Ethio telecom signs a contractual agreement with five Virtual Internet Service Provider partners

Ethio telecom signed a three-year contractual agreement with five virtual internet service partners namely WebSprix IT Solutions PLC, VIVATECH Trading PLC, Zergaw ISP, Skynet IT Solution PLC and Dulle Business Group. Based on the contractual agreement, our new partners will exclusively provide fixed broadband internet service and are believed to broadly availing the service accessible to customers at large and contributing to the overall efforts of the nation in realizing the digital transformation strategy.

As per the signed contract, the mentioned five partner firms would exclusively purchase the fixed bandwidth internet service from Ethio telecom and provide high bandwidth internet service to the customers across the country for the coming three consecutive years, thereby customers will have more options to get fixed broadband internet services from these five partner organizations in addition to Ethio telecom’s sales centres.

Hence, the partners are strongly expected to actively play their roles in heralding the digital Ethiopia plan of the company by providing efficient and quality services to their customers in collaboration with Ethio telecom.

These days, Ethio telecom is immensely working at a high priority to avail fixed broadband internet service to the customers nationwide in partnership with virtual internet service providers. In line with this, our partners have been able to avail fixed broadband internet service to 20,700 customers so far. To make sure that the fixed broadband internet service is accessible across the nation and increase the number of users to 3 million by the end of 2026 G.C, our company has designed and been executing a wide range of systems and strategies. 

In addition to our company’s continuous efforts to expand and meet the mobile internet penetration digital transformation plan of the nation, our partners will play paramount roles in making accessible fixed broadband internet service. As has been the backbone of the economy of the nation, fixed broadband internet service has also multiple roles to play in our society particularly in creating favorable business environment, improving

the health, education, digital marketing and social interaction. It will also enable public institutions and private organizations to digitalize their working system thereby providing efficient services to their customers.

It is obvious that Ethio telecom is highly engaged in a massive network capacity building in its drive to enhance economic growth, foster innovation, increase penetration, ensure affordability, minimize digital divide and enable the country to realize the national digital transformation strategy. In parallel to this infrastructure expansion, the company has recently made a massive tariff discount on fixed broadband internet service to meet the ever-increasing customer demands for the services.

Ethio telecom

April 11, 2022

ኢትዮ ቴሌኮም የመደበኛ ባለገመድ ኢንተርኔት አገልግሎትን በአጋርነት ከሚሰጡ ድርጅቶች ጋር ስምምነት ፈረመ

ኢትዮ ቴሌኮም የሃገራችንን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማሳካትና ለደንበኞቹ ይበልጥ ተደራሽ ለመሆን የሚያደርገውን ጥረት ለማገዝ የመደበኛ ባለገመድ ኢንተርኔት አገልግሎትን  በብቸኛ አጋርነት ከሚያቀርቡ አምስት ድርጅቶች ጋር ማለትም ከዌብ ስፕሪክስ አይቲ ሶሉሽን፣ ከቪቫ ቴክ ትሬዲንግ፣ ዘርጋው አይ ኤስ ፒ፣ ስካይ ኔት አይቲ ሶሉሽን እና ከዱሌ ቢዚነስ ግሩፕ ጋር የሶስት ዓመት ኮንትራት ተፈራረመ፡፡

በስምምነቱ መሠረት ድርጅቶቹ የመደበኛ ኢንተርኔት ከፍተኛ ባንድዊድዝ በመውሰድ በሁሉም የሃገራችን ክፍሎች ለሚገኙ ደንበኞች ለሶስት ዓመት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችላቸው ሲሆን፤ ደንበኞች ከኢትዮ ቴሌኮም ሽያጭ ማዕከላት በተጨማሪ ከተጠቀሱት አምስት ድርጅቶች የመደበኛ ኢንተርኔት አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡

በስምምነቱ መሰረት የኢትዮ ቴሌኮም አጋር ድርጅቶች አገልግሎቱን ከኩባንያው ጋር በመስራት በፍጥነትና በጥራት ለተጠቃሚው በማድረስ ኩባንያችን የያዘውን የዲጂታል ኢትዮጵያ ዕቅድ ለማሳካት የበኩላቸውን ሚና በብቃት መወጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የመደበኛ ኢንተርኔት አገልግሎት በመላ ሀገሪቱ በቀላሉ ለማድረስ ኩባንያችን ከቨርቹዋል ኢንተርኔት አቅራቢዎች (Virtual Internet Service Providers) ጋር በአጋርነት አገልግሎቱን እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን፣ በዚህም እስካሁን በአጋር ድርጅቶች አማካኝነት 20,700 ደንበኞችን ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ ሲሆን ኩባንያችን እ.ኢ.አ በ2026 የመደበኛ ኢንተርኔት አገልግሎትን በመላ ሃገሪቱ ተደራሽ ለማድረግ እና የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ደንበኞችን ቁጥር 3 ሚሊዮን ለማድረስ የተለያዩ መጠነ ሰፊ አሰራሮችን እና ስትራቴጂዎችን በመንደፍ በትግበራ ላይ ይገኛል፡፡

 

የሃገራችንን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እቅድን ለማሳካት ከሞባይል ኢንተርኔት በተጨማሪ በመደበኛ ባለገመድ ኢንተርኔት አገልግሎት ተዳሽነትን ለማስፋፋት ኢትዮ ቴሌኮም በራሱ እያከናወነ ከሚገኘው ሥራ በተጨማሪ የእነዚህ አጋር ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ አቅም የሚፈጥር ይሆናል፡፡ የብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ካለው ድርሻ በተጨማሪ ለማህበረሰቡ በጤና፣ በትምህርት፣ የዲጂታል ግብይት ስርአትን በማስፋት እና ማህበራዊ መስተጋብርን ለማዳበር የሚኖረው ሚና እንዳለ ሆኖ መንግስታዊ ተቋማትም ሆኑ የግል ድርጅቶች አሰራራቸውን በማዘን የዲጂታል አሰራርን እንዲተገብሩ እና ለተገልጋዮቻቸውም ቀልጣፋ አገልግሎትነን እንዲሰጡ ያስችላል፡፡

ኩባንያችን የዲጂታል ኢትዮጵያን ራዕይ እውን ለማድረግ የሚያስችል መጠነ ሰፊ የኔትወርክ አቅም ግንባታ በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በተለይም የሃገራችን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማፍጠን፣ አዳዲስ ፈጠራዎች እንዲጨምሩ እና እንዲበረታቱ ለማድረግ፣ የቴሌኮም ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም አሁን ያለውን የዲጂታል ዲቫይድ ክፍተትን ለመሙላት በትኩረት እየሰራ ሲሆን፤ መሰረተ ልማትን ከማስፋፋት ጎን ለጎን እያደገ የመጣውን የኢንተርኔት አገልግሎት ፍላጎት ለማርካት በቅርቡ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ቅናሽ በመደበኛ የብሮድባንድ ኢንተርኔት ላይ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

 

ኢትዮ ቴሌኮም

ሚያዝያ 03 ቀን 2014 ዓ.ም

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives