ (ለውጭ ሀገር ዜጎች)

ማስታወሻ

·       ሁሉም ዓይነት ተቀባይነት ያላቸው ሰነዶች የግለሰቡን ፎቶ ማካተት አለባቸው

·       የሰነድ ማስረጃ ከሌለዎ የፋይዳ መታወቂያ ስርዓት ውስጥ የተመዘገበ የሰው ምስክር ማቅረብ ይችላሉ፡፡

በመላ ሀገሪቱ የኢትዮ ቴሌኮም    
የተመረጡ አገልግሎት መስጫ ማዕከሎች   
በነፃ ይችላሉ!
   
አጋር ድርጅቶች   
   
ተንቀሳቃሽ የምዝገባ ጣቢያዎች   

በምዝገባ ወቅት የምዝገባ ባለሞያዎች የባዮሜትሪክ መረጃን (10 የጣት አሻራ፣ የ2 አይን አይሪስ እና የፊት ምስል) እና በቅድመ-ምዝገባ ወቅት የተሞሉ ተቀባይነት ያላቸውን ሰነዶችን ይሰበስባሉ።

ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባዎን ካጠናቀቁ በኋላ በምዝገባ ወቅት በሰጡት ሞባይል ቁጥርዎ National ID በሚል ባለ 12 አሃዝ የፋይዳ ልዩ ቁጥር በፅሁፍ መልዕክት የሚላክልዎ ሲሆን ቁጥሩን ቴሌብር ሱፐርአፕን ላይ ከገቡ በኋላ “መተግበሪያዎች’’ የሚለውን በመጫን የብሔራዊ መታወቂያ ሚኒ አፕን በመምረጥ ቁጥሩን በማስገባት ለህትመት ዝግጁ የሆነ (softcopy) መታወቂያዎን ማግኘት ይችላሉ፡፡

  • If you did not receive your Fayda ID via SMS
  • If you lost your Fayda number
  • If you did not get your Fayda digital ID on telebirr superApp fayda mini app

Click Here https://id.et/help

Or dial 9779

0
በሃገር አቀፍ ደረጃ ለመመዝገብ የታቀደ
0
እስከ 2018 ዓ.ም በተቋማችን ለመመዝገብ የታቀደ
0
በወር በአማካይ የሚደረግ ምዝገባ

  1. ፋይዳዲጂታል መታወቂያ ምንነው? ጠቀሜታውስ?

ፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ግለሰቦች ማንነታቸውን እንዲያረጋግጡ የሚያስችል እና ለአገልግሎት አቅራቢዎች ታማኝ የዲጂታል ማረጋገጫ በዚያው ቅጽበት የሚሰጥ መታወቂያ ስርዓት ነው ።

ጠቀሚታውም;

  • መሰረታዊ “የመታወቅ መብትን” የሚሰጥ ትክክለኛ እና ህጋዊ የማንነት ማረጋገጫ ነው።
  • በሁሉም አካባቢዎች የተለያዩ የገቢ ደረጃ ላይ ላሉ እና የከተማ መስፋፋት ውስጥ ለሚካተቱ ማህበረሰቦች፣ ፍትሃዊ ተደራሽነት እንዲኖር የሚያስችል የመታወቂያ ስርአት ነው።
  • በባዮሜትሪክ ላይ የተመሰረተ መለያ ሲኖር የአንድ ሰው ካርድ ወይም የምስክር ወረቀት መጥፋት ማለት የማንነት ማጣት ማለት አይደለም
  • በአገልግሎት ሰጪ እና በተጠቃሚው መካከል ለሚደረጉ ግብይቶች ተአማኒነትን ይጨምራል ፣ ይህም ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል
  • በሁሉም የሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖሊሲዎች ተጠያቂነትን እና ግልፅነትን ያበረታታል።
  1. ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ብቁ የሆነው ማነው?

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ህጋዊ ነዋሪ በሙሉ ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ብቁ ነው። በ "ረቂቅ አዋጁ" ነዋሪ የሚገለፀው “በህጋዊ መልኩ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ፣ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው ወይም የሌለው የተፈጥሮ ሰው እንዲሁም በሀገሪቱ ህግ መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ወይም የሚሰራ የውጭ ሀገር ዜጋ ነው።” ይህም የሚያካትተው ፡-

  1. ዕድሜያቸው ከ 5 ዓመት በላይ የሆኑ ልጆች መመዝገብ ይችላሉ። ከ 5 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት, በቅርቡ ልዩ የምዝገባ ፕሮግራም የምንጀምር ይሆናል።
  2. ኢትዮጵያዊ እና ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ የነዋሪነት ማረጋገጫ ያላቸው
  3. የመኖሪያ አድራሻ ማረጋገጫ ሰነድ ያላቸውም ሆነ የሌላቸው ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪነታቸው “በአዋጁ መሰረት” የተሰጠ።
  4. የት እንደሚኖሩ ምንም ዓይነት ሰነድ የሌላቸው ሰዎች ፣ የዲጂታል መታወቂያ ያለው ሰው እንደ ምስክር ይዞ በመቅረብ መመዝገብ ይችላሉ።
  5. ማንኛውም ለምዝገባ ብቁ የሆነ ሰው id.et/proof ላይ በተጠቀሰው መሰረት ተቀባይነት ያለው የማንነት ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርበታል።
  6. ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የት መመዝገብ እችላለሁ?

ለአገልግሎቱ ብቁ የሆኑ ዜጎች የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት መስጫ ማዕከሎችን እንዲሁም ምዝገባ እንዲያደርጉ ፈቃድ ያላቸው አጋሮች ጋር መመዝገብ ይችላሉ፡፡ የባዮሜትሪክ መረጃ መስጠት ስለሚጠበቅብዎ ለአገልግሎቱ በአካል መቅረብ ይጠበቅብዎታል፡፡

  1. የፋይዳ መታወቂያን ለማግኘት ምን ያክል መክፈል ይኖርብኛል?

ለዲጂታል መታወቂያ በነፃ መመዝገብ ይችላሉ፡፡ የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ አዋጅ መሰረት በስኬት መመዝገብዎን የሚገልፅ “የፋይዳ መለያ ቁጥር” በፅሁፍ መልዕክት የሚደርስዎ ይሆናል፡፡ ይህም ማለት የተረጋገጠ “የፋይዳ መለያ“ አለዎት ማለት ነው፡፡ ነገር ግን የታተመ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ከፈለጉ የህትመት የሚከፍሉ ይሆናል፡፡

  1. ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለመመዝገብ ምን ያክል ጊዜ ይፈጅብኛል?

ሁሉም መረጃዎች በተሟሉበት ሁኔታ ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለመመዝገብ በአማካኝ ከ5 እስከ 10 ደቂቃ ይፈጃል።

  1. የፋይዳ መለያ ቁጥር ለማግኘት ምን ያክል ጊዜ ይፈጃል?

በተሳካ ሁኔታ ምዝገባዎን ከአጠናቀቁ በኋላ መረጃዎን የማረጋገጡ ሂደት ጥቂት ደቂቃዎች አልያም የተወሰኑ ቀናት ሊወስድ ይችላል፡፡ ልዩ የፋይዳ መለያ ቁጥርዎ በምዝገባ ወቅት ባስመዘገቡት የሞባይል ቁጥር ቁጥር የሚላክልዎ ይሆናል፡፡ ያስመዘገቡት ቁጥር ሊቀየር የማይችል ብቸኛ እርስዎ የሚገኙበት አድራሻ በመሆኑ ሲያስመዘግቡ ጥንቃቄ ያድርጉ፡፡

መረጃዎን ሲስተም ውስጥ ለማስገባት እና ለማረጋገጥ በእጅ (manually) ከሆነ ጥቂት ቀናት የሚወስድ ሲሆን መዘግየት ቢኖርም ነገር ግን ማረጋገጫ ቁጥርዎን በ9779 ወይም National ID Ethiopia በሚል የፅሁፍ መልዕክት የሚላክልዎ ይሆናል፡፡

  1. ከምዝገባ በኋላ መረጃዬን ማስተካከል እችላለሁ?

ደንበኞች የግል መረጃቸውን በማንኛውም ጊዜ ያረጋግጡልኛል ያሏቸውን ሰነዶች በኦንላይን ወይም በአካል በማስገባት ማስተካከል ይችላሉ፡፡ ይህ አገልግሎት ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የሚጀምር ሲሆን በአሁኑ ጊዜ መረጃ ማደስ አይቻልም።

 

  1. ለምዝገባ የሚያስፈልጉ የሰነድ ማስረጃዎች ምን ምን ናቸው?

አሁን ላይ የሚኖሩበት ትክክለኛ አድራሻ እና የማንነት ማረጋገጫ ያስፈልጋል። እንደ፦

  • የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፈቃድ እንዲሁም ሌሎች ህጋዊ ተቀባይነት ያላቸው የግለሰቡ መለያዎች በማስረጃነት መቅረብ ይችላሉ፡፡ ለተጨማሪ ዝርዝር gov.et/proof ይሄን ይጫኑ
  • አንድ ግለሰብ ለመመዝገብ ትክክለኛ ሰነድ ማቅረብ ካልቻለ ዲጂታል መታወቂያ ያለው ሰው ምስክር አምጥቶ መመዝገብ ይችላል።
  1. የፋይዳ መለያ ቁጥር ከጠፋብኝ/ከረሳሁት እንዴት መልሼ ማግኘት እችላለሁ?

የፋይዳ መለያ ቁጥርዎን መልሶ ለማግኘት በምዝገባ ወቅት የሞሉትን ግላዊ ወይም የባዮሜትሪክ መረጃዎን በማቅረብ እንዲሁም አቅራቢያዎ የሚገኝ የምዝገባ ጣቢያ በመጎብኘ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ይህን በማድረግ የፋይዳ መለያ ቁጥርዎን በቀላሉ በፅሁፍ መልዕክት ወይም ከምዝገባ ጣቢያዎች ማግኘት ይችላሉ፡፡

ይህ አገልግሎት በቅርቡ የሚጀምር ሲሆን የምናሳውቅዎ ይሆናል፡፡

  1. ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ መመዝገብ ግዴታ ነው?

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ መብት እንጂ ግዴታ አይደለም። ሆኖም የዲጂታል መታወቂያ አዋጁ እንደሚለው፡- “ማንኛውም አካል አገልግሎትን ለማቅረብ ዲጂታል መታወቂያን የግዴታ መስፈርት አድርጎ የማቅረብ ህጋዊ መብቱ የተጠበቀ ነው።

  1. የውጭ ሀገር ዜጎች ዲጂታል መታወቂያ ማግኘት ይችላሉ?

አዎ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ በህጋዊ መንገድ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎች የነዋሪነት መታወቂያቸውን፣ ፓስፖርት ወይም ሌሎች ተዛማጅ ሰነዶችን በመጠቀም ዲጂታል መታወቂያ ማግኘት ይችላሉ።

  1. የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያዬ የመጠቀሚያ ጊዜው ሊያልፍ ይችላል?

የዲጂታል መታወቂያ ለአንድ ግለሰብ ልዩ የሆነ የህይወት ዘመን ቁጥር ነው። ሆኖም ግን የካርዱ እና የባዮሜትሪክ መረጃ በተወሰነ ጊዜ መታደስ አለበት። አሁን ላይ የካርድ እና የባዮሜትሪክ መረጃ በየ10 አመቱ የሚታደስ ይሆናል።

 

 

 

  1. በክልል ደረጃ ምዝገባ የምትጀምሩት መቼ ነው?

በቀጣይ አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በሁሉም የክልል ዋና እና በተመረጡ ከተሞች የሚጀመር ይሆናል፡፡ የፈረንጆቹ 2025 ከመጠናቀቁ በፊት 90 ሚሊዮን የተለያዩ የገቢ ደረጃ ላይ ላሉ እና የከተማ መስፋፋት ውስጥ ለሚካተቱ ማህበረሰቦች ለመመዝገብ ታቅዷል፡፡

  1. የታተመ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያዬን እንዴት ማግኘት እችላለሁ?

በብሔራዊ መታወቂያ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ዲጂታል መታወቂያ የሚባለው ለግለሰቡ የሚሰጠው ልዩ መለያ ቁጥር ሲሆን ይህ ቁጥር ምዝገባዎን ካጠናቀቁ በሰዓታት ወይም ከጥቂት ቀናት በኋላ በነፃ በሞባይል ቁጥርዎ የሚላክልዎ ይሆናል፡፡ የዲጂታል መታወቂያ በሚጠየቁበት ጊዜ ይህን ልዩ ቁጥር በመስጠት ማንኛውንም አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡

በቅርቡ የዲጂታል መታወቂያ ህትመት አገልግሎት በመጀመር የምናሳውቅዎ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ለህትመት ዝግጁ የሆነውን መታወቂያዎን በቴሌብር ሱፐርአፕ ላይ መለያ ቁጥርዎን ተጠቅመው ማግኘት ይችላሉ፡፡

  1. የቀበሌ የነዋሪነት መታወቂያ በፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ይተካል? ያላቸው ግንኙነትስ ምንድነው?

አይተካም፤ የከተማ እና የክልል የመንግስት ነዋሪ መታወቂያ ካርድ የሚሰጡት በአካባቢ አስተዳደር ነው። ነገር ግን “ፋይዳ” ዲጂታል መታወቂያ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጥ ነው። ሁለቱም “ቀበሌ” እና “ፋይዳ” እጅ ለእጅ ተያይዘው እንዲሰሩ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው። ዲጂታል መታወቂያ ማንነትን የሚያረጋግጥ መሠረታዊ መታወቂያ ሲሆን የቀበሌ መታወቂያ ግን ተግባራዊ መታወቂያ (አገልግሎት ለማግኘት የሚጠቅም) ነው። ዲጂታል መታወቂያ የመኖሪያ አካባቢ ገደብ ሳይደረግበት በሀገሪቱ ውስጥ በየትኛውም ቦታ በተፈቀደ አካል ሊሰጥ የሚችል የአንድ ሰው ልዩ መለያ ነው። በአንፃሩ የቀበሌ መታወቂያ ሊሰጥ የሚችለው በሚኖርበት ቀበሌ ብቻ ነው።

Zonal   SCs Selected for NID Phase 1
Region SCs Level Latitude Longtude
CER Harar 2 Medium 9.3116864 42.1270368
CNR Debre Birhan Premium 9.6786142 39.5328828
CNR Fitche Higher 9.7809652 38.7374429
CNR Legtafo Medium 9.0717716 38.8945111
CWR Ambo Premium 8.9822737 37.8635621
CWR Sebeta Higher 8.9114933 38.6229166
EER Jigjiga 1 Premium 9.350944 42.8122418
ER Dire Dawa1 Premium 9.6051208 41.8562975
NEER Semera Premium 11.7919933 41.0102049
NER Dessie Premium 11.118136 39.633081
NER Kombolcha Grand 11.086118 39.7378722
NNWR Gondar 1 Premium 12.6120°N 37.4698° E
NNWR Azezo Medium 12°33'23.9"N 37°25'46.9"E
NR Mekele - 1 Premium 13.488151 39.470106
NR Mekelle -2 Higher 13.497 39.4766
NWR Bahir Dar 1 Premium 11.5999372 37.371938
NWR Abay-Mado Medium 11.60045 37.42676
SER Adama bole Premium 8.5528881 39.2780336
SER Bishoftu 1 Grand 8.7486799 38.9822811
SR Hawassa 1 Premium 7.0477474 38.4882418
SR Hawassa 2 Grand 7.0524472 38.4710576
SR Shashemene Grand 7.1898968 38.5879825
SSWR Wolayta Sodo Premium 6.8502888 37.7632836
SSWR Hossana Higher 7.551939 37.852639
SSWR Welekite Higher 8.291126 37.781985
SWR Jimma 1 Premium 7.6756709 36.8290054
SWR Bonga Medium 7.2658264 36.2449373
SWR Mizan Medium 6.9987729 35.5874085
SWWR Gambella Premium 8.2522527 34.5891079
WR Nekemte Premium 9.0887599 36.5508229
WWR Assosa Premium 10.0628836 34.537877
CAAZ Weha Lemat Premium 9.0142285 38.7811299
CAAZ Lideta Higher 9.011317 38.734482
CAAZ Stadium Higher 9.0119302 38.7544027
EAAZ Bole Medanialem Premium 8.9949221 38.7901214
EAAZ Gerje Grand 8.9948106 38.8135386
EAAZ Ayat/CMC Higher 9.0116 38.85489
NAAZ 6 killo Premium 9.0417156 38.7668494
NAAZ Gurdshola Grand 9.019497 38.8195842
NAAZ Shiro Meda Medium 9.0609024 38.7608034
SAAZ Saris Premium 8.952933 38.7630228
SAAZ Kaliti Higher 8.901103 38.768566
SAAZ Akaki 2 Medium 8.8625291 38.7934422
SWAAZ Jemo Grand 8.9609837 38.7145912
SWAAZ Lebu Premium 8.9488507 38.7286999
SWAAZ Betel Medium 9.0016284 38.6915788
WAAZ Arada Premium 9.0392374 38.751876
WAAZ Kolfe Grand 9.0398205 38.71353
WAAZ Burayou Higher 9.07629 38.67579
TPO TPO Premium 9.024834 38.751978