- ደረጃ 1 ደንበኞች
የደረጃ 1 አካውንት ደንበኞች ማስቀመጥ የሚገባቸው ከፍተኛው የገንዘብ መጠን 5,000 ብር ሲሆን፣ በቀን የተፈቀደ የገንዘብ ግብይት እንቅስቃሴ መጠን ደግሞ 1,000 ነው፡፡ በተጨማሪም አጠቃላይ ወርሃዊ የተፈቀደ የግብይት እንቅስቃሴ ሂሳብ ገደብ መጠን 10,000 ብር ነው፡፡
የምዝገባ መስፈርቶች
- የአመልካቹ ሙሉ ስም ወይም የአካውንት ስም
- የአመልካቹ የትውልድ ቦታና ቀን
- የአመልካቹ የሞባይል ቁጥር
- አመልካቹ በቅርቡ የተነሳው ፎቶ
- አመልካቹ አሁን የሚኖርበት አድራሻ
- አመልካቹ ከዚህ በፊት የቴሌብር አካውንት ባለው ሰው መተዋወቅ ወይም መቅረብ አለበት
- ደረጃ 2 ደንበኞች
የደረጃ 2 አካውንት ደንበኞች ማስቀመጥ የሚገባቸው ከፍተኛው የገንዘብ መጠን 20,000 ብር ሲሆን፣ በቀን የተፈቀደ የገንዘብ ግብይት እንቅስቃሴ መጠን ደግሞ 5,000 ነው፡፡ በተጨማሪም አጠቃላይ ወርሃዊ የተፈቀደ የግብይት እንቅስቃሴ ሂሳብ ገደብ መጠን 40,000 ብር ነው፡፡
የምዝገባ መስፈርቶች
- የአመልካቹ መታወቂያ
- የአመልካቹ ሙሉ ስም ወይም የአካውንት ስም
- የአመልካቹ የትውልድ ቦታና ቀን
- የአመልካቹ የሞባይል ቁጥር
- አመልካቹ በቅርቡ የተነሳው ፎቶ
- አመልካቹ አሁን የሚኖርበት አድራሻ
- ደረጃ 3 ደንበኞች
የደረጃ 3 አካውንት ደንበኞች ማስቀመጥ የሚገባቸው ከፍተኛው የገንዘብ መጠን 30,000 ብር ሲሆን፣ በቀን የተፈቀደ የገንዘብ ግብይት እንቅስቃሴ መጠን ደግሞ 8,000 ነው፡፡ በተጨማሪም አጠቃላይ ወርሃዊ የተፈቀደ የግብይት እንቅስቃሴ ሂሳብ ገደብ መጠን 60,000 ብር ነው፡፡
የምዝገባ መስፈርቶች
- የአካውንቱ ባለቤት መታወቂያ
- የአመልካቹ ሙሉ ስም ወይም የአካውንት ስም
- የአመልካቹ የትውልድ ቀን
- የአመልካቹ የሞባይል ቁጥር
- አመልካቹ በቅርቡ የተነሳው ፎቶ
- አመልካቹ አሁን የሚኖርበት አድራሻ