[et_pb_section fb_built=”1″ _builder_version=”3.0.106″][et_pb_row custom_padding=”13px|0px|0|0px” _builder_version=”3.0.106″][et_pb_column type=”4_4″ _builder_version=”3.0.47″ parallax=”off” parallax_method=”on”][et_pb_cta use_background_color=”off” background_layout=”light” _builder_version=”3.0.106″ text_orientation=”left” title=”ውድ ደንበኞቻችን ከአጭበርባሪዎች ይጠንቀቁ!”]

አንዳንድ ደንበኞቻችን የአየር ሰዓት (ካርድ) ሞልተን ሳንጠቀምበት ያልቃል በሚል ባቀረቡት ቅሬታ መሰረት ባደረግነው የማጣራት ስራ የተወሰኑ ህገወጥ ግለሰቦች ከኢትዮ ገበታ (*999#) በማመሳሰል እና የተለያዩ የማጭበርበሪያ መንገዶችን በመጠቀም በደንበኞቻችን ላይ ህገወጥ ተግባራትን እየፈፀሙ መሆኑን ደርሰንበታል፡፡ በመሆኑም ኩባንያችን ይህንን ህገወጥ ተግባር ለመከላከል የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ የሚገኝ ሲሆን በዚህ አጋጣሚ ውድ ደንበኞቻችን ከታች ከተዘረዘሩት እና መሰል የማጭበርበር ተግባራት እንድትጠነቀቁ በታላቅ አክብሮት እናሳስባለን፡፡

1ኛ. በተለያዩ ማህበራዊ ድረ ገፆች ደንበኞች በኢትዮ ገበታ *999# አማካኝነት “ኢንተርኔት በነፃ እንዲሰራላችሁ” እንዲሁም “የኢንተርኔት ጥቅል በነፃ ተጠቀሙ” በሚል ወደ *999*1*2*2*1*1*91xxxxxx*1# ደውሉ በማለት የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየለጠፉ የሚገኝ ሲሆን ይህ ኮማንድ ወይም ትዕዛዝ ግን ትክክለኛ አገልግሎቱን ማግኛ ዘዴ ካለመሆኑ በተጨማሪ የሞሉት የአየር ሰዓት ቀድሞ ፕሮግራም ወደተደረገው የአጭበርባሪው ስልክ ቁጥር የአየር ሰዓትዎ የሚሄድ በመሆኑ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡

2ኛ. ከፕሌይ ስቶር የኢትዮ ቴሌኮም መተግበሪያን (አፕሊኬሽን) በማስመሰል የሚደረግ የማጭበርበር ተግባር ደንበኞች በነፃ ወይም በቅናሽ የተለያዩ አገልግሎቶችን ከኢትዮ ቴሌኮም መተግበሪያ ላይ እንደሚያገኙ በማስመሰል የማጭበርበር ተግባራትን እያከናወኑ ነው፡፡ ነገር ግን እነዚህን ህገወጥ የማጭበርበሪያ መተግበሪያዎች (አፕሊኬሽኖች) ሲጠቀሙ የሞሉት የአየር ሰዓት ቀደም ብሎ ፕሮግራም ወደተደረገው የአጭበርባሪው ስልክ ቁጥር የአየር ሰዓትዎ የሚሄድ በመሆኑ ጥንቃቄ ያድርጉ፡፡

3ኛ. “ነፃ የቪፒኤን መተግበሪያዎችን ከጎግል ፕሌይ ስቶር ስታወርዱ ነፃ የኢንተርኔት አገልግሎት ታገኛላችሁ” በሚል የሚደረግ የማጭበርበር ተግባር ከታች የተቀመጠው ምስል እንደሚያሳየው መተግበሪያውን አውርደው በቀጥታ ሲጫኑ ወይም “በካርዱ ላይ ያለውን ቁጥር ያስገቡ” የሚለውን ትዕዛዝ ተከትለው ካስገቡ ቀድሞ ፕሮግራም ወደተደረገው የአጭበርባሪው ስልክ ቁጥር የአየር ሰዓትዎ የሚሄድ ስለሆነ ጥንቃቄ ያድርጉ፡፡

[/et_pb_cta][et_pb_cta title=”ትክክለኛ አገልግሎቱን የማግኛ ዘዴ” use_background_color=”off” background_layout=”light” _builder_version=”3.0.106″ text_orientation=”left”]ውድ ደንበኞቻችን የድምፅ ፣ የኢንተርኔት እና የአጭር የፅሁፍ መልዕክት አገልግሎቶችን ለራስዎ ለመግዛት ወይም ለወዳጅ ዘመድዎ ስጦታ ለማበርከት ሲፈልጉ *999# ላይ በመደወል ብቻ አገልግሎቱን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡[/et_pb_cta][/et_pb_column][/et_pb_row][/et_pb_section]

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives