ይህ ሪፖርት ከሐምሌ 2011 እስከ ታህሳስ 2012 ያለውን የኢትዮ ቴሌኮም የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም የሚገልጽ ነው፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ላይ ለህዝብ ይፋ ያደረገውን የሦስት ዓመት ስትራቴጂና የ2012 በጀት ዓመት እቅድ ተከትሎ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ሰፊ የለውጥና የኦፕሬሽን ሥራዎች እያከናወነ ሲሆን በዋናነትም በስትራቴጂው ላይ የተመለከቱ ስድስት ዋና ዋና የትኩረት መስኮችን ለመተግበር ሰፊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
መንግስት በቴሌኮም ዘርፍ ላይ ያስቀመጠውን የፖሊሲ አቅጣጫ ተከትሎ አስፈላጊ ዝግጅቶችን በማድረግ ተቋሙ በለውጡ የበለጠ ተጠቃሚ የሚያደርገውና በሦስት ዓመት እቅዱ ላይ እንደተቀመጠው ብቁ፣ ተወዳዳሪና ተመራጭ የቴሌኮም አገልግሎት ሰጭ ለመሆን የሚያስችል የውስጥ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል፡፡ የኦፕሬሽን ልህቀትን ለማምጣት የሚረዱ የአሰራር ሥርዓቶችና አደረጃጀት የማሻሻል፣ የአገልግሎት ተደራሽነትና ጥራትን ለማሳደግ ተጨማሪ የኔትዎርክ ማስፋፊያና ማሻሻያዎችን ማድረግ፣ ደንበኞችን ለማርካት የተለያዩ አዳዲስ አገልግሎቶችን ማቅረብ፣ የቢዝነስና የቴክኖሎጂ መናበብ በመፍጠር አዳዲስ አገልግሎቶች ማምጣትን፣ ከአጋር ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት ዘላቂና የጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ማድረግ፣ የንብረት አስተዳደርና የሀብት አጠቃቀምን ማሻሻል፣ የቴሌኮም ማጭበርበርን በተለያዩ ስልቶች መከላከል እንዲሁም የተቋም ደህንነትን ከማረጋገጥ አኳያ ልዩ ትኩረት ማድረግ፣ የዓለም አቀፍ ቢዝነስ ማጠናከርና ገበያው በሚጠይቀው መሠረት አዳዲስ አሰራሮችን መከተል፣ የተቋሙን ሠራተኛና አመራር ስትራቴጂ የማስፈጸምና የመፈጸም እንዲሁም የአመራሩን ውሳኔ የመስጠት አቅም ለማጎልበት የሚያስችሉ ሥራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
የደንበኞችን ሁለንተናዊ ተሞክሮ ለማሻሻልና በተለይም የዳታ አገልግሎት ተጠቃሚነት ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ ይህን እያደገ የመጣውን ፍላጎት ማስተናገድ የሚያስችል የኔትወርክ አቅም የማሳደግ ሥራዎች በአዲስ አበባና በክልሎች እየተከናወኑ ሲሆን ባሳለፍነው ስድስት ወራት ከተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች 759,741 ተጨማሪ ደንበኞችን ማስተናገድ የሚችል የ3ጂ እና 170,737 የ2ጂ ሞባይል ኔትወርክ አቅም ፈጥሯል፡፡ በሌላ በኩል በፍጥነት እያደገ ያለውን የዳታ አጠቃቀም ለማስተናገድ የሚያስችል የዓለም አቀፍ ጌትዌይ አቅምን በግማሽ ዓመቱ ከ71% በላይ ለማሳደግ ተችሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች የ4ጂ ኔትዎርክ ማስፋፊያ ፕሮጀክቶች ለመተግበር የሚያስችለውን ስራ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ብዛት 45.6 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን የእቅዱን የ99% አፈጻጸም ያለው ሲሆን እንዲሁም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ሲነጻጸር የ10.9% እድገት አሳይቷል፡፡ በአገልግሎት አይነት ሲታይ የሞባይል ድምፅ ደንበኞች ብዛት 44.03 ሚሊዮን፣ የዳታ እና የኢንተርኔት ተጠቃሚ 22.74 ሚሊዮን፣ እንዲሁም መደበኛ ስልክ 1.01 ሚሊዮን ደንበኞች ሲሆን አጠቃላይ የቴሌኮም ስርጸት (teledensity) መጠኑ 45.4% ደርሷል፡፡
ገቢን ከማሳደግ አኳያ ደንበኞች የቴሌኮም አጠቃቀማቸውን ለማሳደግና ተሞክሯቸውን ለማሻሻል የሚስችሉ የኔትወርክ ማስፋፊያና የአገልግሎት ጥራትን ለመጨመር የሚያስችሉ ማሻሻያዎችን በማከናወን እንዲሁም ከመደበኛ የቴሌኮም አገልግሎቶች በተጨማሪ ሌሎች እሴት የሚጨምሩ 6 አዳዲስ እና 16 የተሻሻሉ የሀገር ውስጥና የዓለም አቀፍ ምርትና አገልግሎቶችን ለገበያ በማቅረብ በስድስት ወራት ውስጥ 22.04 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ያገኘ ሲሆን የእቅዱን 104% ለማሳካት ተችሏል፤ ይህም ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ32% እድገት አሳይቷል፡፡ የውጭ ምንዛሪ ከሚያስገኙ አገልግሎቶች 73 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የተገኘ ሲሆን ይህም የእቅዱን 111% ያስመዘገበ ሲሆን ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ116% እድገት አስመዝግቧል፡፡ የተገኘው ገቢ በአገልግሎት አይነት ሲታይ የሞባይል ድምጽ ገቢ ድርሻ 50.4%፣ የዳታና ኢንተርኔት ገቢ ድርሻ 27.3%፣ የዓለም አቀፍ ንግድ ገቢ ድርሻ 9.8%፣ እሴት ከሚጨምሩ አገልግሎቶች (VAS) 8.5% እንዲሁም ከሌሎች አገልግሎቶች የተገኘው ገቢ ድርሻ 3% ይይዛል፡፡
በስድስት ወራት ውስጥ አጠቃላይ 3.89 ቢሊዮን ብር ታክስና 2 ቢሊዮን ብር ዲቪደንድ ለመንግስት የተከፈለ ሲሆን በቬንደር ፋይናንሲንግ ሞዳሊቲ ለተከናወኑ ፕሮጀክቶች ብድር 4.4 ቢሊዮን ብር ወይም 148.15 ሚሊዮን ዶላር ክፍያ ተፈጽሟል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም ከ16 ሺህ በላይ ቋሚ እና ከ19 ሺህ በላይ የኮንትራት ሠራተኞች አሉት፡፡ በተጨማሪም የኢትዮ ቴሌኮም ምርትና አገልግሎት ለደንበኞች የሚያደርሱ 181 ሺህ አጋሮች ያሉ ሲሆን በአጠቃላይ ከቴሌኮም ጋር ተዛማጅ በሆኑ ሥራዎች ተሰማርተው የሥራና የገቢ እድል የተፈጠረላቸው ዜጎች ቁጥር ከ240 ሺህ በላይ ደርሰዋል፡፡ የተቋሙን የሰው ኃይል በእውቀት፣ በክህሎትና በመልካም የሥራ ባህል ከማነጽ አኳያ በስድስት ወራት 137 የተለያዩ የሥልጠና ፕሮግራሞችን በመቅረጽ 8,928 ሠራተኞች ስልጠና ወስደዋል፡፡
በተጨማሪም የሠራተኛውን ተነሳሽትና የባለቤትነት መንፈስ የሚያሳድጉ ሥራዎች የተከናወኑ ሲሆን ለአብነት ያህል የበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ላይ ሠራተኞችን በተቋሙ ስትራቴጂ ዝግጅትና የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ላይ ተሳትፎ እንዲኖራቸውና ግብዓት እንዲሰጡ የማድረግ፣ ከማኔጅመንቱ ጋር በቅርበት በመናበብና በመተጋገዝ መስራት፣ የሥራ መገልገያ መሣሪያዎችን አቅርቦት ማሻሻል፣ የሥራ ከባቢን አመቺ የማድረግ፣ የተለያዩ የማበረታቻ ክፍያዎች ማከናወን እንዲሁም በሁሉም የተቋሙ የሥራ ቦታዎች የሠራተኞች ቀን በማክበር በሠራተኛውና በአመራሩ መካከል የተሻለ መቀራረብ የሚፈጥሩ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡
ኩባንያችን ለደንበኞቹ ከሚሰጠው የቴሌኮም አገልግሎት በተጨማሪ ለማህበረሰባችን ፋይዳ ባላቸው ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመሳተፍ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በተቀናጀ መልኩ ከመወጣት አንፃር ባለፉት 6 ወራት በድምሩ 151.5 ሚሊዮን ብር በላይ በአይነትና በገንዘብ አስተዋጽኦ በማድረግ በመላው ሃገሪቱ በትምህርት፣ በጤና፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ አረንጓዴ ልማትና ማስዋብ ላይ ተሳትፏል፡፡ ኩባንያችን ከሚያደርገው እገዛ በተጨማሪ ሠራተኞቻችን በበጎ ፍቃደኝነት ላይ የተመሠረተ አስተዋፅኦ በማድረግ የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች የ1.5 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍና የተለያዩ የቁሳቁስና የመልካም ፍቃድ አገልግሎት በመስጠት እጅግ የሚበረታታና አርአያነት ያለው ተግባር አከናውነዋል፡፡
ኩባንያችን በአካባቢ ጥበቃ ላይ ከሚያደርገው እገዛ በተጨማሪ ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ ምርቶችን በመጠቀም በአየር ንብረት ላይ የሚደርሰውን አሉታዊ ተጽዕኖ በመቀነስ ላይ ሲሆን በዚህም 21% የኔትወርክ ጣቢያዎች ከጸሐይ በሚመነጭ ኃይል እንዲሰሩ በማድረግ በድምሩ 20 ሜጋ ዋት ኃይል በማመንጨት ጥቅም ላይ አውሏል፡፡
በመንፈቅ ዓመቱ የፋይበርና ኮፐር መስመሮች ስርቆትና መቆራረጥ፣ የሃይል አቅርቦት መቆራረጥ፣ የቴሌኮም ማጭበርበር፣ የጸጥታ ችግሮችና የቴሌኮም ጣቢያዎች መትከያ ቦታ አቅርቦት መዘግየት በዋናነት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ናቸው፡፡
በመጨረሻም ለተመዘገበው አመርቂ አፈጻጸም ለሠራተኞቻችን፣ ለደንበኞቻችን እንዲሁም ለሥራ አጋሮቻችን እና ለባለድርሻ አካላት ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡

Ethio telecom 2012 EFY (2019/20) First Half Business Performance Summary Report
This report covers the performance period from July 01 to December 31, 2019.


The 2012 Ethiopian fiscal budget year was commenced with the introduction of the company’s three- year strategic plan outlining six strategic themes, BRIDGE, along with the yearly plan in place. Both the three years’ strategy and the annual plans aim to make the company a competent, competitive and preferred telecom service provider in the country.
To keep up with the fluid telecom landscape, the company has made the following major interventions: introduction of new organizational structure in some of its critical operational functions, revision of working systems, expansion of network capacity to enhance quality of service, ensuring enhanced customer experience and satisfaction by improving access, and by offering new and revamped services, strengthening international business, establishing partnership and collaborations in a consistent and in a manner that ensures mutual benefit, ensuring effective property administration and resource utilization, employing new ways and technology to prevent telecom fraud, enhancing execution capacity, interventions to empower and build leadership and skill development of employees and management.
During this period, various projects were finalized to accommodate additional 759,741 3G customers and 170,737 2G mobile customers. Preparation for 4G network expansion in Addis Ababa, regional capitals and other major cities is also underway. Moreover, international gateway capacity has been upgraded by more than 71% to enhance customer experience and to accommodate growing data usage demand.
During the performance period, our subscribes reached 45.6 million which is 99 % of the target and an increase of 10.9% from the previous year of similar period. Mobile voice subscribers reached 44.03 Million, Data and Internet users 22.74 Million and Fixed Services 1.01 Million, which resulted in 45.4% teledensity.
We have harvested a total revenue of 22.04 Billion ETB which is 104% of the target and 32% increment from the same period of the last budget year.
73 Million USD foreign currency was generated from international business showing an increase of 116% from the same of the last budget year and scored 111% of the target for this period. Mobile voice accounted for 50.4% of the total revenue, Data and Internet 27.3%, revenue from international business 9.8%, Value Added Service 8.5% and the remaining 3% is generated from other sources.
During this period, we have paid 3.89 Billion ETB tax and 2 Billion ETB dividend. Moreover, 4.4 Billion ETB, an equivalent of 148.15 Million USD, was paid for loan of NGN and TEP projects implemented under Vendor-financing modality.
We have employed more than 16 thousand indefinite and more than 19 thousand on definite term employees. We have 181 thousand partners who distribute our products and services, totally we have created job and income opportunities for over 240 thousand citizens.
As part of capacity building endeavor, 8,928 employees were able to benefit from 137 training programs and other interventions including capacity development through delivering engagement in strategy development and company performance review, work environment enhancement and safe & healthy working conditions, various compensation and benefits payments, enhancement of social relations by celebrating employee day throughout the company which has positively impacted employee-management relations.
Corporate Social Responsibility (CSR) has been at the heart of our business during this period. We have contributed 151.5 Million Birr in tackling the society’s most pressing challenges that are aligned with our CSR strategic goals. Our CSR projects focused on making a positive impact in strengthening communities by targeting the fundamental drivers of long-term development such as education, health, environmental protection, greening and beautification.
Our 1,537 sites located in various parts of the country use solar power generated by the company amounting to 20 MW, which contributed to green energy.
In addition to our company’s CSR works, our staff across the nation voluntarily mobilized more than 1.5 Million ETB for various humanitarian activities. Also, their material and in-service support has been enormous.
Among the challenges Ethio telecom faced during the period, Fiber and copper cable vandalism, commercial power interruption, telecom fraud & OTT, security problems and delay in land acquisition for new site deployment were the main ones.
Finally, we would like to extend our most sincere gratitude to our employees, customers, partners and stakeholders for such outstanding performance.

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives