ኢትዮ ቴሌኮም አሽከሪካሪዎች የትራፊክ ደንብ ቅጣት ክፍያ በቴሌብር አማካኝነት ለመፈጸም የሚያስችል አሰራር ተግባራዊ አደረገ

ኢትዮ ቴሌኮም አሽከሪካሪዎች የሚገጥማቸውን የትራፊክ ደንብ ቅጣት ክፍያ ለመፈጸም ስራቸውን በማቋረጥ እና ወረፋ በመጠበቅ ያባክኑት የነበረውን አሰራር ለማስቀረት እንዲሁም የቅጣት አስፈጻሚውን አካል አሠራር ለማሳለጥ የክፍያ ቴክኖሎጂ ውጤት በሆነው በቴሌብር አማካኝነት እንዲፈጸም የሚያስችል ዘመናዊ የትራፊክ ደንብ ቅጣት ክፍያ አሠራር ተግባራዊ አድርጓል፡፡

“ደንብ አክብረን በጥንቃቄ እናሽከርክር ቅጣት ካለ በቴሌብር” በሚል መሪ ሀሳብ በዛሬው ዕለት ተግባራዊ የተደረገው አሰራር ዋና ዋና ባለድርሻ አካላት ኢትዮ ቴሌኮም፣ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሲሆኑ፣ አሽከሪካሪዎች በተለያዩ ምክንያቶች የትራፊክ ደንብ ጥሰት ቅጣት ሲያጋጥማቸው በቴሌብር እንደሚከፍሉ ለቅጣት ፈፃሚው ትራፊክ ፖሊስ በማሳወቅ ክፍያቸውን በቴሌብር ወዲያዉኑ መክፈል ያስችላቸዋል፡፡

የትራፊክ ደንብ ቅጣት ክፍያን በቴሌብር አማካኝነት መክፈል የሚያስችለው ይህ አገልግሎት ወይም አሰራር ለዘመናት አድካሚ የነበረውን በወረቀት ላይ ያተኮረ የቅጣት ክፍያ አፈጻጸምን የሚተካ ወይም የሚያስቀር ሲሆን የአሽከርካሪዎችን ጊዜ እና ወጪን ቆጣቢ እንዲሁም የተቋማቱን አሰራር ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂ የሚያዘምን አገልግሎት ነው፡፡

ለዚህ አሰራር ስኬታማነት ከ1500 በላይ ለሚሆኑ የትራፊክ ፖሊሶች በኢትዮ ቴሌኮም ስልጠና የተሰጠ ሲሆን፣ የትራፊክ ፖሊሶች የትራፊክ ደንብ ቅጣት ክፍያን 6050 አጭር ቁጥርን በመጠቀም እና አጭር የጽሑፍ መልዕክት (SMS) በመላክ መፈጸም ይችላሉ፡፡

በዚህም መሰረት አሽከሪካሪዎች ከመኪናቸው ሳይወርዱ ወዲያውኑ በቴሌብር አማካኝነት የትራፊክ ደንብ ጥሰት ቅጣት ክፍያን በቀላሉ በመፈጸም በቅጣቱ ምክንያት የመንጃ ፈቃዳቸው እንዳይያዝባቸው ማድረግ ያስችላቸዋል፡፡

በተጨማሪም በቅርቡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትኬት ግዥን እና ወርሃዊ የውኋ ፍጆታ አገልግሎት ክፍያዎችን ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ በሆው ቴሌብር መፈጸም የሚቻልበትን አሰራር ተግባራዊ በማድረግ ማህበረሰባችን አገልግሎቱን በቀላሉ እንዲያገኝ እየሰራን እንገኛለን፡፡

                   ኢትዮ ቴሌኮም

Ethio telecom has implemented the drivers’ traffic penalty payment through telebirr digital technology system

Ethio telecom has implemented the drivers’ traffic penalty payment via telebirr, the prominent digital payment system, in order to address the problem of drivers who have been wasting their time and resource to settle their traffic penalty payment through extended, tiresome and traditional paper-based methods. This payment system would also modernize and replace the age-old paper-based payment system of the Addis Ababa Traffic Management Agency and other concerned authorities.

Today’s launching ceremony is organized with key message “Respect the traffic rules while driving; if there is a breach, settle your penalty via telebirr” and a memorandum of understanding has been made among the main stakeholders, Ethio telecom, Addis Ababa Traffic Management Agency, and Addis Ababa Police Commission.

In order to settle a traffic penalty payment via telebirr drivers are expected to inform the traffic police in advance their preference to settle the payment though telebirr before the police issue a receipt.

This service, which allows for the payment of traffic penalty through telebirr payment system, can replace the age-old paper-based payment system and save the drivers’ time and money as well as transform the stakeholders operation to digital technology system.In connection with this, more than 1,500 traffic police officers have been trained by Ethio telecom for the success of this technology-based service. Thus, the traffic police can issue traffic penalty payment by using a 6050 short number and by sending short message service (SMS).

Furthermore, Ethio telecom is working to integrate with major utility service providers and Ethiopian Airlines to enable the society to settle payments easily, rapidly and conveniently.

                 Ethio telecom

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives