በቴሌብር ይክፈሉ

በማንኛውም ቦታ እና ጊዜ ቴሌብርን በመጠቀም የኢትዮ ቴሌኮም ሂሳብዎን (bill) ለመክፈል ወይም ትኬቶችን ለመግዛት (ለምሳሌ፡- አንድነት ፓርክ) በጣም አመቺ ነው።

 

የቴሌብር አካውንትዎን በመጠቀም የተለያዩ የድርጅት የአገልግሎት ክፍያዎችን በቀላሉ በማንኛውም ጊዜና በየትኛውም ቦታ ሆነው ለመክፈል ቀላል አማራጭ ነው፡፡ በተለይም የውኃ፣ የመብራ፣ የጋዝ፣ የኢንሹራንስ እና የትምህርት ክፍያዎችን  በቀላሉ ለመክፈል ያስችሎታል።

የቴሌብር አካውንትዎን በመጠቀም የተለያዩ የድርጅት የአገልግሎት ክፍያዎችን በቀላሉ በማንኛውም ጊዜና በየትኛውም ቦታ ሆነው ለመክፈል ቀላል አማራጭ ነው፡፡ በተለይም የውኃ፣ የመብራ፣ የጋዝ፣ የኢንሹራንስ እና የትምህርት ክፍያዎችን  በቀላሉ ለመክፈል ያስችሎታል።

በቴሌብር ክፍያዎን እንዴት መፈጸም ይችላሉ?

የቴሌኮም ቢል መክፈል
  • ከሜኑ ውስጥ "ክፍያን ይክፈሉ" የሚለውን ይምረጡ።
  • «ለራስ»ን ይምረጡ ወይም
    • "ለሌላ" (ለሌላ ሰው) የተቀባዩን ስልክ ቁጥር አስገባ/ ምረጥ
  • ለመክፈል የሚፈልጉትን መጠን ይምረጡ/አስገቡ።
  • ፒን ያስገቡ ግብይቱን ያረጋግጡ
የአንድነት ፓርክ ትኬት መግዛት
  • ከሜኑ ውስጥ "ትኬት ይግዙ" የሚለውን አማራጭ ይምረጡ
  • የቲኬት አይነት ይምረጡ
  • የቲኬቶችን ቁጥር ያስገቡ
  • የመግቢያ ቀን እና ሰዓት ያስገቡ
  • ለማረጋገጥ ፒን ያስገቡ
የዲ ኤስ ቲቪ ክፍያ መክፈል

በቴሌቢር መተግበሪያ፡-

  • ወደ ቴሌብር መተግበሪያ መነሻ ገጽ ይሂዱ እና ክፍያን በቴሌቢር ይምረጡ
  • የፍጆታ ክፍያን ይምረጡ
  • ለመዝናኛ ክፍያን ይምረጡ
  • ክፍያዎን ለመፈጸም የስማርትካርድ ቁጥር ያስገቡ እና
  • መመሪያዎቹን ይከተሉ።
የፓስፖርት አገልግሎት ክፍያ
  • በቴሌብር መተግበሪያ፡
  1. በቴሌብር ይክፈሉ የሚለውን ይጫኑ
  2. የአገልግሎት ክፍያ የሚለውን ይምረጡ
  3. የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ የሚለውን ይጫኑ
  4. የማጣቀሻ ቁጥር ያስገቡ እና ቀጣይ የሚለውን ይጫኑ
  5. የሚስጥር ቁጥር ያስገቡ፣ይጨርሱ እና ያረጋግጡ የሚለውን ይጫኑ

ማስታወሻ፡ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ድረ-ገጽ በመግባት ሲመዘገቡ በሚደርስዎ የክፍያ ማጣቀሻ ቁጥር ክፍያዎን በቴሌብር በቀላሉ ይክፈሉ

  • በአጭር ቁጥር (*127)፡
  1. *127# ይደውሉ
  2. # በማስገባት ወደ ቀጣይ መውጫ ይሂዱ
  3. 7ን በቴሌብር ይክፈሉ የሚለውን ይጫኑ
  4. 2ን የአገልግሎት ሂሳብ ክፍያ የሚለውን ይምረጡ
  5. 1ን በድርጅት ስም የሚለውን ይምረጡ
  6. 8ን ይምረጡ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የሚለውን ይምረጡ
  7. የክፍያ ማጣቀሻ ቁጥር ያስገቡ
  8. የሚስጥር ቁጥርዎን በማስገባት ለማረጋገጥ 1ን ይጫኑ እና  አጭር የጽሁፍ መልእክት ይደርስዎታል

ማስታወሻ፡ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ድረ-ገጽ በመግባት ሲመዘገቡ በሚደርስዎ የክፍያ ማጣቀሻ ቁጥር ክፍያዎን በቴሌብር በቀላሉ ይክፈሉ

የአድማስ ዲጂታል ሎተሪን በቴሌብር እና በአጭር ቁጥር 605 ይግዙ
  • የአድማስ ዲጂታል ሎተሪን በቴሌብር *127# እና በአጭር ቁጥር 605 ይግዙ
  1. *127# ይደውሉ
  2. # በማስገባት ወደ ቀጣይ ይሂዱ
  3. 7 ቁጥርን (ብሔራዊ ሎተሪ) ይምረጡ
  4. 1ቁጥርን (አድማስ ሎተሪ ብር 3) ይምረጡ
  5. ለማረጋገጥ 1 ቁጥርን ያስገቡ
  6. የሚስጥር ቁጥርዎን በማስገባት ክፍያዎን ይፈጽሙ (የማረጋገጫ አጭር የፅሁፍ መልዕክት ይደርስዎታል)

ማስታወሻ፡-

  • ክፍያውን እንዳጠናቀቁ ማረጋገጫ መልዕክት ከ127 እንዲሁም የሎተሪ ቲኬት ቁጥርዎ ከ605 የደርስዎታል ፡፡
  • እድልዎን ለማስፋት ከአንድ በላይ ሎተሪ መግዛት ይችላሉ፡፡

በአጭር መልዕክት የደረስዎትን የሎተሪ ቁጥርዎን በጥንቃቄ ያኑሩ

አመታዊ የግብር ክፍያዎን በቴሌብር ይክፈሉ
  • አመታዊ የግብር ክፍያዎን ባሉበት ቦታ ሆነው በቀላሉ በቴሌብር መተግበሪያ ይክፈሉ
  1. በቴሌብር ለመክፈል የሚለውን ይምረጡ
  2. የአገልግሎት ክፍያ የሚለውን ይምረጡ
  3. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የሚለውን ይምረጡ
  4. የክፍያ ማዘዣ ቁጥር በማስገባት ይቀጥል የሚለውን ይጫኑ
  5. የክፍያ ዝርዝር መረጃዎችን በማረጋገጥ ይቀጥል የሚለውን ይጫኑ
  6. የሚስጥር ቁጥርዎን በማስገባት ክፍያዎን ይፈጽሙ (የማረጋገጫ አጭር የፅሁፍ መልዕክት ይደርስዎታል)
  • አመታዊ የግብር ክፍያዎትን በቀላሉ በቴሌብር ይክፈሉ (*127#)
  1. *127# ይደውሉ
  2. 4 ቁጥርን ይምረጡ (ለግብር ክፍያ)
  3. 1 ቁጥርን ይምረጡ (አዲስ አበባ)
  4. የክፍያ ማዘዣ ቁጥርዎን ያስገቡ፣
  5. የክፍያ ዝርዝር መረጃዎን በማየት ለማረጋገጥ 1 ቁጥርን ያስገቡ፣
  6. የክፍያ ምክንያት ያስገቡ፣
  7. የሚስጥር ቁጥርዎን በማስገባት ክፍያዎን ይፈጽሙ (የማረጋገጫ አጭር የፅሁፍ መልዕክት ይደርስዎታል)
የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያ መክፈል

በቴሌብር መተግበሪያ፡-

  • ወደ ቴሌብር መተግበሪያ መነሻ ገጽ ይሂዱ እና ክፍያን በቴሌቢር ይምረጡ
  • የፍጆታ ክፍያን ይምረጡ
  • የኤሌክትሪክ መገልገያ ክፍያን ይምረጡ
  • የእርስዎን የኮንትራት መለያ ቁጥር ያስገቡ።
  • ስምዎን እና ውልዎን ያረጋግጡ።
  • አይ. ክፍያውን ለመፍታት የእርስዎን ፒን ቁጥር ያስገቡ እና
  • መመሪያዎቹን ይከተሉ

በ*127#፡

  • *127# መደወል
  • ወደ ቀጣዩ ሜኑ ለመቀጠል # ያስገቡ 
  • በቴሌብር መክፈልን ለመምረጥ 7 ያስገቡ
  • የፍጆታ ክፍያ ክፍያን ለመምረጥ 2 ያስገቡ
  • በUtility Company ለመምረጥ 1 ይምረጡ
  • የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትን ለመምረጥ 1 ያስገቡ
  • የኮንትራት መለያ ቁጥርዎን ያስገቡ ለማረጋገጥ 1 ያስገቡ
  • ምክንያት ያስገቡ
  • በመጨረስ ፒንዎን ያስገቡ
ወርሃዊ የውሃ አገልግሎት መክፈል
  • በቴሌብር መተግበሪያ
  1. በቴሌብር ለመክፈል የሚለውን ይጫኑ
  2. የአገልግሎት ክፍያ የሚለውን ይጫኑ
  3. የአገልግሎት ክፍያ በደራሽ የሚለውን ይጫኑ
  4. የሚፈልጉትን የድርጅት ስም ይመርጣሉ
  5. የክፍያ ማጣቀሻ ቁጥር አስገብተው ቀጣይ የሚለውን ይጫኑ
  6. የሚስጥር ቁጥርዎን በማስገባት ለመጨረስ እና ያረጋግጡ የሚለውን በቅደም ተከተል በመጫን ክፍያዎን ይፈጽሙ
  • በአጭር ቁጥር (*127)፡
  1. *127# ይደውሉ
  2. # በመጫን ወደ ቀጣይ ይለፉ
  3. 7ን በመጫን በቴሌብር ይክፈሉ የሚለውን ይምረጡ
  4. 2ን በመጫን የአገልግሎት ሂሳብ ክፍያ የሚለውን ይጫኑ
  5. 1ን በመጫን በድርጅት ስም የሚለውን ይምረጡ
  6. # በመጫን ወደ ቀጣይ ይለፉ
  7. 6ን በመጫን ደራሽ ውሃና ፍሳሽ የሚለውን ይምረጡ
  8. አግልግሎት ሰጪ ተቋሙን ይምረጡ
  9. የመክፈያ ቁጥር እና የሚስጢር ቁጥር በማስገባት ለማረጋገጥ 1ን ይጫኑ
የበረራ ትኬትዎን መግዛት
  • በቴሌብር መተግበሪያ፡
  1. በቴሌብር ለመክፈል የሚለውን ይጫኑ
  2. የአገልግሎት ክፍያ የሚለውን ይጫኑ
  3. የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚለውን ይምረጡ
  4. የሚስጥር ቁጥርዎን በማስገባት ለመጨረስ እና ያረጋግጡ በቅደም ተከተል በመጫን ክፍያዎን ይፈጽሙ

ማስታወሻ፡ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሞባይል መተግበሪያ ወይም ድረ-ገጽ ሲመዘገቡ በሚደርስዎ የክፍያ ማጣቀሻ ቁጥር ክፍያዎን በቴሌብር በቀላሉ ይክፈሉ፡፡

  • በአጭር ቁጥር (*127#)፡
  1. *127# ይደውሉ
  2. # ያስገቡ
  3. 7ን በቴሌብር ለመክፈል የሚለውን ይምረጡ
  4. 6ን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚለውን ይምረጡ
  5. 1ን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚለውን ይምረጡ
  6. የክፍያ ማጣቀሻ ቁጥር ያስገቡ
  7. ለማረጋገጥ 1ን ያስገቡ
  8. አስተያየትዎን ያስገቡ
  9. የሚስጥር ቁጥርዎን አስገብተው ክፍያዎን ሲፈጽሙ የማረጋገጫ መልእክት ይደርስዎታል

ማስታወሻ፡ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሞባይል መተግበሪያ ወይም ድረ-ገጽ ሲመዘገቡ በሚደርስዎ የክፍያ ማጣቀሻ ቁጥር ክፍያዎን በቴሌብር በቀላሉ ይክፈሉ፡፡

የነዳጅ ክፍያዎን በቴሌብር ይክፈሉ
  • የነዳጅ ክፍያዎን በቴሌብር መተግበሪያ ይክፈሉ
  1. ለግብይት ለመክፈል የሚለውን ይጫኑ
  2. የሻጭ ቁጥር የሚለውን በመምረጥ የሻጭ ቁጥር፣ ኦፕሬተር መለያ ቁጥር፣  የገንዘብ መጠን በማስገባት ይቀጥሉ የሚለውን ይጫኑ
  3. የሚስጥር ቁጥር ያስገቡ
  4. ለግብይት ለመክፈል ሚለውን በመጫን ክፍያዎን ይፈጽሙ
  • የነዳጅ ክፍያዎትን በቴሌብር አጭር ቁጥር *127# ይክፈሉ
  1. *127# ይደውሉ
  2. # በማስገባት ወደ ቀጣይ ዝርዝር ማውጫ ይሂዱ
  3. 9 ቁጥርን ግብይት ለመክፈል የሚለውን ይምረጡ
  4. 1ቁጥርን ግብይት ለመክፈል የሚለውን ይምረጡ
  5. የሻጭ መለያ ቁጥር ያስገቡ
  6. የብር መጠን ያስገቡ
  7. ለማረጋገጥ 1ቁጥርን ይጫኑ
  8. የሚስጥር ቁጥርዎን አስገብተው ክፍያዎትን ይፈጽሙ

ማስታወሻ:- የሻጭ መለያ ቁጥር ማለት የአገልግሎት ሰጪው ማደያ የመክፈያ መለያ  ቁጥር ነው

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ክፍያዎችን በቴሌብር ይፈጽሙ!
  1. ወደ www.eservices.gov.et በመሄድ ወደ አካውንትዎ ይግቡ
  2. የአገልግሎት ሰጪውን እና የአገልግሎት ዓይነቱን ይምረጡ
  3. የማመልከቻ ቅጹን ይሙሉ
  4. ለክፍያ አማራጭዎ ቴሌብርን ይምረጡ
የትራፊክ ቅጣት መክፈል

በቴሌብር መተግበሪያ:

ቅጣቱን በቴሌብር መክፈል እንደሚፈልጉ ለትራፊክ ፖሊስ አስቀድመው ያሳውቁ

  1. በቴሌቢር መተግበሪያ ዋና ገጽ ላይ በቴሌብር ይክፈሉ የሚለውን ይምረጡ
  2. የትራፊክ ቅጣት ክፍያን ይምረጡ
  3. አ.አ የትራፊክ አስተዳደር ኤጀንሲን ይምረጡ
  4. በትራፊክ ፖሊስ ለእርስዎ የተዘጋጀ የክፍያ ማዘዣ ቁጥር ያስገቡ
  5. ያሉትን ዝርዝሮች ያረጋግጡ
  6. ፒን ቁጥር ያስገቡ፣ መጨረስ የሚለውን ይጫኑ፣ ክፍያን ይጫኑ እና የማረጋገጫ መልእክት ይደርሶታል

 በቴሌብር አጭር ቁጥር *127#

ቅጣቱን በቴሌብር መክፈል እንደሚፈልጉ ለትራፊክ ፖሊስ አስቀድመው ያሳውቁ

  1.  *127# ይደውሉ
  2.  # ያስገቡ
  3. 7'ን ያስገቡ እና በቴሌብር ይክፈሉ የሚለውን ይምረጡ
  4. 3'ን ያስገቡ እና የቅጣት ክፍያን ይጫኑ
  5. 1'ን ያስገቡ እና የፍጆታ ክፍያን ይምረጡ
  6. 1'ን አዲስ አበባ የትራፊክ አስተዳደር ኤጀንሲን ይምረጡ
  7. የክፍያ ማዘዣ ቁጥር ያስገቡ
  8. ለማረጋገጥ 1ን ይጫኑ
  9. ፒን ያስገቡ
  10. ምክንያት ያስገቡ እና የማረጋገጫ መልእክት ይደርሶታል