To Our Esteemed Customers
Updates on Telecom Service Resumption in the North Region
Our company briefed on December 10, 2020 to our esteemed customers and media on Telecom services interruption in the North region since November 4/2020, 00:37 AM. In the press briefing, detail clarifications were given on when and how the service outage has occurred, information and evidence about the perpetrators. We have also provided information about the challenges to restore the service, like damages on transmission lines and commercial power cuts.
Efforts underway to restore telecom services in the region now, following coordinated and concerted efforts, we have managed to provide Mobile Voice services in Mekele city and Maychew. Dear our Customers be aware that Mekele city mobile service is up using alternative power solution; hence there might be some service instability until commercial power is restored.
It is also to be remembered that we have restored the service in the areas such as Dansha, Humera, Maykadra, Turkan, Maytsebri and Korem partially and full-service restoration in Alamata.
Dear our esteemed customers, please be notified that we are doing our best effort to rehabilitate all damaged transmission lines, and working with Ethiopian Electric Utility to realize full restoration of telecom services in the region.
Ethio telecom
December 12, 2020
ለክቡራን ደንበኞቻችን
በሰሜን ሪጅን የቴሌኮም አገልግሎት የተጀመረባቸው አካባቢዎችን በሚመለከት ወቅታዊ መረጃ
ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ከሌሊቱ 6፡37 ሰዓት ጀምሮ በሰሜን ሪጅን የቴሌኮም አገልግሎት መቋረጡን አስመልክቶ ታህሳስ 1 ቀን 2013 ዓ.ም በሰጠነው ጋዜጣዊ መግለጫ አገልግሎቱ መቼና እንዴት እንደ ተቋረጠ እንዲሁም አገልግሎቱን ያቋረጡ አካላት በሚመለከት ዝርዝር መረጃና ማስረጃ ያቀረብን ሲሆን አገልግሎቱን መልሶ ለማስጀመር ከዋና ሞባይል ጣቢያ የሚያገናኙ ሁሉም አማራጭ መስመሮች መቆረጣቸውና የኃይል አቅርቦት መቋረጥ ዋነኛ ተግዳሮት መሆናቸውን መጥቀሳችን ይታወሳል፡፡
በሰሜን ሪጅን የቴሌኮም አገልግሎትን ለማስጀመር ሰፊ የቅንጅት ሥራዎችና ከፍተኛ ርብርብ እየተካሄደ ሲሆን በአሁን ወቅት በመቀሌ ከተማና በማይጨው የሞባይል ድምጽ አገልግሎት ማስጀመር ተችሏል፡፡
በመቀሌ የሞባይል ድምጽ አገልግሎት ያስጀመርነው አማራጭ ኃይል በመጠቀም ከመሆኑ አንጻር የአገልግሎት መቆራረጥ ሊያጋጥም የሚችል መሆኑን ከወዲሁ ደንበኞቻችን እንዲገነዘቡ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
ከዚህ ቀደም በዳንሻ፣ በተርካን፣ በሁመራ፣ በሽራሮ፣ ማይጸብሪና፣ ማይካድራ እና በኮረም አካባቢዎች በከፊል እንዲሁም በአላማጣ ሙሉ በሙሉ የቴሌኮም አገልግሎት የተጀመረ መሆኑን መግለጻችን ይታወሳል፡፡
የጥገና እና የመሠረተ ልማቶችን መልሶ የማቋቋም ሥራዎችን በማከናወንና ከኃይል አቅርቦት ጋር በተገናኘ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በመሥራት የተሟላ የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት ከፍተኛ ጥረት እያደረግን መሆኑን ለክቡራን ደንበኞቻችን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም
ታህሳስ 3 ቀን 2013 ዓ.ም