- በማንኛውም ቅድመ ክፍያ፣ ድህረ ክፍያ እንዲሁም ሀይብሪድ ሞባይል ቁጥራቸውን በመጠቀም ጥቅል የገዙ ደንበኞች በሙሉ አገልግሎቱን ለመጠቀም ብቁ ናቸው፡፡
- የግለሰብ ቅድመ/ድህረ ክፍያ ወይም ሀይብሪድ ሞባይል ደንበኞች ካላቸው የጥቅል ቀሪ ሀብት ላይ ለግለሰብ ወይም የድርጅት ቅድመ/ድህረ ክፍያ ወይም ሀይብሪድ ሞባይል ተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ይችላሉ፡፡
- ደንበኞች የጥቅል ሀብታቸውን ወደ ሌሎች ሲያስተላልፉ የአገልግሎት ክፍያ 12 ሣንቲም ለአንድ ጊዜ መላኪያ የሚከፍሉ ይሆናል፡፡
- የድርጅት ደንበኞች ሲላክላቸው መቀበል የሚችሉ ሲሆን ነገር ግን ወደ ሌሎች ያላቸውን ቀሪ ጥቅል ማጋራት አይችሉም፡፡
- የኢትዮ ቴሌኮም ሠራተኛ የሆነ ደንበኛ ድርጅቱ ከሰጠው ጥቅማ ጥቅም ላይ ለሌሎች ደንበኞች ማጋራት የማይችል ሲሆን ነገር ግን ከሌሎች መቀበል ይችላል፡፡
- ደንበኞች የገዙት የሞባይል ጥቅል ከ24 ሰዓት በላይ የአገልግሎት ጊዜ ካለው ለሌሎች ለማጋራት ይችላሉ፡፡
- የሚተላለፈው የጥቅል ሀብት የአገልግሎት ጊዜ የዋናው/ተላላፊው ጥቅል የአገልግሎት ጊዜ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡
ምሳሌ፡ አንድ ደንበኛ የአገልግሎት ጊዜው በሚያዚያ 1 ቀን 2014 ዓ.ም የሚያበቃ ጥቅል ኖሮት ከሌሎች ቢያጋራ ተቀባዩም ደንበኛ በተመሳሳይ ሚያዚያ 1 ቀን 2014 ዓ.ም የአገልግሎት ጊዜ ማብቂያ ይኖረዋል ማለት ነው፡፡
- ደንበኞች ከሌሎች የተቀበሉትን ጥቅል መልሰው ለሌላ ደንበኛ ማጋራት ይችላሉ፡፡
- አገልግሎቱን በኢትዮ ገበታ (*999#) እንዲሁም በማይ ኢትዮቴል ሞባይል መተግበሪያ ያገኙታል፡፡
- ያልተገደበ የሞባይል ጥቅል አገልግሎት ተጠቃሚዎች ለሌሎች ጥቅላቸውን ማጋራት አይችሉም፡፡
- የመደበኛ ስልክ ተጠቃሚዎች ማንኛውንም አይነት ጥቅል መቀበል አይችልም፡፡
- ወደሌሎች ያጋሩትን ጥቅል መመለስ አይችሉም፡፡ ጥቅል ከማጋራትዎ በፊት ማረጋገጫ ሲመጣልዎት ተመልክተው መላክ ይኖርብዎታል፡፡
- ጥቅል የማጋራት አገልግሎት ለመጠቀም የላኪው እና የተቀባዩ የሞባይል ቁጥር የሚሰራ በአገልግሎት ጊዜው ያላለፈ መሆን አለበት፡፡
- የሚያጋራው ደንበኛ ጥቅል የሚልክበት በሞባይል ቁጥሩ ዝቅተኛም ቢሆን ሂሳብ ሊኖረው ይገባል፡፡
- ደንበኞች ያላቸውን የጥቅል መጠን ሙሉ በሙሉ ማስተላለፍ ይችላሉ፡፡
- የተቀባዩ ሞባይል ቁጥር በአገልግሎት ጊዜ ማለፍ ምክንያት ከተዘጋ፣ ከታገደ እንዲሁም የተቋረጠ ከሆነ ለላኪው መቀበል እንደማይችል ማሳወቂያ ይደርሰዋል፡፡
- ደንበኞች በቀን እስከተፈቀደው ገደብ ድረስ ለአንድ ተቀባይ በተደጋጋሚ ጥቅል ማጋራት ይችላሉ፡፡
- የማስታወቂያ እና የማበረታቻ ጥቅል ስጦታዎች ለሌሎች ማጋራት የሚችሉ ሲሆን ነገር ግን ከማሽን ወደ ማሽን ጥቅል እና ለመጀመሪያ ጊዜ ሞባይል ቁጥር ሲያወጡ የሚያገኙት የማበረታቻ ስጦታ ወደ ሌሎች ለማስተላለፍ አይችሉም፡፡
- ጥቅሉ በተሳካ ሁኔታ መጋራቱን የሚገልፅ መልዕክት ለተቀባዩም ለላኪውም የሚደርሳቸው ይሆናል፡፡ መልዕክቱ የጥቅሉ መጠን፣ አሁን ያለው ቀሪ መጠን፣ የአገልግሎት ጊዜ ማብቂያ እንዲሁም የላኪው ስልክ ቁጥር የያዘ ይሆናል፡፡