ቨርቹዋል (ሆስትድ) ፒ.ቢ.ኤክስ ምንድነው?
ኢንተርኔት ፕሮቶኮልን (IP) በመጠቀም ድርጅቶች የስልክ ጥሪ የሚያስተናግዱበት አገልግሎት ነው፡፡ ቨርቹዋል ፒቢኤክስ ሶሉሽን በአገልግሎት ሰጪ ድርጅት ወይም ክላውድን በመጠቀም ሊቀርብ የሚችል ነው፡፡ ክላውድን መሰረት ያደረገ የቴሌፎን አገልግሎት ድምፅን ከኢንተርኔት ጋር ያገናኛል፤ የክላውድ ቴሌፎን ተጠቃሚ ከሆኑ ኢንተርኔት የሚያስጠቅም ማንኛውንም መገልገያ በመጠቀም ወጪ ጥሪ ማድረግ እና ጥሪ መቀበል ይችላሉ፡፡
ጥቅሞች
- ደህንነቱ በተጠበቀ የዳታ ማዕከል መሰረት አድርጎ የቀረበ አገልግሎት በመሆኑ ያልተቋረጠ አገልግሎት አለው
- ከመደበኛው የፒ.ቢ.ኤክስ አገልግሎት ጋር ሲነፃፀር ወጪ ቆጣቢ
- በኢንተርኔት የቀረበ አገልግሎት በመሆኑ የጥገና ወጪ የሌለበት
- ሰራተኞችዎ በስራ ገበታቸው፣ በጉዞ ላይ እንዲሁም በቤታቸው ውስጥ ሁነው የደንበኞችን ጥሪ እንዲቀበሉ እና እንዲያስተላልፉ ያግዛል
- የጥሪ ቅጂዎች እና ዝርዝር መረጃዎች እንዲያገኙ ስለሚረዳ በቀላሉ መረጃ መተንተን እና አፈፃፀምን መገምገም ይችላሉ
- ለአጠቃቀም ቀላል
- የእንኳን ደህና መጡ ሰላምታ፣ የድምፅ መልዕክት ወደ ኢሜል መላክ እንዲሁም ጥሪ ማስተላለፍ የሚያስችል በመሆኑ ድርጅቶች ገፅታቸውን እና የደንበኞች አገልግሎታቸውን ለማጎበት ያግዛል
መደበኛ ጥቅል
- የተጠቃሚ የጥሪ ሁኔታ
- ጥሪ ማስተላለፍ
- አይቪአር ማውጫ
- የድምፅ መልዕክት
- የጥሪ ዝረዝር መረጃ
- ጥሪ ማዘዋወር
- የጥሪ ማቆያ
- የጥሪ ፓርኪንግ
- የፍጥነት መደወያ
- ያልተገደበ ማከማቻ
- ሞባይል መተግበሪያ
- የማቆያ ሙዚቃ
ወርሃዊ ክፍያ በኤክስቴሽን፡- 200 ብር
አድቫንስድ ጥቅል
የመደበኛ ጥቅሎችን እንዲሁም
- የጥሪ ኮንፈረንስ
- ሪሰፕሽኒስት
- አይቪአር
- የጥሪ ማሰራጫ
- የጥሪ ቅጂ
- ከጥሪ በኋላ ዳሰሳ ማስሞላት
የኮል ሴንተር ጥቅል
የአድቫንስድ ጥቅሎችን እንዲሁም
- የጥሪ ማቆያ
- የማስተዳደሪያ ፖርታል
- የአድራሻ ማውጫ
- የተለያዩ ሶፍትዌሮችን፣ ገፆችን እና መተግበሪያዎን ማገናኘት
- የጥሪ ሪማይንደር
- ጥሪ መገደቢያ
- የተራዘመ የቆይታ ጊዜ
ደንብና ሁኔታ
- ለመደበኛ እና አድቫንስድ ጥቅል የሚፈቀደው አነስተኛ የፒ.ቢ.ኤክስ አገልግሎት ብዛት 5 ነው፡፡
- ለኮል ሴንተር ጥቅል የሚፈቀደው አነስተኛ የኤጀንት ብዛት 2 ነው፡፡
- ለመደበኛ ስልክ እና ሞባይል አገልግሎት የድምፅ ጥሪ መገልገያ በመደበኛው ታሪፍ መሰረት ይሆናል፡፡
- ደንበኞች እየተገለገሉበት ያለውን ቁጥር መጠቀም ወይም አዲስ የአገልግሎት ቁጥር መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- አገልግሎቱ ቪፒኤን እና የኢንተርኔት ግንኙነትን በመጠቀም የሚቀርብ ይሆናል፡፡