ኢትዮ ቴሌኮም በደቡብ ሪጅን ከተሞች ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት ጀመረ
ኩባንያችን ከፍተኛ የዳታ አጠቃቀም በሚታይባቸው 103 ከተሞች የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎትን ለማስፋፋት የያዘውን ዕቅድ ተከትሎ በዛሬው ዕለት በደቡብ ሪጅን በሚገኙ 12 ከተሞች ማለትም በሀዋሳ፣ ሻሸመኔ፣ አርሲ ነገሌ፣ ቡሌ ሆራ፣ዲላ፣ ያቤሎ፣ ይርጋለም፣ አለታ ወንዶ፣ ሞያሌ፣ ሻኪሶ፣ አዶላ እና ነገሌ የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ የሞባይል ኢንተርኔት ማስፋፊያ ፕሮጀክት አጠናቆ አገልግሎቱን ማስጀመር ችሏል።