Ethiotelcom_Logo

የስንቅ አገልግሎትን ለማስጀመር እና ለመጠቀም ደንቦች እና ሁኔታዎች

  1. የውል ስምምነት
  2. ይህ ስምምነት (ከዚህ በኋላ “ደንቦች እና ሁኔታዎች” የሚባል) የስንቅ አገልግሎትን በተመለከተ አጠቃላይ ደንብ እና ሁኔታዎች ያካትታል፡፡
  3. እነዚህ ደንቦችና ሁኔታዎች እንዲሁም ከዚህ ጋር የተያያዙ ማሻሻያዎች እና ለውጦች ይህ በጽሁፍ ከታተመበት ጊዜ አንስቶ ሥራ ላይ ይውላሉ፡፡
  4. ትርጓሜ

በዚህ የደንቦች እና ሁኔታዎች መረጃ ውስጥ የተዘረዘሩ ቃላት እና አባባሎች የሚከተለውን ትርጉሜ ይይዛሉ፡-

  • “አነስተኛ የስንቅ አገልግሎት” ማለት ከታች በተቀመጡ ደንብ እና ሁኔታዎች መሰረት በኢትዮ ቴሌኮም ለደንበኞች የሚቀርብ የክሬዲት አገልግሎት ነው፡፡
  • “ዝግ የስንቅ አገልግሎት” ማለት ደንበኞች በተሻለ የወለድ መጠን በተወሰነ የጊዜ ገደብ ውስጥ መቆጠብ የሚችሉበት የስንቅ  አገልግሎት ዓይነት ነው።
  • “ደንበኛ” ማለት በስሙ አነስተኛ የስንቅ አካውንት ያለው የቴሌብር ደንበኛ ነው።
  • “አንተ” “አንቺ” ወይም “የአንተ” ማለት ደንበኛውን ለማለት ነው።
  • “ኢ-ገንዘብ” ማለት እኩል መጠን ያለው ጥሬ ገንዘብን የሚወክል ደንበኛው የሚመለከተው የቴሌብር የኤሌክትሮኒክስ የገንዘብ ዋጋ ነው።
  • “ዋና ገንዘብ” ማለት በመጀመሪያ በደንበኞች የተቀመጠ የገንዘብ መጠን ማለት ነው።
  1. ደንብ እና ሁኔታዎችን ስለመቀበል
  • የስንቅ አገልግሎትን ለመጠቀም ከማመልከትዎ በፊት እነዚህን ደንብ እና ሁኔታዎች በጥንቃቄ በማንበብ የክሬዲት ክፍያ ሂሳብ አጠቃቀም እና መመሪያን አንብበው ይስማሙ፡፡
  • በእነዚህ ደንቦችና ሁኔታዎች ካልተስማሙ እባክዎን ከዝርዝር መምረጫ /Menu/ ሰርዝ የሚለውን ይጫኑ፤
  • ደንቦችና ሁኔታዎችን እንዳነበቡ፣ እንደተረዱና እንደተቀበሉ የሚቆጠረው፡-
  • “ይስማሙ” የሚለውን አማራጭ ሲጫኑ ደንብ እና ሁኔታዎችን በማንበብ ተረድተው ለማክበር መስማማትዎን እንዳረጋግጡ ወይም ክሬዲት ክፍያን ለመጠቀም ይወሰዳል።
  • ደንብ እና ሁኔታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በኢትዮ ቴሌኮም ሊሻሻሉ ወይም ሊለዋወጡ የሚችሉ ሲሆን ከታወቀበት ዕለት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል፡፡
  • ከዚህ የማሳወቂያ ጊዜ በኋላ የስንቅ አገልግሎትን ለመጠቀም እና በማንኛውም ማሻሻያ ወይም ለውጥ ለመገዛት ተስማምተዋል፡፡
  • የስንቅ አገልግሎትን በኤሌክትሮኒካዊ መንገድ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ለመተግበር እና የስንቅ  አገልግሎትን በኤሌክትሮኒካዊ መንገድ በቴሌብር ሲስተም ለመጠቀም ተስማምተዋል።
  1. የስንቅ አገልግሎትን አገልግሎትን ለማስጀመር

የስንቅ  አገልግሎትን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ለማጀመር ቢያንስ፡-

  1. 18 አመት እና ከዚያ በላይ
  2. አገልግሎት የሚሰጥ የኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርድ መያዝ
  3. የቴሌብር እና የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቶችን እንደ ዳታ/ድምጽ/አጭር የጽሁፍ መልዕክት የሚጠቀሙ
  4. ለመመዝገብ በዩኤስኤስዲ(*127#) ወይም በቴሌብር መተግበሪያ መጠቀም ይችላሉ፡፡
  5. ለተሳካ ምዝገባ የማሳወቂያ አጭር የፅሁፍ መልዕክት ይደርስዎታል፡፡
  • የስንቅ አገልግሎት ከተመዘገቡ በኋላ ስልክዎን ተጠቅመው በቀላሉ የቴሌብር አማራጮችን በመጠቀም ወደ ስንቅ  አካውንትዎ ገንዘብ ማስቀመጥ እና ወጪ ማድረግ ይችላሉ።
  1. የስንቅ አገልግሎት አይነቶች
  • ወለድ ያለው፣ ከወለድ ነፃ የስንቅ አገልግሎት ወይም የተወሰነ መጠን ለተወሰነ ጊዜ መቆጠብ  ማስጀመር ይችላል።
  • ወለድ ያለው ስንቅን ከተጠቀሙ ለቆጠቡት ገንዘብ አበዳሪው በወሰነው የወለድ መጠን ክፍያ ያገኛሉ፡፡
  • መድበኛ ስንቅ አገልግሎትን ለመጠቀም ደንበኞች ማንኛውንም ገንዘብ ከብር 1 ጀምሮ ማስገባት አለባቸው፡ ወለድ ለማግኘት ግን ደንበኞች ከብር 26 በላይ ማስያዝ አለባቸው።
  • ለተቆለፈው ስንቅ ደንበኞች በአንድ ጊዜ ከብር 20,000 በላይ ማስገባት አለባቸው።
  • ደንበኞች ለ3 ወራት፣ ለ6 ወራት፣ ለ9 ወራት እና ለ12 ወራት ቢቆጥቡ 7.25%፣ 7.5%፣ 7.75% እና 8% በዓመት ወለድ ያገኛሉ።
  • ደንበኞች በግዜ ገደብ ያስቀመጡትን ገንዘብ ከግዜ ገደቡ በፊት ቢያወጡት የወለድ መጠኑ በመደበ (7%) ተሰልቶ ይሰጣቸዋል፡፡
  1. የአስተዳደር ህግ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕጎች፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የኢትዮ ቴሌኮም አግባብነት ያላቸው አሠራሮች እነዚህን ውሎችና ሁኔታዎች ይቆጣጠራሉ።

  1. መጠይቆች (መረጃ)

ከቴሌብር ስንቅ አገልግሎት ሂደት፣ ውሎች እና ሁኔታዎች ጋር ለተያያዘ ማንኛውም ጥያቄ በቴሌብር የደንበኞች ግንኙነት ማእከል (127 በመደወል) ተጨማሪ መረማግኘት ይችላሉ።

  1. የውል መቋረጥ

ማንኛውንም የአነስተኛ ቁጠባ አገልግሎቶችን ያለቅድመ ማስጠንቀቂያ ወይም ያለ ማስታወቂያ በእርስዎ አላግባብ መጠቀም ወይም ማጭበርበር ምክንያት ይህን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ለማገድ ወይም ለማቋረጥ መብት ይኖረናል። የዚህ ውል መቋረጥ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች መብቶችን እና ግዴታዎችን ሊነካ አይችልም።

  1. ቅሬታዎች

ቅሬታዎች በአካል፣ በጽሁፍ፣ በፖስታ፣ በፋክስ፣ በኢሜል ወይም በስልክ ሊቀርቡ ይችላሉ። ኢትዮ ቴሌኮም ቅሬታዎትን በተገቢው ጊዜ ለመፍታት ሁሉንም እርምጃዎች ይወስዳል። በመልሱ ካልተደሰቱ ጉዳዩን ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቅደም ተከተል ማድረስ ይችላሉ።

  1. የክርክር መፍትሄ

ከዚህ ውል ጋር በተያያዘ የሚነሳ ማንኛውም አለመግባባት ከላይ በአንቀጽ 9 መሠረት ያልተፈታ አለመግባባት ሥልጣን ላለው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፍርድ ቤት መቅረብ ይችላል።

  1. ማስተባበያ

የቴሌብር ሚስጥር ቁጥር (ፒን) በሚስጥር መቀመጥ አለበት፡፡ ከዕርስዎ ሌላ ለማንም ተደራሽ መሆን የለበትም። ከሚስጥር ቁጥር አጠቃቀም፣የሚስጥር ቁጥርን በየጊዜው አለመቀየር፣ ያልተፈቀደ የቴሌብር አካውንት መጠቀም፣ የሞባይል ስልክ ወይም ሲም ካርድ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ ለሚከሰት ኪሳራ ወይም ስርቆት የእርስዎ ሃላፊነት ብቻ ይሆናል።