ቴሌብር ሳንዱቅ (ቁጠባ)

ደንበኞች በተሻለ የወለድ መጠን ወይም ያለወለድ መቆጠብ የሚችሉበት የቁጠባ አገልግሎት ዓይነት ነው።

ወለድ የሚታሰብበት ቁጠባ

ይህ አገልግሎት ደንበኛው ወለድ ሊያስገኝለት የሚችል ማንኛውም አይነት መጠን ያለው ገንዘብ በማንኛውም ጊዜ እና ቦታ ተቀማጭ የሚያደርግበት የቁጠባ አገልግሎት ነው፡፡ ደንበኛው ቁጠባውን በወለድ አገልግሎት ካስጀመረ እንደ ተቀማጭ ሂሳቡ የቆይታ ጊዜ ገደብ ወለድ የሚሰላበት ይሆናል፡፡

ወለድ የማይታሰብበት የቁጠባ

ወለድ የማይታሰብበት የቁጠባ አይነት ነው፡፡ ደንበኛው በማንኛውም ጊዜ ገንዘብ መቆጠብ እና ወጪ ማድረግ ይችላል፡፡

የገንዘብ ማስቀመጫ አማራጭ አይነቶች

1. በደንበኛው ፍላጎት ላይ የተመሠረተ ቁጠባ

  • ይህ የቁጠባ አይነት ደንበኛው በማንኛውም ጊዜ ማንኛውንም የገንዘብ መጠን መቆጠብ እንዲሁ በማንኛውም ጊዜ ወጪ ማድረግ የሚያስችል አገልግሎት ነው፡፡
  • የተቀማጭ ገንቡ የወለድ መጠን በዓመት 7 በመቶ ይሆናል፡፡

2. ዝግ ቁጠባ

  • ደንበኛው መጠኑ የታወቀ ገንዘብ በተወሰነ የቆይታ ጊዜ ገደብ ለመቆጠብ የሚያስችል አገልግሎት ሲሆን፣ ነገር ግን ደንበኛው ገንዘቡን ከጊዜ ገደቡ በፊት ወጪ ማድረግ አይችልም፡፡
  • የተቀማጭ ገንዘቡ የወለድ መጠን በዓመት 8 በመቶ ይሆናል፡፡

3. ቋሚ ቁጠባ

  • ደንበኞች በቋሚነት በተወሰነ የጊዜ እና የገንዘብ መጠን ተቀማጭ የሚያደርግበት የአገልግሎት አይነት ሲሆን፣ የተቀማጭ ገንዘቡ የወለድ መጠን በዓመት 7.5 በመቶ ይሆናል፡፡
  • ደንበኛው 500 ብር እና ከዚያ በላይ መቆጠብ ወይም ተቀማጭ ማድረግ ይችላል፡፡

• 18 አመት እና ከዚያ በላይ
• አገልግሎት የሚሰጥ የኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርድ መያዝ
• የቴሌብር እና የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቶችን እንደ ዳታ/ድምጽ/አጭር የጽሁፍ መልዕክት የሚጠቀሙ
• ለመመዝገብ በዩኤስኤስዲ(*127#) ወይም በቴሌብር መተግበሪያ መጠቀም ይችላሉ፡፡

በቴሌብር
የሞባይል መተግበሪያ
እንዴት አገልግሎቱን ማስጀመር እና መጠቀም እንችላለን?

አገልግሎቱን ለማስጀመር

  • የፋይናንስ አገልግሎት የሚለውን ይጫኑ
  • ቴሌብር ሳንዱቅ የሚለውን ይምረጡ
  • ደንብ እና ሁኔታዎችን በማንበብ የ √ ምልክት በመጫን መስማማትዎን ይግለጹ
  • ለማስጀመር የሚለውን ይጫኑ
  • የሚፈልጉትን ዓመታዊ የወለድ ምጣኔ በመምረጥ፣ ለማስጀመር የሚለውን ይጫኑ

ገንዘብ ለማስቀመጥ

  • ቴሌብር ሳንዱቅ ከሚለው ስር ቴሌብር ሳንዱቅ የሚለውን ይጫኑ
  • ተቀማጭ የሚለውን ይጫኑ
  • የሚያስቀምጡትን የገንዘብ መጠን በማስገባት ተቀማጭ የሚለውን ይጫኑ

ገንዘብ ወጪ ለማድረግ

  • ቴሌብር ሳንዱቅ ከሚለው ስር ቴሌብር ሳንዱቅ የሚለውን ይጫኑ
  • ለማውጣት የሚለውን ይምረጡ
  • የወጪ ገንዘብ መጠን በማስገባት ወጪ የሚለውን ጫኑ

1. የውል ስምምነት

    • ይህ ስምምነት (ከዚህ በኋላ "ደንቦች እና ሁኔታዎች" የሚባል) የቴሌብር መላ የክሬዲት አገልግሎትን በተመለከተ አጠቃላይ ደንብ እና ሁኔታዎች ያካትታል፡፡
    • እነዚህ ደንቦችና ሁኔታዎች እንዲሁም ከዚህ ጋር የተያያዙ ማሻሻያዎች እና ለውጦች ይህ በጽሁፍ ከታተመበት ጊዜ አንስቶ ሥራ ላይ ይውላሉ፡፡

2. ትርጓሜ

በዚህ የደንቦች እና ሁኔታዎች መረጃ ውስጥ የተዘረዘሩ ቃላት እና አባባሎች የሚከተለውን ትርጉሜ ይይዛሉ፡-

    • "የቴሌብር መላ የክሬዲት አገልግሎት" ማለት ለግለሰብ እና ለነጋዴዎች/ወኪሎች አነስተኛ ንግድ/ቢዝነስ እንዲጀምሩ ወይም እንዲያስፋፉ በኤሌክትሮኒክ ገንዘብ አነስተኛ መጠን ያለው ክሬዲት የሚያገኙበት የአገልግሎት አይነት ነው።
    • “የክሬዲት አገልግሎት” ማለት ከታች በተቀመጡ ደንብ እና ሁኔታዎች መሰረት በኢትዮ ቴሌኮም ለደንበኞች የሚቀርብ የክሬዲት አገልግሎት ነው፡፡
    • “ደንበኛ” ማለት በስሙ አነስተኛ የቁጠባ አካውንት ያለው የቴሌብር ደንበኛ ነው።
    • "አንተ" "አንቺ" ወይም "የአንተ" ማለት ደንበኛውን ለማለት ነው።
    • “ኢ-ገንዘብ” ማለት እኩል መጠን ያለው ጥሬ ገንዘብን የሚወክል ደንበኛው የሚመለከተው የቴሌብር የኤሌክትሮኒክስ የገንዘብ ዋጋ ነው።
    • "ዋና መጠን" ማለት መጀመሪያ እንደመነሻ ከኢትዮ ቴሌኮም የተወሰደ የክሬዲት መጠን ነው፡፡
    • “ደንበኛ” ማለት በስሙ በቴሌብር አካውንት የቴሌብር መላ ለክሬዲት አገልግሎት የተመዘገበ የቴሌብር ተመዝጋቢ ማለት ነው።
    • "አንተ" "አንቺ" ወይም "የአንተ" ማለት ደንበኛውን ለማለት ነው።
    • “ኢ-ገንዘብ” ማለት ከጥሬ ገንዘብ እኩል መጠን ያለው የቴሌብር የኤሌክትሮኒክስ ገንዘብ ማለት ነው።
    • "ዋና ገንዘብ" ማለት በክሬዲት መልክ ልተበዳሪ ደንበኞች የተሰጠ የገንዘብ መጠን ማለት ነው።
    • “የአገልግሎት ክፍያ” ማለት የክሬዲት ክፍያ አገልግሎትን ለመጠቀም በደንበኞች የሚከፈል የክፍያ መጠን ነው።
    • "የቅጣት ክፍያ" ማለት ለክሬዲት የመጨረሻ መክፍያ ቀነ ገደቡ አልፎ ክፍያው ሲፈጸም የሚከፍል ተጨማሪ የክፍያ መጠን ነው፡፡
    • "የመጨረሻ ክፍያ ቀን" ማለት የክሬዲት መመለሻ የጊዜ ገደብ (ገባሪ የክሬዲት ጊዜ) ያላለፈ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን ክሬዲት ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ 30 ቀናትን የሚያካትት ነው፡፡
    • "ቀነ ገደቡ ያለፈ" ማለት የክሬዲት መመለሻ ቀነ ገደቡ ያለፈ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
    • "የተበላሸ ብድር" ማለት ክሬዲት ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በ90 ቀናት ውስጥ ያልተከፈለ ክሬዲት ሲሆን በወቅቱ ባለመመለሱ እንደ ተበላሸ ብድር መሆኑን የሚያሳይ ጊዜ ነው፡፡

3. ደንብ እና ሁኔታዎችን ስለመቀበል

    • የቴሌብር መላ የክሬዲት አገልግሎትን ለመጠቀም ከማመልከትዎ በፊት እነዚህን ደንብ እና ሁኔታዎች በጥንቃቄ በማንበብ የክሬዲት አጠቃቀም እና መመሪያን አንብበው ይስማሙ፡፡
    • በእነዚህ ደንቦችና ሁኔታዎች ካልተስማሙ እባክዎን ከዝርዝር መምረጫ ውስጥ ሰርዝ የሚለውን ይጫኑ፤
    • ደንቦችና ሁኔታዎችን እንዳነበቡ፣ እንደተረዱና እንደተቀበሉ የሚቆጠረው፡-
    • “ይስማሙ” የሚለውን አማራጭ ሲጫኑ ደንብ እና ሁኔታዎችን በማንበብ ተረድተው ለማክበር መስማማትዎን እንዳረጋግጡ ወይም ክሬዲት ክፍያን ለመጠቀም እንደተስማሙ ይወሰዳል።
    • ደንብ እና ሁኔታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በኢትዮ ቴሌኮም ሊሻሻሉ ወይም ሊለወጡ የሚችሉ ሲሆን ከታወቀበት ዕለት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል፡፡
    • የክሬዲት ክፍያ አገልግሎትን በኤሌክትሮኒካዊ መንገድ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ለመተግበር እና የክሬዲት ክፍያ አገልግሎትን በኤሌክትሮኒካዊ መንገድ በቴሌብር ሲስተም ለመጠቀም ተስማምተዋል።

4. የክሬዲት አገልግሎትን ለማስጀመር

የክሬዲት አገልግሎትን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ለማስጀመር ቢያንስ፡-

    • 18 አመት እና ከዚያ በላይ
    • አገልግሎት የሚሰጥ የኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርድ መያዝ
    • የቴሌብር እና የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቶችን እንደ ዳታ/ድምጽ/አጭር የጽሁፍ መልዕክት የሚጠቀሙ
    • የቴሌብር የደንበኝነት ቆይታ 3 ወር እና ከዛ በላይ መሆን አለበት
    • ለመመዝገብ በዩኤስኤስዲ(*127#) ወይም በቴሌብር መተግበሪያ መጠቀም ይችላሉ፡፡
    • ለተሳካ ምዝገባ የማሳወቂያ አጭር የፅሁፍ መልዕክት ይደርስዎታል፡፡

5. የቴሌብር መላ የክሬዲት አገልግሎት ለማግኘት መሰረታዊ መስፈርቶች

    • የደንበኛ የመበደር አቅም ደንበኛው ባደረገው የ6 ወር የቴሌብር የገንዘብ እንቅስቃሴ እና በቴሌኮም አጠቃቀም ይወሰናል። ከታች ያሉት የቴሌብር ግብይቶች እና የገንዘብ ልውውጥ  የደንበኛ የበደር አቅምን ለማስላት ይውላሉ።
    • ለእርስዎ ወይም ለስጦታ የአየር ሰዓት መሙላት ወይም ጥቅል መግዛት (በራስ አገዝ ወይመ ከወኪሎች)
    • ዕቃ ወይም አገልግሎት በመግዛት ግብይት መፈጸም
    • ለእርስዎ ወይም የሌላ ደንበኛ ቢል ክፍያ (በራስ አገዝ ወይም ከወኪሎች)
    • ለእርስዎ ወይም የሌላ ደንበኛ የፍጆታ አገልግሎት ክፍያ (በራስ አገዝ ወይም ከወኪሎች)
    • ከውጭ አገር ገንዘብ መቀበል
    • የጅምላ ክፍያ (ደሞዝ፣ ሴፍቲኔት…)
    • የትኬት ክፍያ
    • ለገንዘብ ማሰባሰቢያ የእርዳታ ክፍያ
    • የቁጠባ አገልግሎት
    • የቴሌኮም ፍጆታ (ድምጽ፣ ዳታ ወይም መልዕክት)
    • ብቁ ለመሆን ደንበኞች ከቴሌኮም አገልግሎት ፍጆታ በተጨማሪ የቴሌብር አገልግሎት መጠቀም አለባቸው፡፡

6. የክሬዲት መጠን እና ክፍያ

    • በሚፈቀደው ዝቅተኛ እና ከፍተኛ የክሬዲት መጠን መካከል ማንኛውንም መጠን መበደር ይችላሉ።
    • የጠየቁትን የብድር መጠን እንዳገኙ በዋናው የቴሌብር ሂሳብዎ (ኤሌክትሮኒክ-ገንዘብ አካውንት) ላይ ገቢ ይደረጋል።
    • ሌላ ክሬዲት ለማግኘት መጀመሪያ ቀድመው የወሰዱትን ክሬዲት መክፈል ይጠበቅብዎታል፡፡
    • ያለብዎትን ክሬዲት በከፊል ወይም በሙሉ መክፈል ይችላሉ።
    • የክሬዲት መክፈያ ማብቂያ ቀነ ገደብ በ30 ቀናት ውስጥ ይሆናል።
    • ያለብዎትን ክሬዲት በ30 ቀናት ውስጥ ከከፈሉ 10% የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላሉ፡፡
    • ከ30 ቀን በኋላ ለሚከፍሉ በቀን5% በመቶ የቅጣት ክፍያ እንዲከፍሉ ታሳቢ ይደረጋል።
    • ከ30 ቀናት በኋላ ያልተመለሰ ክሬዲት መጠን ከቴሌብር ሂሳብ ወዲያውኑ ተቀናሽ ይደረጋል፡፡
    • በጉርሻ የሚያገኙት ገንዘብ ለክሬዲት ክፍያ አይውልም፡፡
    • ይህ የክሬዲት አገልግሎት የሚሰጠው ኢትዮ ቴሌኮም ከዳሸን ባንክ ጋር በመተባበር ነው፡፡ ለክሬዲት አገልግሎት የሚውለውን ገንዘብ የሚያቀርበው ዳሸን ባንክ ሲሆን ይህን ገንዘብ በባለቤትነት የሚቆጣጠረው ዳሸን ባንክ ነው፡፡ የተበላሼ ብድር በሚከሰትበት ጊዜ ባንኩ ጉዳዩን ወደ መደበኛ ፍርድቤት የመውሰድና የመክሰስ ሙሉ መብት አለው፡፡