የቴሌብር ፓርትነር ሱፐርአፕ መተግበሪያ አጠቃቀም መግለጫ
- የቴሌብር ፓርትነር ሱፐርአፕ መተግበሪያ በኢትዮ ቴሌኮም ተሰናድቶ የቀረበ ሲሆን በዋናነት ለወኪሎችና ለነጋዴዎች የሚያገለግል ዘመናዊ እና ቀልጣፋ መተግበሪያ ነው፡፡ በዚህ የቴሌብር ፓርትነር ሱፐርአፕ መተግበሪያ ወኪሎችና እና ነጋዴዎች በቴሌ ብር በኩል የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለተጠቃሚዎች በማቅረብ ከደንበኞቻቸው ጋር በላቀ ሁኔታ እንዲቆራኙ፣ ንግዳቸውን (ገቢያቸውን) እንዲሳድጉ እና ቀላል ቀልጣፋ እና ምቹ በሆነው ቴሌብር መተግበሪያ በመጠቀም ደህንነቱ የተጠበቀ የገንዘብ ክፍያ እንቅስቃሴ ለማድረግ ያስችላል፡፡
የቴሌብር ፓርትነር ሱፐርአፕ ለወኪሎች ምን ይዟል?
- የባዮሜትሪክ ማረጋገጫ
- የአንድ ጊዜ ሚስጥር ቁጥር ማረጋገጫ
- ገንዘብ ለማስገባት
- ገንዘብ ለማውጣት
- የደንበኛ ምዝገባ
- ደረጃ ማሳደጊያ
- የአየር ሰዓት ለመሙላት
- ጥቅል ለመሸጥ
- የአገልግሎት ክፍያ መክፈል
- የፋይናንስ አገልግሎት
- ፈጣን መፈለጊያ
- የመልዕክት ማሳወቂያ
- የማስታወቂያ ገፅ
- ፎቶ ማስገቢያ
- የሱቅ መግለጫ
- ትኬት ለመግዛት
- በወኪል ገቢ ማድረግ
- በወኪል ወጪ ማደረግ
- የቴሌብር ፓርትነር ሱፐርአፕ መተግበሪያ ለመጠቀም ወኪሎችም ሆኑ ነጋዴዎች በቅድሚያ ምዝገባ ማከናወን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ምዝገባውን በስኬት ያጠናቀቁ ወኪሎች/ነጋዴዎች ባስመዘገቡት የእጅ ስልካቸው በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መተግበሪያውን ለመጠቀም የሚያስችል ‹‹አጭር ቁጥር›› እና ‹‹የኦፕሬተር መለያ ቁጥር›› ይደርሳቸዋል፡፡
- በወኪል አካውንት ለመጀመሪያ ጊዜ ለመግባት
- ምዝገባውን በስኬት ያጠናቀቀ ወኪል በ 127 በኩል መተግበሪያውን ለመጠቀም የሚያስችለውን አጭር ቁጥር፣ ኦፕሬተር መለያ ቁጥር እና ለመግቢያ የሚሆን ሚስጥር ቀጥር ይደርሰዋል፡፡
- የቴሌብር ፓርትነር ሱፐርአፕን በመክፈት በ127 በኩል የተላከልዎትን መግቢያ በመጠቀም ይግቡ የሚለውን ይጫኑ::
- ወደ መተግበሪያው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲገባ የወኪሉን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ለአንድ ጊዜ የሚያገለግል የሚስጥር ቁጥር (ኦቲፒ) የሚላክ ሲሆን፤ የመፃፊያ ቦታው ላይ በራሱ የሚገባ ይሆናል::
- በመቀጠል ለመግቢያ የተላከልዎትን የሚስጥር ቁጥር በመቀየር የራሱን አዲስ የሚስጥር ቁጥር እንዲያስገቡ የሚጋብዝ ገፅ ያገኛሉ
- በመቀጠል ነባሩን የሚስጥር ቁጥር፤ በማስከተል የራስዎን የሚስጥር ቁጥር፤ በመጨረሻም ማረጋገጫ በመስጠት የሚስጥር ቁጥር ይቀይሩ
- በመጨረሻ አዲሱን የሚስጥር ቁጥር እና የወኪል መለያ ቁጥር በመጠቀም ወደመተግበሪያው ዋና ገጽ ይግቡ
2.ፎቶ ለማስቀመጥ
- በዋና ገፅ ላይ ከስም ጎን የሚገኘውን የፎቶ ምልክት ወይም
በመተግበሪያው አናት በኩል የሚገኘውን ሶስት ሰረዞች ≡
በመንካት፤ ፎቶውን መጫን
- ፎቶ አንሳ ወይም ከመስል ማከማቻ ይምረጡ የሚለውን መንካት
- ማረጋገጥ
3.የባዮሜትሪክ ማረጋገጫ
- በዋናው ገፅ እራስጌ የሚገኘውን ሶስት ሰረዞች ≡ በመንካት
- የባዮሜትሪክ ማረጋገጫ በሚለው ስር ለመግቢያ እና ለክፍያ እንዲሆን መምረጥ
- የጣት አሻራ መግቢያ የሚለውን ማብራት
- የሚስጠር ቁጥር ማስገባት
- የጣት አሻራ መስጠት
4.የሚስጥር ቁጥር ለመቀየር
- በዋናው ገፅ እራስጌ የሚገኘውን ሶስት ሰረዞች ≡ በመንካት
- የሚስጥር ቁጥር ለመቀየር የሚለውን መምረጥ
- የአሁን የሚስጥር ቁጥር የሚለው ላይ ነባሩን ማስገባት
- አዲስ የሚስጥር ቁጥር ማስገባት
- አዲሱን የሚስጥር ቁጥር በመድገም ማረጋገጥ
- ያረጋግጡ የሚለውን በመጫን ማጠናቀቅ
5.ቋንቋ ለመቀየር
- በዋናው ገፅ እራስጌ የሚገኘውን ሶስት ሰረዞች ≡ በመንካት
- ቋንቋ ለመቀየር የሚለውን መምረጥ
- ከተዘረዘሩት አምስት ቋንቋዎች ውስጥ አንዱን መምረጥ
ማስታወሻ፡ የቋንቋዎች ዝርዝር (English፣አማርኛ፣Afaan Oromoo፣ትግርኛ፣Af Somali
5 የአገልግሎት ማዕከሉን ለማግኘት
7 ጥያቄና መልስ
- በዋናው ገፅ እራስጌ የሚገኘውን ሶስት ሰረዞች ≡ በመንካት
- ጥያቄና መልስ የሚለውን መምረጥ
- ከተዘረዘሩት ጥያቄና መልሶች ውስጥ ለበለጠ መረጃ እንዲሆንዎ ማጣቀሻ ያገኛሉ፡፡
8 ለአስተያየት
- በዋናው ገፅ እራስጌ የሚገኘውን ሶስት ሰረዞች ≡ በመንካት
- ለአስተያየት የሚለውን መምረጥ
- ጉዳዪን እና ማብራሪያውን ማስገባት
- ይላኩ የሚለውን መጫን
9 ስለ
- በዋናው ገፅ እራስጌ የሚገኘውን ሶስት ሰረዞች ≡ በመንካት
- ስለ የሚለውን መምረጥ
- የቴሌብር ስነምግባር እና ዝማኔን መመልከት ይችላሉ
ማስታወሻ፡ በዚህ ገፅ ስር ስለ ቴሌብር መተግበሪያ መረጃዎች ይገኛሉ
10 ዋና ገጽ - ሒሳብ መመልከቻ
- በዚህ ገጽ ላይ ወኪሉ የሚከተሉትን ማየት ይችላል
- ቀሪ ሒሳብ
- የአገልግሎት ክፍያ
- አኑቲ ኮሚሽን
ማስታወሻ፡ ሒሳብዎን ዝርዝር ለማግኘት/ለመሸፈን የአይን ምልክቱን ይጫኑ፡፡
ዋና ገጽ - ቁልፍ ቃል መፈለጊያ
- በዚህ ገጽ ላይ ወኪሉ ቁልፍ ቃላትን በማስገባት በተለያየ ምህዳር ያሉ አገልግሎቶችን ወይም መረጃዎችን ማግኘት ይችላል፡፡
- 10 3 ዋና ገጽ - ማሳወቂያ (ደውል)
- በዚህ ገጽ ላይ ወኪሉ የሚከተሉትን ያገኛል
- የአሰራር መረጃ
- የግብይት መልዕክት
- የማስታወቂያ ዜናዎች
10.4 ዋና ገጽ - ደንበኛ ለመመዝገብ
- በዚህ ገጽ ስር ወኪሉ የሚከተሉትን ያገኛል
- የደንበኛውን መረጃ ለማየት
- ደንበኛ መመዝገቢያ
- የደንበኛውን መረጃ ለማየት፡ ወኪሉ ሊመዘግበው የፈለገውን ደንበኛ የኢትዮ ቴሌኮም ማህደር መረጃ ማየት ይችላል፡፡ ይህን ለማድረግ በደንበኛው ቁጥር የሚላከውን የማረጋገጫ ቁጥር ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ደንበኛ መመዝገቢያ
- ወኪሉ ለምዝገባ የቀረበውን የደንበኛ የሞባይል ቁጥር በማስገባት ማረጋገጫ ያግኙ የሚለውን በመጫን የተላከውን መልዕክት መጠበቅ፡፡
- ሊሚዘገብ የቀረበው የደንበኛ ቁጥር ላይ የተላከውን የማረጋገጫ ቁጥር በማስገባት ይቀጥሉ የሚለውን መጫን
- የኮከብ (*) ምልክት የተደረገባቸው አስገዳጅ የሆኑ የተመዝጋቢውን መረጃዎች በማስገባት ማጠናቀቅ
ማስታወሻ፡ የሚከተሉት መረጃዎች አስገዳጅ ናቸው
- መታወቂያ ፣ የመታወቂያ ቁጥር ፣ የመታወቂያ ፎቶ በፊትና በጀርባ ፣ የደንነኛው ፎቶ ፣ የደንበኛው ስም የአባት ስም ፣ የአያት ስም ፣ ፃታ ፣ የትውልድ ዘመን ፣ ክልል ፣ ዞን/ክ/ከተማ ፣ ወረዳ ፣ ቀበሌ ፣ የቤት ቁጥር
- ወኪሉ ያስገባውን መረጃ ትክክለኛነት ካረጋገጠ በኃላ ላክ የሚለውን ቁልፍ በመጫን ይጨርሳል
- ያልተሞላ ወይም ስህተት ያለበት መረጃ ካለ ወዲያውኑ ለወኪሉ የሚያሳውቀው ሲሆን፤ ድጋሜ አስተካክሎ በመሙላት ማጠናቀቅ ያስፈልጋል
10.6 ዋና ገጽ - ገንዘብ ለማስገባት
በዚህ ገጽ ስር ወኪሉ የሚከተሉትን ያገኛል
- በገንዘብ አስገቢው ሞባይል ቁጥር/QR
- በኪው አር ኮድ/QR
- በቮውቸር መለያ ቁጥር
- በገንዘብ አስገቢው ሞባይል ቁጥር
- ወኪሉ የገንዘብ አስገቢውን የሞባይል ቁጥር በማስገባት ይቀጥሉ የሚለውን መጫን
- የአስገቢውን ሙሉ ስም ቀጥሎ ከሚመጣው ገፅ ላይ በማረጋገጥ፤ ተቀማጭ ሊያደረግ የፈለገውን የብር መጠን በማስገባት እና እሽ የሚለውን ይጫኑ
- ከመጣው ገጽ ላይ ገንዘብ ለማስገባት የሚለው ተጭኖ የሚስጥር ቁጥር በማስከተል መጨረስ፡፡ እንደ አማራጭ ከሚስጥር ቁጥር ውጭ በእጅ አሻራ ብቻ ግብይቱን ማጠናቀቅ ይቻላል፡፡
- በኪው አር ኮድ/QR
- ወኪሉ በገንዘብ አስገቢው የተዘጋጀውን የኪው አር ኮድ ፍሬም አስተካክሎ ማንበብ
- የአስገቢውን ሙሉ ስም ቀጥሎ ከሚመጣው ገፅ ላይ በማረጋገጥ፤ ተቀማጭ ሊደረግ የፈለገውን የብር መጠን በማስገባት እና እሺ የሚለውን ይጫኑ
- ከመጣው ገጽ ላይ ገንዘብ ለማስገባት የሚለው ተጭኖ የሚስጥር ቁጥር በማስከተል መጨረስ፡፡ እንደ አማራጭ ከሚስጥር ቁጥር ውጭ በእጅ አሻራ ብቻ ግብይቱን ማጠናቀቅ ይቻላል፡፡
-
- በቮውቸር መለያ ቁጥር
- ወኪሉ ከገንዘብ አስገቢው ስልክ ላይ የደረስውን የቮውቸር መለያ ቁጥር ቮውቸር ኮድ የሚለው ክፍት ቦታ ላይ በማስገባት የገንዘብ መጠን የሚለው ላይ ደግሞ ደንበኛው ተቀማጭ ሊያደረግ የፈለገውን የብር መጠን በመፃፍ ይቀጥሉ የሚለውን መጫን
- በቀጣይ ገፅ ላይ ወኪሉ ያስገባውን መረጃ አጠቃሎ የሚያመጣ ሲሆን ትክክለኛነቱን ካረጋገጡ በኃላ ይቀጥሉ የሚለውን መጫን
ከመጣው ገጽ ላይ ገንዘብ ለማስገባት የሚለው ተጭኖ የሚስጥር ቁጥር በማስከተል መጨረስ፡፡ እንደ አማራጭ ከሚስጥር ቁጥር ውጭ በእጅ አሻራ ብቻ ግብይቱን ማጠናቀቅ ይቻላል፡፡
- 10.7 ዋና ገጽ - ገንዘብ ለማውጣት
በዚህ ገጽ ስር ወኪሉ የሚከተሉትን ያገኛል
- በኪው አር ኮድ/QR
- በቮውቸር መለያ ቁጥር
- በኪው አር ኮድ/ QR
- ወኪሉ ደንበኛው እንዲወጣ ያዘዘውን ብር የገንዘብ መጠን በሚለው ቦታ ላይ በማስገባት የኪው አር ኮዱን ምስል ማስቀመጥ ወይም ደንበኛውን የኪው አር ፍሬሙን ቀጥታ ማስነበብ
- ደንበኛው በወኪሉ የተመለከተውን ኪው አር ኮድ በማንበብ የወኪሉን ስም እና የገንዘብ መጠን ትክክለኛነት ካረጋገጠ በኃላ የሚስጥር ቁጥሩን በማስገባት ትዕዛዙን ማጠናቀቅ
- በቮውቸር መለያ ቁጥር
- ወኪሉ ከገንዘብ አውጪው ስልክ ላይ የደረስውን የቮውቸር መለያ ቁጥር ቮውቸር ኮድ የሚለው ክፍት ቦታ ላይ በማስገባት የገንዘብ መጠን የሚለው ላይ ደግሞ ደንበኛው ወጪ ሊያደርግ የፈለገውን የብር መጠን በመፃፍ በማስቀጠል የደንበኛውን የሞባይል ቁጥር የመጨረሻ 4 ቁጥሮች በመፃፍ ይቀጥሉ የሚለውን መጫን
- በቀጣይ ገፅ ላይ ወኪሉ ያስገባውን መረጃ አጠቃሎ የሚያመጣ ሲሆን ትክክለኛነቱን ካረጋገጡ በኃላ ይቀጥሉ የሚለውን መጫን
- ከመጣው ገጽ ላይ ገንዘብ ለማውጣት የሚለው ተጭኖ የሚስጥር ቁጥር በማስከተል መጨረስ፡፡ እንደ አማራጭ ከሚስጥር ቁጥር ውጭ በእጅ አሻራ ብቻ ግብይቱን ማጠናቀቅ ይቻላል፡፡
10.9 ዋና ገጽ - ጥቅል ለመሸጥ
- የደንበኛ የሞባይል ቁጥር ያስገቡ በሚለው የመጻፊያ ቦታ ላይ ጥቅል የሚገዛለትን ደንበኛ ቁጥር ማስገባት
- ተዘርዝረው ከሚገኙት የጥቅል አይነቶች ውስጥ በደንበኛው የተፈለገውን የጥቅል አይነት በመምረጥ ክፍያውን ለማጠናቀቅ
- በሚስጥር ቁጥር ወይም በእጅ አሻራ ትዕዛዙን ማረጋገጥ
10.10 ዋና ገጽ - የአየር ሰዓት ለመሙላት
- የደንበኛውን የአገልግሎት ቁጥር እና የገንዘብ መጠን በማስገባት ወይም ከተዘረዘሩት ውስጥ መምረጥ
- በሚስጥር ቁጥር ወይም በእጅ አሻራ ትዕዛዙን ማረጋገጥ
10.11 ዋና ገጽ - ቢል መክፈል
- የደንበኛውን የአገልግሎት ቁጥር ወይም የአካውንት ቁጥር በማስገባት ይቀጥሉ የሚለውን መጫን
- ከተዘረዘሩት ያልተከፈሉ የቢል እዳዎች ጠቅላላ የሚለውን ወይንም በከፊል መርጦ ይቀጥሉ የሚለውን መጫን
- በሚስጥር ቁጥር ወይም በእጅ አሻራ ትዕዛዙን ማረጋገጥ
10.12 ዋና ገጽ - ትኬት ለመግዛት
- ከተዘረዘሩት የትኬት ሽያጭ አማራጮች ውስጥ በደንበኛው የተጠየቀውን መምረጥ
- የደንበኛውን የሞባይል ስልክ ማስገባት
- የትኬት አይነት እና የትኬት ብዛት ማስገባት
- በሚስጥር ቁጥር ወይም በእጅ አሻራ ትዕዛዙን ማረጋገጥ
10.13 ዋና ገጽ - የፋይናንስ አገልግሎት
- ወኪሉ በወቅቱ የፋይናንስ አገልግሎት ከሚያቀርቡት ውስጥ አንዱን መምረጥ
- የተፈቀደለትን የብር መጠን በእያንዳንዱ ኮንትራት ውስጥ ገብቶ በመመልከት ይሆነኛል የሚለውን ክሬዲት መምረጥ
- በመጨረሻም የኮንትራቱን ይዘት ከሚያመላክተው ላይ በጥንቃቄ በመመርመር ትዕዛዙን በሚስጥር ቁጥር ማረጋገጥ
- ከዳሽን ባንክ ጋር በትብብር የሚሰጡ የፋይናንስ አገልግሎት - አጋዥ መላ በአንድ፣ በሁለት፣ በሶስት፣ በስድስት እና በዘጠኝ ወር ክፍያ
- ከንግድ ባንክ ጋር በትብብር የሚሰጡ የፋይናንስ አገልግሎት - ድልድይ በአንድ፣ በሁለት እና በሶስት ወር ክፍያ
- 10.14 ዋና ገጽ - ለወኪል ማስተላለፍ
- የተወካይን አጭር ቁጥር/ቲል ማስገባት
- የኦፕሬተር መለያ ቁጥር ማስገባት
- የገንዘብ መጠን ማስገባት
- በሚስጥር ቁጥር ወይም በእጅ አሻራ ትዕዛዙን ማረጋገጥ
10.16 ዋና ገጽ - ኪው አር ኮድ ለማንሳት
- ወኪሎች የተለያዩ ግብይቶችን ለመፈጸም ቁልፉን በመጫን ከኪው አር ኮድ ፍሬሙን ለማንበብ ያስችላቸዋል፡፡
- በወኪል ገቢ ለማድረግ በዋና ወኪል ኪው አር ኮዱን ስካን በማድረግ ገቢ የሚደረገውን የገንዘብ ቀድሞ በተዘጋጀው የኪው አር ኮድ መሰረት ገቢ ለማድረግ ያስችላል
- በወኪል ወጪ ለማድረግ የተቀባይን አጭር ቁጥር እና የገንዘብ መጠን በማስገባት እና ይቀጥሉ የሚለውን መጫን ማከናወን ይቻላል፡፡
- ትዕዛዙን በሚስጥር ቁጥር ወይም በጣት አሻራ ማረጋገጥ
11 አገልግሎት
- በአገልግሎት ስር ለተለያዩ ተቋማት የአገልግሎት ክፍያ መፈፀሚያ ሲሆን የቴሌብር ወኪሎች በደንበኛ የተጠየቀውን የአገልግሎት አይነት በመምረጥ ክፍያ መፈፀም ያስችላል
- ክፍያ የሚፈፀምለትን የአገልግሎት ተቋም በቁልፍ መፈለጊያ ወይም በአገልግሎት አይነት በማህደር ተስድረው ከሚገኙት ውስጥ መምረጥ ይችላል
12.መተግበሪያዎቸ
- የቴሌብር ወኪሎች ሌሎች መተግበሪያዎችን በፓርትነር ሱፐራፕ በመጠቀም ማግኘት እና በቀላሉ ለመጠቀም የሚችሉበት ገጽ ነው፡፡
13.ሪፖርት
- ወኪሎች ጠቅላላ ሪፓርታቸውን ግብይት፣ የአገልግሎት ክፍያ እና ምዝገባ በሚል ያገኛሉ
- በግብይት ስር ወኪሎች ኦፕሬተር ይምረጡ የሚለውን በመጫን ካሏቸው ሰራተኞች ውስጥ መምረጥ ያስችላቸዋል
- በተጨማሪም ለሪፖርት ማውጫ የሚያስፈልገውን ቀን እና ሰዓት በመምረጥ በተመረጡት ቀናት ውስጥ የነበረውን ጠቅላላ ገቢ ፣ ጠቅላላ ወጪ እና የተጣራ ሂሳብ ማወቅ ይችላሉ
- በግብይት ሂሳብ መግለጫ ስር የተከናወኑ የግብይት አይነቶችን እና የብር መጠናቸውን ያገኛሉ
- የአገልግሎት ክፍያ ስር የአገልግሎት ክፍያ ድምር ተዘርዝሮ የተቀመጠ ሲሆን ለሪፖርት ማውጫ የሚያስፈልገውን ቀን እና ሰዓት በመምረጥ በተመረጡት ቀናት ውስጥ የነበረውን የተጠቃለለ የአገልግሎት ክፍያ ማወቅ ይቻላል
- በምዝገባ ስር አጠቃላይ የተመዘገቡ የተጠቃሚዎች ቁጥር ማግኘት የሚያስችል ሲሆን ለሪፖርት ማውጫ የሚያስፈልገውን ቀን እና ሰዓት በመምረጥ በኦፕሬተር ደረጃ መረጃን ለማግኘት ያስችላል
14. ዋና ገጽ
14.1 ዋና ገጽ - ሒሳብ መመልካቻ
- በዚህ ገጽ ላይ የቴሌብር ነጋዴ የሚከተሉትን ማግኘት ይችላል
- ቀሪ ሒሳብ
- የአገልግት ክፍያ
- አኑቲ ኮሚሽን
ማስታወሻ፡ ሒሳብዎን ዝርዝር ለማግኘት/ለመሸፈን የአይን ምልክቱን ይጫኑ፡፡ የነጋዴ የአድሚን ፍቃድ ያለው ሂሳብ የሚችል ሲሆን የአድሚን ፍቃድ የሌለው ግን ሂሳብ ለማየት አልተፈቀደለትም
14.2 ዋና ገጽ - ገንዘብ ለመቀበል
- ነጋዴው ለሸጠው እቃ የክፍያ መጠኑን ከደንበኛው ጋር ተነጋግሮ ከተስማማ በኃላ በኪው አር ኮዱ ላይ የገንዘብ መጠኑን ማስገባት
- በመቀጠል ደንበኛውን የኪው አር ኮዱን ፍሬም እንዲያነቡ በመጋበዝ ክፍያውን ማጠናቀቅ ይችላል
14 3 ዋና ገጽ - የነዳጅ ክፍያ
- ነጋዴው በነዳጅ ክፍያ ስር የሚከተሉት ያገኛል
- በድጎማ
- ያለ ድጎማ
- ለድርጅት ነዳጅ ክፍያ (ኩፓን)
- በበርሜል
- ነጭ ጋዝ
14.4 የነዳጅ ክፍያ - በድጎማ
- የነዳጅ ግብይት ፈጻሚ ድጎማ የተፈቀደለት ተሽከርካሪ መሆኑን ካረጋገጠ በኃላ አስገዳጅ ሆነው የኮከብ ምልክት ተደረገባቸውን መረጃዎች ማስገባት
- አስገዳጅ የሆኑ መረጃዎች የሚከተሉት ናቸው
- የነዳጅ አይነት (ቤንዚን ወይም ናፍጣ)
- ቤንዚን
- ናፍጣ
- የሰሌዳ ቁጥር
- የመኪና ኮድ
- የክልል ኮድ
- የሰሌዳ ቁጥር
- መረጃዎቹን ከሞሉ በኃላ ይቀጥሉ የሚለውን መጫን
- የተሽከርካሪው መረጃ ለነዳጅ ድጎማ ተመዝግቦ የሚገኝ ከሆነ ዝርዝር መረጃው በቀጣይ ገጽ ላይ የሚታይ ሲሆን ነገር ግን የተሽከርካሪ መረጃ ለነዳጅ ድጎማ ያልተመዘበ ከሆነ የድጎማ ተጠቃሚ ባለመሆኑ ያለመመዝገቡን የሚያሳይ መረጃ ያገኛሉ
- የድጎማ ተጠቃሚ ከሆኑ መረጃውን አመሳክሮ ይቀጥሉ የሚለውን መጫን እና የአሽከርካሪውን የክፍያ ማረጋገጫ መጠበቅ
የነዳጅ ክፍያ - ያለ ድጎማ
- ነጋዴው በሁለት መንገድ ደንበኛውን ሊያስተናግድ ይችላል
- በአጭር ቁጥር
- በኪው አር ኮድ
- በአጭር ቁጥር ያለ ድጎማ የነዳጅ መቅዳቱን ለማስተናበር ነጋዴው የሚከተሉትን መረጃዎች ማስገባት ይጠበቅበታል
- የደንበኛውን የሞባይል ቁጥር
- የገንዘብ መጠን
- የነዳጅ አይነት
- ቤንዚን
- ናፍጣ
- የሰሌዳ መረጃ
- የመኪና ኮድ
- የክልል ኮድ
- የሰሌዳ ቁጥር
- ነጋዴው የመረጃውን ትክክለኛነት ካረጋገጠ በኃላ ይቀጥሉ የሚለውን ቁልፍ በመጫን ወደ ቀጣይ ገጽ ያልፋል
- በመጨረሻም ያረጋግጡ የሚለውን በመጫን ከአሽከርካሪውን የክፍያ ማረጋገጫ መጠበቅ
- አሽከርካሪው የደረስው መልዕክት ላይ የሚስጥር ቁጥሩን በማስገባ ግብይቱን ማጠናቀቅ ይቻላል
- ነዳጅ ቀጂው ነጋዴ የሚስጥር ቁጥር ጥያቄው በደንበኛው ወዲያው ተቀባይነት እንዳገኘ - ክፍያው እንደተፈፀመ የሚያመላክት መረጃ በቴሌብር ሱፐርአፑ ገፅ ላይ ይመላከታል
- የክፍያ መፈፀሙን ከሚያረጋግጠው ገፅ ላያ ነዳጅ ቀጂው ቲፕ ጠይቅ የሚለውን በመጫን ከአሽከርካሪው ቲፕ ለመጠየቅ መላክ ይችላል
14 5 የነዳጅ ክፍያ - ለድርጅት ነዳጅ (ኩፓን)
- ነጋዴው በሁለት መንገድ ደንበኛውን ሊያስተናግድ ይችላል
- በአጭር ቁጥር
- በኪው አር ኮድ
- በአጭር ቁጥር ያለ ድጎማ የነዳጅ መቅዳቱን ለማስተናበር ነጋዴው የሚከተሉትን መረጃዎች ያስገቡ
- የደንበኛውን የሞባይል ቁጥር
- የገንዘብ መጠን
- የነዳጅ አይነት
- ቤንዚን
- ናፍጣ
- የሰሌዳ መረጃ
- የመኪና ኮድ
- የክልል ኮድ
- የሰሌዳ ቁጥር
- የመጨረሻ ኪሜ
- ነጋዴው የመረጃውን ትክክለኛነት ካረጋገጠ በኃላ ይቀጥሉ የሚለውን ቁልፍ በመጫን ወደ ቀጣይ ገጽ ያልፋል
- በመጨረሻም ያረጋግጡ የሚለውን በመጫን ከአሽከርካሪውን የክፍያ ማረጋገጫ መጠበቅ
- አሽከርካሪው የደረስው መልዕክት ላይ የሚስጥር ቁጥሩን በማስገባ ግብይቱን ማጠናቀቅ ይቻላል
- ነዳጅ ቀጂው ነጋዴ የሚስጥር ቁጥር ጥያቄው በደንበኛው ወዲያው ተቀባይነት እንዳገኘ - ክፍያው እንደተፈፀመ የሚያመላክት መረጃ በቴሌብር ሱፐርአፑ ገፅ ላይ ይመላከታል
- የክፍያ መፈፀሙን ከሚያረጋግጠው ገፅ ላያ ነዳጅ ቀጂው ቲፕ ጠይቅ የሚለውን በመጫን ከአሽከርካሪው ለመጠየቅ መላክ ይችላል
የነዳጅ ክፍያ - ለድርጅት ነዳጅ (ኩፓን)
- ነጋዴው በሁለት መንገድ ደንበኛውን ሊያስተናግድ ይችላል
- በአጭር ቁጥር
- በኪው አር ኮድ
- በኪው አር ኮድ ያለ ድጎማ የነዳጅ መቅዳቱን ለማስተናበር ነጋዴው የሚከተሉትን መረጃዎች የመፃፊያ ገጹ ላይ ማስገባት ይጠበቅበታል
- የገንዘብ መጠን
- የነዳጅ አይነት
- ቤንዚን
- ናፍጣ
- የሰሌዳ መረጃ
- የመኪና ኮድ
- የክልል ኮድ
- የሰሌዳ ቁጥር
- የመጨረሻ ኪሜ
- ነጋዴው የመረጃውን ትክክለኛነት ካረጋገጠ በኃላ ይቀጥሉ የሚለውን ቁልፍ በመጫን ወደ ቀጣይ ገጽ ያልፋል
- ነዳጅ ቀጂው በገፁ ላይ የመጣለትን የኪው አር ኮድ ፍሬም በአሽከርካሪው ስልክ በማስነበብ ክፍያውን ማጠናቀቅ ይቻላል
- አሽከርካሪው በተጓዳኝ የኪው አር ኮዱን ፍሬም በማንበብ የሚስጥር ቁጥሩን በማስከተል ክፍያውን ማጠናቀቅ ይችላል
- ነዳጅ ቀጂው ነጋዴ በደንበኛው ገብየቱ ተቀባይነት እንዳገኘ ወዲያውኑ - ክፍያው እንደተፈፀመ የሚያመላክት መረጃ በቴሌብር ሱፐርአፑ ገፅ ላይ ይመላከታል
- የክፍያ መፈፀሙን ከሚያረጋግጠው ገፅ ላያ ነዳጅ ቀጂው ቲፕ ጠይቅ የሚለውን በመጫን ከአሽከርካሪው ለመጠየቅ መላክ ይችላል
14.6 የነዳጅ ክፍያ - በርሜል
- ነጋዴው በሁለት መንገድ ደንበኛውን ሊያስተናግድ ይችላል
- በአጭር ቁጥር
- በኪው አር ኮድ
- በአጭር ቁጥር ያለ ድጎማ የነዳጅ መቅዳቱን ለማስተናበር ነጋዴው የሚከተሉትን መረጃዎች የመፃፊያ ገጹ ላይ ማስገባት ይጠበቅበታል
- የሞባይል ቁጥር
- የሊትር መጠን
- የገንዘብ መጠን
- የነዳጅ አይነት (ቤንዚን ወይም ናፍጣ)
- የደብዳቤ ቁጥር
- የድርጅት ወይም የግለሰብ ስም
- ደብዳቤውን የሰጠው (የክልል ኮድ፣ ዞን/ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ)
- የቲን ቁጥር
- ነጋዴው የመረጃውን ትክክለኛነት ካረጋገጠ በኃላ ይቀጥሉ የሚለውን ቁልፍ በመጫን ወደ ቀጣይ ገጽ ያልፋል
- በመጨረሻም ያረጋግጡ የሚለውን በመጫን ከአሽከርካሪውን የክፍያ ማረጋገጫ መጠበቅ
- አሽከርካሪው የደረስው መልዕክት ላይ የሚስጥር ቁጥሩን በማስገባ ግብይቱን ማጠናቀቅ ይቻላል
- ነዳጅ ቀጂው ነጋዴ የሚስጥር ቁጥር ጥያቄው በደንበኛው ወዲያው ተቀባይነት እንዳገኘ - ክፍያው እንደተፈፀመ የሚያመላክት መረጃ በቴሌብር ሱፐርአፑ ገፅ ላይ ይመላከታል
- የክፍያ መፈፀሙን ከሚያረጋግጠው ገፅ ላያ ነዳጅ ቀጂው ቲፕ ጠይቅ የሚለውን በመጫን ከአሽከርካሪው ለመጠየቅ መላክ ይችላል
14.7 የነዳጅ ክፍያ - ነጭ ጋዝ
- ነጋዴው በሁለት መንገድ ደንበኛውን ሊያስተናግድ ይችላል
- በአጭር ቁጥር
- በኪው አር ኮድ
- በአጭር ቁጥር ያለ ድጎማ የነዳጅ መቅዳቱን ለማስተናበር ነጋዴው የሚከተሉትን መረጃዎች የመፃፊያ ገጹ ላይ ማስገባት ይጠበቅበታል
- የደንበኛውን የሞባይል ቁጥር
- የገንዘብ መጠን
- ነጋዴው የመረጃውን ትክክለኛነት ካረጋገጠ በኃላ ይቀጥሉ የሚለውን ቁልፍ በመጫን ወደ ቀጣይ ገጽ ያልፋል
- በመጨረሻም ያረጋግጡ የሚለውን በመጫን ከደንበኛው የክፍያ ማረጋገጫ መጠበቅ
- ደንበኛው የደረስው መልዕክት ላይ የሚስጥር ቁጥሩን በማስገባ ግብይቱን ማጠናቀቅ ይቻላል
- ነዳጅ ቀጂው ነጋዴ የሚስጥር ቁጥር ጥያቄው በደንበኛው ወዲያው ተቀባይነት እንዳገኘ - ክፍያው እንደተፈፀመ የሚያመላክት መረጃ በቴሌብር ሱፐርአፑ ገፅ ላይ ይመላከታል
- በኪው አር ኮድ ያለ ድጎማ የነዳጅ መቅዳቱን ለማስተናበር ነጋዴው የሚከተለውን መረጃ የመፃፊያ ገጹ ላይ ያስገባል
- የገንዘብ መጠን
- ነጋዴው የመረጃውን ትክክለኛነት ካረጋገጠ በኃላ ይቀጥሉ የሚለውን ቁልፍ በመጫን ወደ ቀጣይ ገጽ ያልፋል
- ነዳጅ ቀጂው በገፁ ላይ የመጣለትን የኪው አር ኮድ ፍሬም በደንበኛው ስልክ በማስነበብ ክፍያውን ማጠናቀቅ ይቻላል
- ነዳጅ ሻጩ የክፍያ መረጋገጫውን የሱፐርአፑ ገፅ ላይ ወዲያውኑ ያገኛል
14.8 ቲፕ
- ነዳጅ ቀጂው ነጋዴ ለአሽከርካሪው የሚያስፈልገውን አገልግሎት ከሰጠ በኃላ ክፍያው በስኬት እንደተጠናቀቀ የሚገልጽ ገፅ ላይ ቲፕ ጠይቅ የሚለውን ቁልፍ በመጫን ጥያቄ ማቅረብ ይችላል
- ቀጥሎ ከሚመጣው ገፅ ላይ የቲፕ ተጠያቂው ስም እና ስልክ ተያይዞ የሚመጣ ሲሆን በማስከተል ተዘርዝረው ከሚገኙት አማራጭ የብር መጠኖች ወይም ደግሞ ሌላ መጠን የሚለው ላይ ለቲፕ የሚጠየቀው የብር መጠንን በማስገባ ያረጋጡ የሚለውን መጫን
- የቲፕ ይከፈለኝ ጥያቄው ወደያውኑ አገልግሎት ወዳገኘው ደንበኛ የሚደርስ ሲሆን ፈቃደኛ ሆኖ በሚስጥር ቁጥር የሚያስገባ ከሆነ ለነዳጅ ቀጂው ወዲያውኑ ገንዘቡ በቴሌብር ቁጥሩ የሚገባለት ይሆናል፡፡
- ማስታወሻ፡ አገልግሎት ያገኘው ደንበኛ ቲፕ ለመስጠት ወደቴሌብር ሱፐር አፕ በመግባት የግብይት ዝርዝር ስር የግብይት አይነቱን በመምረጥ ቲፕ በቀላሉ መስጠት
15. ሪፖርት
- ነጋዴዎች ጠቅላላ የቴሌብር ግብይታቸውን ሪፖርት በሚለው ስር ገብተው ማግኘት ይችላሉ
- ነጋዴዎች ቀን እና ሰዓት በመምረጥ በተመረጡት ቀናት ውስጥ የነበረውን ጠቅላላ ገቢ ፣ ጠቅላላ ወጪ እና የተጣራ ሂሳብ ማወቅ ይችላሉ
- በተጨማሪም ግብይት የተከናወነባቸው አማራጮች በመለየት በ ዩኤስኤስስዲ ወይም ኪው አር ኮድ ብሎ ሪፓርቱን መለየት በግብይቱ አይነት ዝርዝር ለማግኘት ይረዳል
- በግብይት ሂሳብ መግለጫው ስር ደግሞ የተከናወኑ የግብይት አይነቶችን እና የብር መጠናቸውን ያመላክታል
16. የእኔ ሰራተኞች
- የአድሚን ፍቃድ ያለው ነጋዴ በስሩ ያሉ ሰራተኞቹን የሚስጥር ቁጥር መቀየር የሚችሉበት ቦታ ነው
- ሚስጥር ቁጥሩ እንዲቀየርለት የጠየቀውን የሰራተኛ ስም ከዝርዝሩ ውስጥ በመፈለግ ፒን ዳግም ያስጀምሩ የሚለውን መምረጥ
- በቀጣይ ገፅ ላይ ማስታወሻ በሚል መረጃ የሚያጋራ ሲሆን ነጋዴው የሚስጥር ቁጥር ቅያሬውን ለማጠናቀቅ ለመላክ የሚለውን መጫን እና ለማጠናቀቅ የሚስጥር ቁጥር ማስገባት
- ሰራተኛው የደረሰውን የሚስጥር ቁጥር በማስገባት እና በራሱ የሚስጥር ቁጥር በመቀየር አገልግሎቱን ስጀመር ይችላል
- በቴሌብር የገንዘብ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ወኪሎች፣ ነጋዴዎች፣ ማስተር ኤጀንቶች እንዲሁም ተቋማት ከባንክ አካውንታቸው ወደቴሌብር አጭር ቁጥር በባንኩ መተግበሪያ፣ ዩኤስኤስዲ፣ ኢንተርኔት ባንኪንግ ወይም በቅርንጫፎች በአካል በመገኘት ገንዘብ ከባንክ ለማስተላለፍ የሚረዳ ሲሆን ያለምንም ገንዘብ እጥረት ግብይትን ለማሳለጥ ይጠቅማል፡፡
- ተቀባዩ የቴሌብር ተመዝጋቢ እና አጭር ቁጥር ያለ መሆን ይኖርበታል፡፡
በመተግበሪያ እና በዩኤስኤስዲ በመጠቀም ገንዘብ ከባንክ ወደቴሌብር ለማስተላለፍ የሚችሉባቸው ባንኮች ፦
- ህብረት ባንክ፣ አማራ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ብርሃን ባንክ
እንዲሁም በቅርንጫፎች በአካል በመገኘት ገንዘብ ከባንክ ወደቴሌብር ለማስተላለፍ የሚችሉባቸው ባንኮች፦
- የአቢሲንያ ባንክ፣ ንብ ባንክ፣ አማራ ባንክ እና ቡና ባንክ
ከባንክ ወደቴሌብር ወኪል አካውንት ገንዘብ ለማስተላለፍ የሚከተሉትን አጭር መመሪያዎች ይከተሉ ፦
17.1. ከህብረት ባንክ ወደወኪል አካውንት ገንዘብ ለማስተላለፍ
- የህብረት ባንክ መተግበሪያ በመጠቀም ለማስተላለፍ የሚከተሉትን መመሪያዎች ይተግብሩ ፦
- የህብረት ባንክ መተግበሪያ ይክፈቱ እና የሚስጥር ቁጥርዎን ያስገቡ
- ለ”ውጪ ማስተላለፍ” (External Transfer) የሚለውን ይምረጡ
- ሞባይል ዋሌትን ይመረጡ እና ቴሌብርን ይምረጡ
- የቴሌብር አጭር ቁጥርዎን፣ የገንዘብ መጠን እና ማስታዎሻ ያስገቡ
- ያስገቡትን መረጃ በመመልከት ትክክለኛነቱን ያረጋግጡ
- ለመጨረስ የአንድ ጊዜ የማረጋገጫ ሚስጥር ቁጥር ያስገቡ
- የማረጋገጫ አጭር የጽሁፍ መልእክት ከባንኩ እና ከ127 ይደርስዎታል፡፡
የህብረት ባንክ ዩኤስኤስዲ በመጠቀም ለማስተላለፍ የሚከተሉትን መመሪያዎች ይተግብሩ ፦
- *811# በመደወል የሚስጥር ቁጥርዎን ያሰገቡ
- ገንዘብ ለማሰተላለፍ (Fund transfer)ን ይምረጡ
- ለ”ውጪ ማስተላለፍ” (External Transfer) የሚለውን ይምረጡ
- ቴሌብርን ይምረጡ
- ወደነጋዴ አካውንት የሚለውን በመምረጥ የባንክ ቁጥርዎን ይምረጡ
- የቴሌብር አጭር ቁጥርዎን፣ የገንዘብ መጠን እና ማስታዎሻ ያስገቡ
- ለመጨረስ የአንድ ጊዜ የማረጋገጫ ሚስጥር ቁጥር ያስገቡ
- ለማረጋገጥ 1ን ይላኩ ለመሰረዝ 2ን ይላኩ
- የማረጋገጫ አጭር የጽሁፍ መልእክት ከባንኩ እና ከ127 ይደርስዎታል፡፡
በባንኩ ቅርንጫፎች በኩል ለማስተላለፍ በአካል አቅራቢያዎ የሚገኝ የብርሃን ባንክ ቅርንጫፎችን ይጎብኙ፡፡
17.2. ከአማራ ባንክ ወደወኪል አካውንት ገንዘብ ለማስተላለፍ
የአማራ ባንክ ዩኤስኤስዲ በመጠቀም ለማስተላለፍ የሚከተሉትን መመሪያዎች ይተግብሩ ፦
- *690# በመደወል የሚስጥር ቁጥርዎን ያሰገቡ
- ለማሰተላለፍ (Transfer)ን ይምረጡ
- ለቴሌብር ወኪል የሚለውን ይምረጡ
- የቴሌብር አጭር ቁጥርዎን ያስገቡ
- የወኪል መረጃዎትን ይመለከቱ እና አሁን ለመክፈል 1ን ይላኩ ለመሰረዝ 2ን ያስገቡ
- የባንክ አካዎንትዎን ይምረጡ
- የሚያስተላለፉትን የገነዘብ መጠን ያስገቡ
- ለማረጋገጥ 1ን ይላኩ ፤ ለመሰረዝ 0ን ይላኩ
- የማረጋገጫ አጭር የጽሁፍ መልእክት ከባንኩ እና ከ127 ይደርስዎታል፡፡
በባንኩ ቅርንጫፎች በኩል ለማስተላለፍ በአካል አቅራቢያዎ የሚገኝ የአማራ ባንክ ቅርንጫፎችን ይጎብኙ፡፡
17.3. ከብርሃን ባንክ ወደወኪል አካውንት ገንዘብ ለማስተላለፍ
- የብርሃን ባንክ መተግበሪያ በመጠቀም ለማስተላለፍ የሚከተሉትን መመሪያዎች ይተግብሩ ፦
- የባንክ መተግበሪያውን ይክፈቱ እና የሚስጥር ቁጥርዎን ያስገቡ
- የአካውንት አገልግሎትን (Account Service) ይምረጡ
- ገንዘብ ለማስተላለፍ (Fund Transfer)ን ይምረጡ
- የማስተላለፊያ አይነት ዝርዝር ውስጥ ወደቴሌብር ማስተር ኤጀንት/ኤጀንት/መርቻንት/ተቋምን ይምረጡ
- በገንዘብ ማስተላለፍ ስር የቴሌብር አጭር ቁጥርዎን እና የገንዘብ መጠን ያስገቡ
- ተቀናሽ የሚሆንበትን የባንክ አካውንትዎን ይምረጡ
- ለመጨረስ የሚስጥር ቁጥርዎን በማስገባት ያረጋግጡ
- የማረጋገጫ አጭር የጽሁፍ መልእክት ከባንኩ እና ከ127 ይደርስዎታል፡፡
የብርሃን ባንክ ዩኤስኤስዲ በመጠቀም ለማስተላለፍ የሚከተሉትን መመሪያዎች ይተግብሩ ፦
- *881# በመደወል የሚስጥር ቁጥርዎን ያሰገቡ
- የቴሌብር አገልግሎትን ይምረጡ
- ወደኤጀንት ለማስተላለፍ የሚለውን ይምረጡ
- የባንክ አካውንትዎን ይምረጡ
- የቴሌብር አጭር ቁጥርዎን ያስገቡ
- የገንዘብ መጠን ያስገቡ በመቀጠል የሚስጥር ቁጥርዎን ያስገቡ
- ለማረጋገጥ 1ን ይላኩ ለመሰረዝ 0ን ይላኩ
- የማረጋገጫ አጭር የጽሁፍ መልእክት ከባንኩ እና ከ127 ይደርስዎታል፡፡
በባንኩ ቅርንጫፎች በኩል ለማስተላለፍ በአካል አቅራቢያዎ የሚገኝ የብርሃን ባንክ ቅርንጫፎችን ይጎብኙ፡፡
17.4. ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደወኪል አካውንት ገንዘብ ለማስተላለፍ
- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መተግበሪያ በመጠቀም ለማስተላለፍ የሚከተሉትን መመሪያዎች ይተግብሩ ፦
- የባንክ መተግበሪያውን ይክፈቱ እና የሚስጥር ቁጥርዎን ያስገቡ
- ገንዘብ ለማስተላለፍ (Transfer)ን ይምረጡ
- ለቴሌብር ኤጀንት ገንዘብ ለማስተላለፍን ይምረጡ
- የቴሌብር አጭር ቁጥርዎን ያስገቡ
- ተቀናሽ የሚሆንበትን የባንክ አካውንትዎን ይምረጡ
- የገንዘብ መጠን ያስገቡ
- የማረጋገጫ መልዕክቱን በማየት ይቀጥሉ
- የማረጋገጫ አጭር የጽሁፍ መልእክት ከባንኩ እና ከ127 ይደርስዎታል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዩኤስኤስዲ በመጠቀም ለማስተላለፍ የሚከተሉትን መመሪያዎች ይተግብሩ ፦
- *889# በመደወል የሚስጥር ቁጥርዎን ያሰገቡ
- የሚስጥር ቁጥርዎን ያስገቡ
- ወደቴሌብር ኤጀንት ለማስተላለፍ የሚለውን ይምረጡ
- የቴሌብር አጭር ቁጥርዎን ያስገቡ
- መረጃዎን በመመልከት የገንዘብ መጠን ያስገቡ
- ለማረጋገጥ ማንኛውንም ቁልፍ ከ1 እና 2 ውጪ ይላኩ
- ለማረጋገጥ 1ን ይላኩ ለመሰረዝ 2ን ይጫኑ
- የማረጋገጫ አጭር የጽሁፍ መልእክት ከባንኩ እና ከ127 ይደርስዎታል፡፡
በባንኩ ቅርንጫፎች በኩል ለማስተላለፍ በአካል አቅራቢያዎ የሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎችን ይጎብኙ፡፡