ኢትዮ ቴሌኮም በምሥራቅ ሪጅን የላቀ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን 4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት ጀመረ::

ኩባንያችን በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች የዳታ ትራፊክ እድገትና ፍላጎትን መሠረት በማድረግ እያከናወነ ያለውን የ4G/LTE አገልግሎት የማስፋፊያ ሥራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል አሁን ደግሞ በምሥራቅ ሪጅን በሚገኙ ከተሞች ማለትም በድሬዳዋ፣ ጭሮ እና አይሻ የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ   የሞባይል ኢንተርኔት  አገልግሎት  ማስፋፊያ ፕሮጀከት አጠናቆ አገልግሎቱን ማስጀመር ችሏል፡፡

የ4G LTE አገልግሎት የላቀ ፍጥነትና ባንድዊድዝ እንዲሁም አስተማማኝ የዳታ አገልግሎት የሚሰጥ እንደመሆኑ ደንበኞቻችን አገልግሎታቸውን ዲጂታይዝ ለማድረግ፣ ምርታማነትን ለማሳደግ እና በአጠቃላይ የቴሌኮም አገልግሎት ላይ ያላቸውን ተሞክሮ በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ ያስችላል፡፡

በቀጣይነትም ኩባንያችን በተመሳሳይ ሁኔታ  የዳታ ትራፊክ እድገትና ፍላጎትን መሠረት ባደረገ መልኩ  በዕቅድ ይዞ  በከፍተኛ ርብርብ  እያከናወናቸው ያሉ የ4G/LTE አገልግሎት የማስፋፊያ ሥራዎችን በማጠናቀቅ  በተለያዩ የክልል ከተሞች በቅርቡ ለማስጀመር የሚያስችሉ ቅድመ ሥራዎችን በመከናወን ላይ  ይገኛል፡፡

 በዚህ አጋጣሚ የቴሌኮም አገልግሎት መጠቀሚያ መሣሪያ (smart phone) እና የይዘት (content) አቅራቢዎች በመረጃ የበለፀገ ማህበረሰብና ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ እንዲሁም አሁን የተዘረጋውን ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የሞባይል ኔትወርክ በስፋት ለመጠቀም የሚያስችሉ ዘመናዊ የሞባይል ቀፎዎችና ይዘቶችን ለህብረተሰባችን በስፋትና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives