የጥሪ ማሳመሪያ ከ አዳዲስ ገጽታዎች ጋር የጥሪ ማሳመሪያ ፍላጎትዎን ግምት ውስጥ በማስገባት የጥሪ ማሳመሪያ አገልግሎት በአዲስ አቀራረብ ተዘጋጅቷል፡፡ ለአገልግሎቱ በመመዝገብ ደዋዮችዎን እንዲሁም ራስዎን ዘና ያድርጉ! የአገልግሎት ዓይነቶች ♪ መደበኛ ጥሪ ማሳመሪ (ደዋዮችዎ የሚሰሙት) ♪ የደዋይ ጥሪ ማሳመሪያ (ወጪ ጥሪ ሲያደርጉ ለራስዎ የሚሰማ) የአገልግሎት ክፍያ ወርሃዊ ኪራይ: 5 ብር የቶን ግዢ: 5 ብር የጥሪ ማሳመሪያ / ሲአርቢቲ ባህሪያት እና ጥቅሞች በደዋዮችዎ ዘንድ የሚታወስ መለያ እንዲኖርዎት እንዲሁም ደዋዮችዎ ሳይሰለቹ እየተዝናኑ እንዲጠብቁዎት ያደርጋሉ፡፡ ለመረጡት ወዳጅዎ/ወዳጆችዎ የተለየ እና የተመረጠ ጥሪ ማሳመሪ ማድረግ ይችላሉ፡፡ በቀን ውስጥ በመረጡት ሰዓት እንዲሁም ለበዓላት የተለየ ጥሪ ማሳመሪያ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ፡ የጠዋት፣ የበዓል ቀናት ጥሪ፣ የፍቅረኛሞች ቀን ወዘተ….. የሀገር ውስጥ እና የውጪ ሀገር ሙዚቃዎችን እንዲሁም መንፈሳዊ ዝማሬዎች መርጠው መጠቀም ይችላሉ፡፡ ለሌሎች ደንበኞች የመረጡትን ጥሪ በስጦታ ማበርከት የሚችሉ ሲሆን በተጨማሪም ከሌሎች ተጠቃሚዎች ሰምተው የወደዱትን የራስዎ ማድረግ ያስችልዎታል፡፡ ተጨማሪ አሳይ ለአገልግሎቱ መመዝገብ፡- A ወደ 822 መላክ 822 ወይም *822# ይደውሉ ወደ www.crbt.et ይጎብኙ ጥሪዎችን ለመምረጥ እና አገልግሎቱን ለማስተዳደር 822 ይደውሉ እና መጠየቂያውን ይከተሉ በድረ-ገጻችን www.crbt.et ወይም *822# ይደዉሉ በ822 የፅሁፍ መልዕክት በመላክ የሚያገኟቸው መሰረታዊ አገልግሎቶች ማውጫ ቁጥርየአገልግሎት ዓይነትመደበኛ ጥሪ መሳመሪያየደዋይ ጥሪ መሳመሪያ1ለአገልግሎቱ ይመዝገቡAA12የጥሪ ማሳመሪያ ለመግዛትC የጥሪ ማሳመሪያ መለያ ቁጥርC የጥሪ ማሳመሪያ መለያ ቁጥር3የጥሪ ማሳመሪያ ለመምረጥSN የቶን ኮድSC የቶን ኮድ4ሌሎች የሚጠቀሙትን ጥሪ ማሳመሪያ ለመቅዳት/ለራስዎ ለመጫንመልሰው በመደወል ደንበኛው ከማንሳታቸው በፊት * ን ይጫኑ **5ለሌሎች ደንበኞች የጥሪ ማሳመሪያ በስጦታ ለመላክG የጥሪ ማሳመሪያ ኮድ የተቀባዩ ስልክ ቁጥርምሳሌ: G 123456 09XXXXXXXXG የጥሪ ማሳመሪያ ኮድ የተቀባዩ ስልክ ቁጥርምሳሌ: G 123456 09XXXXXXXX6ስጦታ መቀበልga የጥሪ ማሳመሪያ መለያ ቁጥርga የጥሪ ማሳመሪያ መለያ ቁጥር7ስጦታን አለመቀበልዎትን ለማሳወቅgr የጥሪ ማሳመሪያ መለያ ቁጥርgr የጥሪ ማሳመሪያ መለያ ቁጥር8እርዳታ ለማግኘትHH9ከግል ማህደርዎ የጥሪ ማሳመሪያ ለመምረጥPP10የግል መቼት ለመጠየቅ QCQC11የጥሪ ማሳመሪያ መቼት ለማጥፋትDC የጥሪ ማሳመሪያ መለያ ቁጥርDC1 የጥሪ ማሳመሪያ መለያ ቁጥር12አገልግሎቱን በጊዜያዊነት ለማቋረጥDACDAC113በጊዜያዊነት የተቋረጠውን መልሶ ለማስጀመርACAC114አገልግሎቱን ለማቋረጥUU1 ደንብና ሁኔታዎችሁሉም የቅድመ ክፍያ፣ ድህረ ክፍያ እና ሀይብሪድ ሞባይል ተጠቃሚዎች ለአገልግሎቱ መመዝገብ ይችላሉ፡፡ደንበኞች ለመደበኛ እንዲሁም ለደዋይ ጥሪ ማሳመሪያ አገልግሎት በተመሳሳይ ጊዜ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡የጥሪ ማሳመሪ አገልግሎት 822 ላይ የድምፅ ጥሪ በማድረግ, *822# በመደወል እንዲሁም በድረ ገፃችን https://www.crbt.et ማግኘት ይችላሉ፡፡የጥሪ ማሳመሪያ ተጠቃሚ ላልሆነ ደንበኛ የመረጡትን የጥሪ ሙዚቃ ገዝተው በስጦታ ለመላክ ከፈለጉ በተጨማሪ የሚቀበለውን ደንበኛ የአንድ ጊዜ ወርሃዊ መመዝገቢያ መክፈል ይጠበቅብዎታል፡፡ ስጦታው የደረሰው ደንበኛ ለአገልግሎቱ መመዝገብ እንደሚፈልግ በአጭር የፅሁፍ መልዕክት በአንድ ሰዓት ውስጥ ምላሽ መስጠት የሚጠበቅበት ሲሆን ከምዝገባው በኋላ የተበረከተለት የጥሪ ሙዚቃ የሚደርሰው ይሆናል፡፡የጥሪ ማሳመሪያ ለመረጡት ደንበኛ ወይም ደንበኞች ለመረጡት ሙዚቃ በመክፈል በአንድ ጊዜ መላክ ይችላሉ፡፡ወደሌሎች ደንበኞች ሲደውሉ ሰምተው ለራስዎ የፈለጉትን የጥሪ ማሳመሪያ ለመጠቀም ስልኩ ሳይነሳ (*) ምልክት በመጫን በስልክዎ የሚላክልዎትን የጥሪ ማሳመሪያው የመለያ ቁጥር ወደ 822 በመላክ የራስዎ ማድረግ ይችላሉ፡፡ የጥሪ ማሳመሪያው ተጠቃሚው ሌሎች ደንበኞች ጥሪውን እንዳይቀዱበት የማገድ መብት አለው፡፡· ማንኛውም ደንበኛ ሲመዘገብ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚጫነው ጥሪ መቀዳት የማይቻል ሲሆን ሌሎች ተጠቃሚ ደንበኞች ከመጀመሪያው ጥሪ ውጪ የቀየሩትን ማንኛውም ጥሪ ሰምተው ከወደዱት የራስዎ ማድረግ ይችላሉ፡፡ለአገልግሎቱ እንደተመዘገቡ የመጀመሪያው ጥሪ በነፃ የሚጫን ሲሆን በማንኛውም ጊዜ አዲስ ጥሪ መቀየር ይቻላል፡፡ደንበኞች የገዟቸው እስከ 20 የሚደርሱ ጥሪ ማሳመሪያዎች በግል ማህደራቸው የሚቀመጡ ሲሆን በማንኛውም ጊዜ መርጠው ከማህደራቸው ሊያጠፏቸው ይችላሉ፡፡ደንበኞች በጊዜያዊነት የጥሪ ማሳመሪያ ማቋረጥ የሚችሉ ሲሆን በግል ማህደራቸው የተቀመጡት ጥሪ ማሳመሪያዎች ሳይጠፉባቸው በድጋሚ ማስጀመር ይችላሉ፡፡ደንበኞች ወርሃዊ ኪራይ መክፈል የሚጠበቅባቸው ሲሆን ይህን ለማድረግ በቂ ሂሳብ ከሌላቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲመዘገቡ የሚደረገው ነባር የጥሪ ማሳመሪያ የሚሰማ ሲሆን ኪራዩ ከ7 ቀናት በኋላም የማይከፈል ከሆነ አገልግሎቱ በጊዜያዊነት ይታደገዳል፡፡ ነገር ግን ደንበኞች ከ15 ቀናት በኋላ ወርሃዊ ክፍያውን መፈፀም ካልቻሉ አገልግሎቱ እንዲቋረጥ ይደረጋል፡፡ደንበኞች በማንኛውም ጊዜ አገልግሎቱን ማቋረጥ የሚችሉ ሲሆን በድጋሚ አገልግሎቱን ለማግኘት ሲፈልጉ እንደ አዲስ ደንበኛ የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡