ኩባንያችን ከኮኔክቲቪቲ አገልግሎት ባሻገር (beyond connectivity) የፋይናንስ አካታችነትን በማረጋገጥ እና የዲጂታል አገልግሎቶችን በስፋት ተደራሽ በማድረግ የዲጂታል ኢትዮጵያን ራዕይ ለማሳካት በርካታ ሥራዎችን የመከወኑን ጉዞ አጠናክሮ እየቀጠለ የሚገኝ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለትም ከአዲስ አበባ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጋር ስማርት የእሳትና አደጋ ስጋት አመራር ፕሮጀክትን እውን ለማድረግ የሚያስችል የሶሉሽን ትግበራ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ይህ በኢትዮ ቴሌኮም እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የሚደረገው ስትራቴጂያዊ ስምምነት የአደጋ ጊዜ ድጋፍ አሠጣጥን በማዘመን የአደጋ መረጃ አሰጣጥ ፈጣን እንዲሆን፣ በተለያዩ ቦታ የሚገኙ ቅርንጫፎች ከዋናው ማዕከል ጋር ፈጣን ግንኙነት እንዲኖራቸው ለማድረግ፣ የምላሽ ጊዜን በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ፣ የመረጃ አሰባሰብ እና ግብረመልስ አሰጣጥ አቅምን ለማሳደግ፣ በተለያዩ የግንኙነት ዘዴዎች ድጋፍ ለመስጠት፣ ወጭና ቆጣቢ አሰራር ለመተግበር እና የርቀት የአደጋ ጊዜ ድጋፍ እውን ለማድረግ ከማስቻሉ በተጨማሪ  በአጠቃላይ የአደጋ ጊዜ የአሠራር ሂደትን በማዘመን፣ ውጤታማና ቀልጣፋ የአደጋ ጊዜ ምላሽ በመስጠትና ጉዳቶችን በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ የሚያስችሉ እንዲሁም እንደአስፈላጊነቱ አቅሙን ማሳደግ እንዲሁም አዳዲስ የቴክኖሎጂ ገጽታዎችን በማካተት አዳዲስ የቴክኖሎጂ አገልግሎቶችን ለማቅረብ ያስችላል፡፡

ስምምነቱ በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የቴክኖሎጂ አተገባበር ተግዳሮቶችን ለመፍታት እና የተቀናጀ የግንኙነት ሥርዓት በመተግበር፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ዲስፓች (CAD)፣ አካባቢያዊ የመረጃ ስርዓት (GIS) እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ ቴክኖሎጂዎችን ስራ ላይ በማዋል ውጤታማ የአደጋ ጊዜ ስራ አመራርን ለመደገፍ፣ የመስክ ምላሽ ሰጪ ተሽከርካሪዎችን በአካባቢያዊ መልኩ ለማቀናጀት፣ የመስክ የድንገተኛ አደጋ ምላሽ ሰራተኞች ስልኮችን ከሞባይል CAD መተግበሪያ ጋር እንዲናበቡ በማድረግ በማንኛውም ጊዜ ከድንገተኛ አደጋ ጋር የተያያዙ ተግባራትን ለማቀላጠፍ ያስችላል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም በስምምነቱ መሰረት የተሟላ የአደጋ ጊዜ የጥሪ ማዕከል (contact center) አገልግሎት እና የአደጋ ጊዜ መገናኛ ማዕከልን እውን በማድረግ እና በመምራት አገልግሎቱን በጥራትና በቅልጥፍና ለማቅረብ የሚያስችል  ሲሆን፣ ለዚህ የሲስተም ኦፕሬሽን ተግባራዊነት እና 24/7 የሙሉ ጊዜ አገልግሎት አቅርቦት መረጋገጥ ብቁ ባለሙያዎችን በመመደብ ድጋፍ ያደርጋል፡፡በተጨማሪም የድንገተኛ አደጋ አስተዳደር አገልግሎትን ለማዘመን ሁሉን አቀፍ የድንገተኛ አደጋ ጊዜ አገልግሎቶች የመገናኛ/የኮንታክት ማዕከል ሶሉሽን ለማቅረብ የክለውድ አገልግሎት እና አቅርቦት፣ የተከላ፣ የሙከራ፣ የስልጠና እና ቀጣይነት ያለው የድህረ ትግበራ ድጋፍ ያደርጋል። ኩባንያችን ከጥቂት ወራት በፊት የአዲስ አበባ ስማርት ሲቲ ፕሮጀክትን ጨምሮ በበርካታ መስኮች ለመሰል ተቋማት የቴክኖሎጂ እና ዲጂታል ሶሉሽኖችን በማቅረብ እና የአገልግሎት አሰጣጣቸውን በማዘመን ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ለማህበረሰባችን የዕለት ከዕለት የኑሮ እንቅስቃሴ መሻሻል፣ ለቢዝነስ አጋሮቻችን ጥራት፣ ቅልጥፍና እና ዘመናዊ የአሰራር ሥርዓት በቴክሎጂ የታገዘ ለማድረግ እንዲሁም አጠቃላይ ለዜጎች ሕይወትና ደህንነት ጉልህ ድርሻ ያላቸውን ቴክኖሎጂዎችና የአሰራር ሥርዓቶች መዘርጋት ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረጉን አጠናክሮ ይቀጥላል።

ኢትዮ ቴሌኮም

መስከረም 15 ቀን 2016 ዓ.ም

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives