Ethio telecom signs a memorandum of understanding with Amhara Bank to provide modern modular data center service

In the recent past, Ethio telecom has built and launched modern modular data center service that enables the company sign the agreement with Amhara Bank today so that the bank would use this modern high capacity world standard data center for modernizing its information technology system so as to provide reliable services to its customers.

This modular data center is designed to ensure mission-critical data and equipped with extensive security and compliance system controls with 99% reliable connectivity and high electric power saving capacity. It is also a high capacity world class standard data center managed by skilled man power and has more than five direction fiber connectivity with automatic switch over functionality to ensure service reliability and can help carry out quick incident detection and maintenance activities in case of network connection failure or other related problems.

In addition, the center is equipped with the state-of-the-art power saving electrical systems, cooling systems and security cameras as well as modern network and fiber cable enclosures/accessories and compartments. Specifically, what makes building this modern modular data center unique is that its mission to enhance the services of all the company’s information technology and network infrastructure developments.

Currently, 84 customers/partners have collocated in the company’s data center, and each data center has six-degree resilient fiber connection. The data center would enable various technology products and services rendering companies to become operational in a short period of time by sharing them the data center collocation.

The data center’s major importance on customer experience includes high availability-best customer experience, flexibility to introduce new platform and service, reliability to run customers’ businesses, high level physical security as well as fast time to market to host for collocation/ cloud service for the existing and potential partners.

So far, our company has built two modular data centers and three more data centers are under construction that will soon have five data centers altogether. Moreover, big Green Data Center is under requirement preparation and it can host 1000 racks with geographical redundancy. To this effect, five sites are made already available outside Addis Ababa for geography redundancy equipped with its own disaster time emergency backup.

Ethio telecom           

12 April 2022

ኢትዮ ቴሌኮም ለአማራ ባንክ ዘመናዊ የሞጁላር መረጃ ማዕከል አገልግሎት ለመስጠት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

ኢትዮ ቴሌኮም ዘመናዊ የሞጁላር መረጃ ማዕከል (Modular Data Center) ገንብቶ አገልግሎት ላይ ያዋለ ሲሆን ይህንኑ ከፍተኛ አቅም ያለውን የመረጃ ማዕከል አገልግሎት ለመጠቀም የሚያስችል ስምምነት ከአማራ ባንክ ጋር በዛሬው ዕለት ተፈራርሟል፡፡ ይህም የባንኩን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስርዓት በዚህ እጅግ ዘመናዊ እና ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃውን በጠበቀ የመረጃ ማዕከል አማካኝነት አስተማማኝ አገልግሎት ለደንበኞቹ ለመስጠት ያስችለዋል፡፡

ይህ ዘመናዊ የመረጃ ማዕከል ከፍተኛ የራሱ መጠባበቂያ የኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦት ያለው፣ እጅግ ጠቀሜታ ያለውን የዳታ አገልግሎት (mission-critical data) ማስቀመጥ በሚያስችል መልኩ ዲዛይን የተደረገ፣ በሰለጠነ የሰው ኃይል የሚመራ ከፍተኛ አቅም ያለው የዳታ ማዕከል ሲሆን፣ አገልግሎት እንዳይስተጓጎል የሚያስችል 99% አስተማማኝ የኔትዎርክ አቅም እንዲኖረው ከአምስት በላይ አቅጣጫዎች በአውቶማቲክ ማዞሪያ (switch) በሚሰራ የፋይበር ኮኔክሽን የተገጠሙለት እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች በማዕከሉ ውስጥ ያሉ ሲስተሞች ላይ የኔትዎርክ ኮኔክሽንም ይሁን ሌሎች ተዛማጅ ችግሮች ቢያጋጥሙ ፈጣን ፍተሻና ጥገና ለማከናወን የሚያስችል (quick incident detection and maintenance) ስርዓት ያለው ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃውን የጠበቀ የመረጃ ማዕከል ነው፡፡

በአሁኑ ሰዓት በዳታ ማዕከሎቹ በኮሎኬሽን (በመጋራት) የሚገለገሉ 84 ተጠቃሚ አካላት ያሉ ሲሆን፣ እያንዳንዱ የዳታ ማዕከል ስድስት ዲግሪ ባለው እጅግ ጠንካራ በሆነ የፋይበር ኮኔክሽን የሚገነባ ሲሆን የመረጃ ማዕከሉ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ምርትና አገልግሎቶችን መስጠት ለሚፈልጉ ድርጅቶች በአጭር ጊዜ የመረጃ ቋቱን በመጋራት (data center collocation) ወደ ሥራ እንዲገቡ ያስችላቸዋል፡፡

የዳታ ማዕከሉ ካለው ከፍተኛ ጠቀሜታዎች መካከል ለላቀ የደንበኛ አገልግሎት ተሞክሮ የሚሆን፣ አዳዲስ ፕላትፎርምና አገልግሎትን ለማስጀመር የሚያስችል ተለዋዋጭ (flexible) የቴክኖሎጂ ባህሪይ ያለው፣ ደንበኞች ለሚያካሄዱት ቢዝነስ አስተማማኝ እና ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሁም ለክላውድ አገልግሎት ፈላጊዎች ወይም አጋሮች በኮሎኬሽን አማካይነት በፈጣን ሁኔታ ለመገብየት እና ለማስተናገድ የሚያስችል ሆኖ የተደራጀ ነው፡፡

በተጨማሪም ማዕከሉ ደረጃውን የጠበቀ ኃይልን የሚቆጥብ የኤሌክትሪክ ሲስተም፣ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ቆጣቢ፣ የማቀዝቀዣ ሲስተምና የደህንነት ካሜራዎች የተገጠሙለት ሲሆን ዘመናዊ የሆነ የኔትዎርክና የፋይበር ኬብል ማቀፊያዎች እና ኮምፓርትመንቶች ያሉት ነው፡፡ ኩባንያው አገልግሎት ለሚሰጥባቸው ለሁሉም የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅና የኔትዎርክ መሰረተ ልማቶች አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ የተገነባ መሆኑም የተለየ ያደርገዋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ሁለት የሞዱላር ዳታ ማዕከላትን የገነባ ሲሆን፣ ተጨማሪ በግንባታ ላይ ካሉት ሶስት ማዕከላት/ሳይቶች ጋር በድምሩ አምስት የዳታ ማዕከላት በቅርቡ የሚኖሩት ይሆናል፡፡ ከዚህም ባሻገር በተለያዩ ቦታዎች የመጠባባቂያ ጣቢያዎች ያሉት አንድ ሺህ ራክ ማስተናገድ የሚችል ትልቅ አረንጓዴ የዳታ ማዕከል (Green Data Center) ለመገንባት የመስፈርት ዝግጅት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ለጂኦግራፊያዊ ሽፋን መጠባባቂያ የሚሆኑ ከአዲስ አባባ ውጪ አምስት ሳይቶች /ቦታዎች/ እንዲሁም የራሱ የሆነ የአደጋ ጊዜ መጠባበቂያም ተገጥሞለታል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም

ሚያዝያ 04 ቀን 2014 ዓ.ም

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives