ኩባንያችን በቅርቡ የተለያዩ መተግበሪያዎችን በአንድ አካቶ የያዘ እና ደንበኞች አንድ መተግበሪያ ላይ ሆነው የተለያዩ የዲጂታል ግብይቶችን መፈጸም እና የፋይናንስ አገልግሎት ማግኘት ወደሚችሉበትና “በአንድ መተግበሪያ እልፍ ጉዳይ” ወደሚያከናውኑበት ቴሌብር ሱፐርአፕ  መተግበሪያ ማሳደጉ ይታወቃል፡፡  

ይህም የቴሌብር ተጠቃሚ የሆኑ ደንበኞቻችን ፈርጀብዙ የዲጂታል ግብይቶችን በቀላሉ እንዲፈጽሙ እና የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ በማስቻል ተሞክሮአቸውን ይበልጥ ያላቀ ሲሆን አገልግሎታቸውን በቴክኖሎጂ ታግዘው ለደንበኞቻቸው ለማድረስ የሚሰሩ የቢዝነስ ተቋማትን በማዘመን እና ሥራቸውን በማቀላጠፍ ትልቅ ሚና በማበርከት ላይ ይገኛል፡፡

ኩባንያችን የቴሌብር ሱፐርአፕ መተግበሪያን ይበልጥ አስተማማኝ የሚያደርጉ ተጨማሪ የደህንነት (security) ማሻሻያዎች ተግባራዊ ያደረገ ሲሆን ይህም አገልግሎቱ ሁልጊዜ አስተማማኝ እና ዘመናዊ ሆኖ እንዲቀጥል ለማድረግ የሚያስችል ነው፡፡

በዚህም መሠረት፡-

  • ደንበኞች የቴሌብር ሱፐርአፕ አገልግሎት ማግኘት የሚችሉት ቴሌብር በተመዘገቡበት ሲም ካርድ ብቻ ማለትም ሲም ካርዱን በያዘው የሞባይል ስልክ ብቻ እንዲሆን ተደርጓል፡፡
  • ደንበኞች ወደ ቴሌብር ሱፐርአፕ መተግበሪያ ለመግባት (login ለማድረግ) የሞባይል ስልካቸውን ዳታ መክፈት እንዲሁም ወደመተግበሪያው ውስጥ ከገቡ (login ካደረጉ) በኋላ እንደፍላጎቸው ወደ ዋይፋይ ኢንተርኔት በመቀየር አገልግሎቱን ከዳታ ክፍያ ነጻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
  • እንዲሁም ደንበኞች በዘመነው የቴሌብር ሱፐርአፕ መተግበሪያ ሲጠቀሙ እንደፍላጎታቸው ቲፕ (ጉርሻ) መስጠት ይችላሉ፡፡

በመሆኑም የቴሌብር ሱፐርአፕ ተጠቃሚ ደንበኞቻችን የደህንነት ማሻሻያ እና ሌሎች አዳዲስ ተጨማሪ አገልግሎቶች ወደሚያስገኘው የተሻሻለ መተግበሪያ በቀላሉ ፕሌይ ስቶር፣ አፕ ስቶር እና አፕ ጋለሪ ላይ በመግባት አልያም መተግበሪያውን ሲከፍቱ የሚመጣውን “update” የሚለውን ጽሑፍ በመጫን ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ የሆነውን የቴሌብር ሱፐርአፕ አገልግሎት ማግኘት የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም

መስከረም 8 ቀን 2016 ዓ.ም

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives