ሰብዓዊነት ማሕበራዊ ሃላፊነታችን ነው፤ ማካፈል የኢትዮ ቴሌኮም አንዱ እሴት ነው፣” ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ

ኢትዮ ቴሌኮም ለድንገተኛ አደጋ አገልግሎት የሚውል አምቡላንስ ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የካቲት 04 ቀን 2011 ዓ.ም አበርክቷል፡፡

በርክክብ ወቅት “ሰብዓዊነት ማሕበራዊ ሃላፊነታችን ነው፤ ማካፈል የኢትዮ ቴሌኮም አንዱ እሴት ነው፣” ያሉት ወ/ሪት ፍሬሕይወት፣ ኢትዮ ቴሌኮም እንደ ተቋም ከሚያደርገው ሰብዓዊ ድጋፍ በተጨማሪ፤ የተቋሙ ሰራተኞችም ከደመወዛቸው በየወሩ የሁለት ብር መዋጮ በማድረግ በጠቅላላው በወር 30 ሺህ ብር እና በዓመት ሁለት ጊዜ የበጎ ፍቃደኞች ደም ልገሳ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡

 ከዚህ በተጨማሪ የኩባንያው ሰራተኛ ማህበርም ራሱን ችሎ እንደ ተቋም አባል በመሆን በየዓመቱ 50,000 ብር ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም ኢትዮ ቴሌኮም ለማህበሩ በተለያዩ መስኮች ከሚሰጠው ድጋፍ በተጨማሪ ቋሚ አባል በመሆን በዓመት የ100,000 ብር የኮርፖሬት አባልነት ክፍያ ይከፍላል፡፡ በጠቅላላው ኩባንያው ለቀይ መስቀል ማህበር ከላይ በተጠቀሱት የተለያዩ መንገዶች ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ በመግለጽ ለዚህም ስራ አስፈፃሚዋ ለተቋሙ ለሠራተኞቹ እና ለሠራተኛ ማህበሩ፤ ማህበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት አንፃር ለሚያደርጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በእለቱ ኢትዮ ቴሌኮም ያስረከበው አምቡላንስ፤ ወላድ እናቶች እና ድንገተኛ አደጋ የደረሰባቸው ወገኖችችን በወቅቱ ህክምና እንዲያገኙ ይረዳል:: በኢትዮ ቴሌኮም ሠራተኞች፣ በተቋሙ የሠራተኛ ማህበር እንዲሁም በተቋሙ የሚደረጉ ድጋፎች እጅግ አጋዥ መሆናቸውን እና ለሌሎች ተቋማት አርአያ እንደሚሆኑ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ብሔራዊ ጽ/ቤት እና ሌሎች የተቋሙ ኃላፊዎች በመግለጽ ለዚህም ድጋፍ ለኢትዮ ቴሌኮምና ለሰራተኞቹ ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives