የወዳጅ ዘመድ ጥቅል

የወዳጅ ዘመድ ጥቅል

የራስዎን የወዳጅ እና የዘመድ ግሩፕ በመፍጠር ያሎትን ጥቅል ለሌሎች ማጋራት ይችላሉ።

Share

የድምጽ

  • 2500 ደቂቃ. የሃገር ውስጥ ጥሪ
  • ሲዩጂ ኪራይ፡ 25 ብር በወር
  • እስከ 5 አባላት
20% ቅናሽ

የዳታ

  • 20 ጊ.ባ ሞባይል ዳታ
  • ሲዩጂ ኪራይ: 25ብር በወር
  • እስከ 5 አባላት
30% ቅናሽ

ድምጽ + ዳታ

  • 2500 ደቂቃ
  • 20 ጊ.ባ ኢንተርኔት
  • ሲዩጂ ኪራይ: 25 ብር በወር
  • እስከ 5 አባላት
20% ቅናሽ

  • ሁሉም አገልግሎት የሚሰጡ የቅድመ ክፍያ፣ ድህረ ክፍያ እና ሀይብሪድ ሞባይል ተጠቃሚዎች አገልግሎቱን ለማግኘት ብቁ ናቸው፡፡
  • የመደበኛ ስልክ፣ ዳታ ብቻ ሲም፣ ከማሽን ወደማሽን እንዲሁም ሲዲኤምኤ አገልግሎት የሚጠቀሙ የወዳጅ ዘመድ ጥቅል ለመግዛት አይችሉም፡፡
  • ያልተገደበ ጥቅል ተጠቃሚዎች (የድምፅ፣ የዳታ እና የአጭር መልዕክት) አገልግሎቱን አባል ሁነው በመመዝገብ መጠቀም አይችሉም ነገር ግን መስራች ሁነው በመመዝገብ ሌሎች አባላት በማካተት ተጠቃሚ ማድረግ ይችላሉ፡፡
  • የተለያዩ የወዳጅ ዘመድ ጥቅል አይነቶች ዋና መስራች በመግዛት ለሌሎች አባላት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ይቻላል፡፡ (አስተዳዳሪው የተለያዩ የድምፅ፣ የዳታ ወይም ሁለቱንም የያዘ ጥቅል አባል ላደረጓቸው ደንበኞች ማከፋፈል ይችላሉ)፡፡
  • መስራቹ ቋሚ መሆን ሲኖርበት ከተገዛው የጥቅል መጠን ሀብት ከ 50% በላይ ለራሱ ብቻ መጠቀም አይችልም፡፡
  • የወዳጅ ዘመድ ጥቅል መስራች በማንኛውም ጊዜ የማይ ኢትዮቴል መተግበሪያን በመጠቀም ወይም በአካል በመቅረብ ቡድን መፍጠር፣ አባላትን ማካተት፣ ማስተካከያ ማድረግ እንዲሁም አባላትን መሰረዝ ይችላል፡፡ በተጨማሪም የጥቅል ሀብቱን ለቀን፣ ለሣምንት እና ለወር ከፋፍሎ መመደብ ይችላል፡፡
  • እስከተፈቀደው የአባል መጠን (5 አባላት) ድረስ ለመመዝገብ በነፃ ሲሆን ነገር ግን ከተፈቀደው በላይ አባላትን ለማስገባት በአንድ ደንበኛ 5 ብር መስራቹ የሚከፍል ይሆናል፡፡ በአንድ የወዳጅ ዘመድ ቡድን የሚፈቀደው ከፍተኛው የአባላት ብዛት መስራቹን ጨምሮ 15 ነው፡፡
  • በተጨማሪም የቡድን መስራቹ እስከ 5 አባላት ድረስ የሲዩጂ ኪራይ 25 ብር መክፈል ይጠበቅበታል፡፡
  • ለአገልግሎቱ የተመዘገበው ቁጥር ወይም የቡድኑ መስራች ለጥቅል አገልግሎቱ ወርሃዊ ኪራይ የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
  • አገልግሎቱ በየወሩ ቀጣይነት እንዲኖረው በወሩ የመጀመሪያ ቅድመ ክፍያ ከሆነ በቂ ሂሳብ እንዲሁም ድህረ ክፍያ ከሆነ በቂ ተቀማጭ ሂሳብ ሊኖረው ይገባል፡፡
  • አገልግሎቱን ለማቋረጥ የማይ ኢትዮቴል መተግበሪያ መጠቀም ወይም ወደ ሽያጭ ማዕከሎቻችን መምጣት ይችላሉ፡፡
  • ሁሉም ዋጋዎች ተ.እ.ታ ያካትታሉ፡፡
  •