የድርጅት የስልክ ጥሪ መለያ ድርጅቶች በሰራተኞቻቸው ወይም የሚመለከታቸው አጋሮች ሞባይል ላይ ስለምርት እና አገልግሎታቸው እንዲሁም ብራንዳቸውን በአዲስ መንገድ ለማስተዋወቅ የሚረዳ አገልግሎት ነው፡፡ ድርጅቱ የራሱን መልዕክት በማዘጋጀት የጥሪ መለያ የሚጠቀሙ ሰራተኞች/አጋሮች ጥሪ በሚቀበሉበት ወይም በሚደውሉበት ወቅት ለሌሎች ደንበኞች የፅሁፍ መልዕክት በሞባይል ስክሪን ላይ የሚታይበት አገልግሎት ነው፡፡ የአገልግሎት ዋጋ የድርጅት ጥሪ መለያ ጥቅል ዓይነትወርሃዊ (ለ30 ቀናት) ዓመታዊ (ለ12 ወራት) ዋጋ በብርዋጋ በብር  የድርጅት ጥሪ መለያ ጥቅል 203801,900  የድርጅት ጥሪ መለያ ጥቅል 509004,500  የድርጅት ጥሪ መለያ ጥቅል 1001,7008,500  የድርጅት ጥሪ መለያ ጥቅል 3004,80024,000  የድርጅት ጥሪ መለያ ጥቅል 50,0007,50037,500 ደንብና ሁኔታዎች የድርጅት ደንበኞች ለአገልግሎቱ ለማመልከት አቅራቢያቸው የሚገኝ የኢት ቴሌኮም የድርጅት አገልግሎት መስጫ ማዕከል በአካል መምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የወርሃዊ ጥሪ መለያ ተጠቃሚ ድርጅቶች የአገልግሎት ክፍያቸውን በወርሃዊ ቢል እንዲከፈሉ የሚደረግ ይሆናል፡፡ ዓመታዊ የጥሪ ፊርማ ለመጠቀም የሚፈልጉ ድርጅቶች የጥቅሉን ቅድመ ክፍያ በምዝገባ ወቅት መክፈል ይጠበቅባቸዋል፡፡ ድርጅቶች የሚጠቀሙትን የጥሪ መለያ ጥቅል ለማሳደግ፣ ዝቅ ለማድረግ እንዲሁም አገልግሎቱን ለመሰረዝ ሲፈልጉ አቅራቢያቸው ያለ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል መጎብኘት የሚጠበቅባቸው ሲሆን ጥያቄያቸው የሚተገበረው በቀጣይ የድርጅቱ የቢል ወቅት ይሆናል፡፡ አንድ አባል ለአንድ የጥሪ መለያ አካውንት ብቻ መካተት የሚችል ሲሆን አዲስ የጥሪ መለያ አካውንት በአባልነት የሚካተት ከሆነ ቀድሞ ከነበረበት የሚሰረዝ ይሆናል፡፡ ድርጅቱ እንደሚጠቀምበት የጥሪ መለያ ጥቅል ዓይነት ከተፈቀደለት ከፍተኛ የአባላት መጠን በላይ ማካተት የማይችል ሲሆን ነገር ግን ቀድሞ የነበሩትን አባላት በመሰረዝ አዲስ የሚካተቱ አባላትን ማስገባት ይችላል፡፡ በድርጅቱ የተወከለ የጥሪ መለያ አስተዳዳሪ የድርጅት ጥሪ መለያ፣ የቡድን ጥሪ መለያ እና የአባል ጥሪ መለያ መወሰን ይችላል፡፡ የጥሪ መለያ ሲዘጋጅ ያልተገቡ ቃላትን ማስገባት የማይቻል ሲሆን እንዲህ ዓይነት ቃላቶች በሲስተም የሚለዩ እና የሚከለከሉ ይሆናሉ፡፡ ተጠቃሚው ድርጅት የጥሪ ማሳመሪያ የሚያስተዳድርለት ባለሞያ በራሱ ሲኖረው ባለሞያው አባላትን የማካተት/የመሰረዝ፣ ቡድኖችን የመፍጠር/የመሰረዝ፣ መለያዎችን የማዘጋጀት እና የሂሳብ ዝርዝር መመልከት ይችላል፡፡