ረዘም ላለ ጊዜ ሳይጠቀሙበት ቀርተው ጥሪ ማድረግ እና መቀበል የማይችል ባለገመድ ስልክዎን አገልግሎቱን በነፃ በማስቀጠል ለተከታታይ 6 ወራት የሚከፋፈል 600 ደቂቃዎችን ወደ መደበኛ ስልክ እንዲሁም 120 ደቂቃዎችን ወደ ሞባይል ነፃ ጥሪ ማድረግ የሚያስችሎትን ስጦታ ያግኙ፡፡
ደንብና ሁኔታዎች
- የመደበኛ ባለገመድ ስልክዎን ለአገልግሎት በድጋሜ ለማስጀመር አቅራቢያዎ የሚገኝ የኢትዮ ቴሌኮም የአገልግሎት ማዕከልን ይጎብኙ፡፡
- አዲስ የባለገመድ መደበኛ ስልክ ቀፎ ለመግዛት 160 ብር የሚከፍሉ ሲሆን የተበላሸ የስልክ ቀፎ ካሎት 100 ብር ብቻ በመክፈል በአዲስ ቀፎ መቀየር ይችላሉ፡፡
- አገልግሎቱ ሲቀጠል የሚቀርቡት ነፃ የጥሪ ደቂቃዎች ከመለቀቃቸው በፊት ያልተከፈለ የአገልግሎት ሂሳብ (ቢል) ካለ በአንድ ጊዜ ወይም በየወሩ መከፈል ይኖርበታል፡፡
- ያልተጠቀሙበት ነፃ የጥሪ ደቂቃዎች የአገልግሎት ጊዜያቸው ካለፈ በኋላ የማያገለግሉ ሲሆን ወደ ሶስተኛ ወገንም መተላለፍ አይችሉም፡፡
- አገልግሎቱ ካስቀጠሉ በኋላ ሂሳብ ባለመክፈል የሚቋረጥ ከሆነ ያልከፈሉበት ወር ነፃ የጥሪ ደቂቃዎች የማይለቀቁ ሲሆን በድጋሜ ሂሳብዎን ከፍለው የሚያስቀጥሉ ከሆነ ስጦታዎቹም በድጋሜ የሚቀርቡ ይሆናል፡፡