ኢትዮ ቴሌኮም የብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የተለያዩ ማሻሻዎችን እና እጅግ ከፍተኛ የዋጋ ቅናሽ ማድረጉን ኩባንያው የካቲት 19 ቀን 2012 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል ደንበኞቹ፣ አጋር ድርጅቶቹ እና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ስነ-ስርዓት አስታውቋል፡፡
ኩባንያው መንግስት የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት ለማፋጠን ካለው ቁርጠኛ አቋም በመነሳት የሦስት ዓመት ስትራቴጂያዊ እቅድ ነድፎ ዘርፈ ብዙ የአገልግሎት ማሻሻያዎችን እያደረገ እንደሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን ጥራቱን የጠበቀ እና ተደራሽ የሆነ የብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት አንዲኖር የህብረተሰቡን የመክፈል አቅም ያገናዘበ እንዲሁም ለቢዝነስ እና ኢንቨስትመንት ምቹ ከባቢን ለመፍጠር የሚያስችል የአገልግሎት ማሻሻያ እና እጅግ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ቅናሽ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
ኩባንያው በብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ላይ ያደረገው የአገልግሎት ማሻሻያ እና የዋጋ ቅናሽ የቴክኖሎጂና የአገልግሎት ልህቀት ማምጣት እና የደንበኛን ሁለንተናዊ ተሞክሮ ማሳደግ በሚል ተቋሙ ያስቀመጣቸውን ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች ትግበራ አንዱ አካል መሆኑን ተገልጿል፡፡
በዚሁ መሠረት ኩባንያው ጥራት ያለውና ተደራሽ የሆነ ባለገመድ ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት እንዲኖር ለማድረግ ነባር የብሮድባንድ መሠረተ ልማት አቅምን የማሳደግ፣ አዳዲስ መሠረተ ልማቶችን የመዘርጋት፣ ቀልጣፋ እና ምቹ የሆነ የአገልግሎት አሰጣጥ የመፍጠር ፣ የባለገመድ ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት የመነሻ ፍጥነት መጠንን በሰኮንድ ወደ አንድ ሜጋ ባይት (1Mbs) የማሳደግ፣ የድርጅት ደንበኞች የሚያገኙትን የብሮድባንድ አገልግሎት አስተማማኝ ለማድረግ የሚያስችሉ የቴክኖሎጂና የቢዝነስ አማራጮችን የማስፋፋት፣ አዳዲስ የቴክኖሎጂ አማራጮችን የመተግበር፣ አዳዲስ አገልግሎቶችን የማቅረብ፣ እንዲሁም በተለያዩ የብሮድባንድ አገልግሎት ታሪፎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ቅናሽ የማድረግ ሥራዎችን ተግባራዊ ማድረጉን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል፡፡
በመሆኑም በተደረገው የብሮድባንድ አገልግሎት ታሪፍ ቅናሽ መሠረት ነባር የባለገመድ ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ደንበኞች ተጨማሪ ክፍያ ሳይጠየቁ ቀደም ሲል ሲያገኙት ከነበረው አገልግሎት በትንሹ በ3 እጥፍ የባንድዊድዝ ፍጥነት እድገት የሚያገኙ ከመሆኑም በተጨማሪ ደንበኞች አገልግሎታቸውን ወደ ከፍተኛ ፍጥነት ማሳደግ እንዲችሉ ቋሚ የማበረታቻ አሰራር ተግባራዊ ( Try & buy) ተደርጓል፡፡
ለግለሰብ ደንበኞች በወርሃዊ የብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ክፍያ ላይ እስከ 69 በመቶ የሚደርስ ቅናሽ የተደረገ ሲሆን ለአብነትም ቀደም ሲል ለአንድ ሜጋ ባይት ፍጥነት ( Mbps) 978 ብር የነበረው ወርሃዊ ክፍያ ወደ 499 ብር ፣ ለሁለት ሜጋ ባይት ፍጥነት 1768 ብር የነበረው ወርሃዊ ክፍያ ወደ 699 ብር፣ ለአራት ሜጋ ባይት ፍጥነት 3191 ብር የነበረው ወርሃዊ ክፍያ ወደ 1099 ብር እንዲቀንስ ከመደረጉም በተጨማሪ ለግለሰብ ደንበኞች ቀደም ሲል 10 ሜጋ ባይት የነበረውን አማራጭ የፍጥነት ገደብ 50 ሜጋ ባይት ከፍ እንዲሆን ተደርጓል፡፡
ለድርጅት ደንበኞች በወርሃዊ የብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ወርሃዊ ክፍያ ላይ እስከ 65 በመቶ የሚደርስ ቅናሽ የተደረገ ሲሆን ለአብነትም ቀደም ሲል ለአንድ ሜጋ ባይት ፍጥነት ( Mbps) 1369 ብር የነበረው ወርሃዊ ክፍያ ወደ 709 ብር ፣ ለሁለት ሜጋ ባይት ፍጥነት 2475 ብር የነበረው ወርሃዊ ክፍያ ወደ 999 ብር፣ ለአራት ሜጋ ባይት ፍጥነት 4468 ብር የነበረው ወርሃዊ ክፍያ ወደ 1575 ብር እንዲቀንስ ተደርጓል፡፡
ለድርጅት ደንበኞች የብሮድባንድ ኢንተርኔት ቪ ፒ ኤን አገልግሎት ወርሃዊ ላይ እስከ 72 በመቶ የሚደርስ ቅናሽ የተደረገ ሲሆን ለአብነትም ቀደም ሲል ለአንድ ሜጋ ባይት ፍጥነት ( Mbps) 1809 ብር የነበረው ወርሃዊ ክፍያ ወደ 499 ብር ፣ ለሁለት ሜጋ ባይት ፍጥነት 2846 ብር የነበረው ወርሃዊ ክፍያ ወደ 899 ብር፣ ለአራት ሜጋ ባይት ፍጥነት 5137 ብር የነበረው ወርሃዊ ክፍያ ወደ 1439 ብር እንዲቀንስ ተደርጓል፡፡
በተጨማሪም ለአዲስ ደንበኞች የብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ማስገቢያ እንደሁም የተቀማጭ ገንዘብ (deposit) ሙሉ በሙሉ የተነሳ ከመሆኑም በተጨማሪ ለነባር ደንበኞ የተቋረጠ አገልግሎት ማስቀጠያ፣ ከክፍያ ነፃ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ በተደረገው የአገልግሎት ማሻሻያ መሰረት ደንበኞች https://onlineservices.ethiotelecom.et ላይ በቀላሉ መመዝገብ የሚችሉ መሆኑ ተገልéDል፡፡
ከዚሁ በተጨማሪ የደንበኞችን የመክፈል አቅም ግምት ውስጥ በማስገባት ኩባንያው የብሮድባንድ አገልገሎት መገልገያ መሣሪያዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንደሚያቀርብ የሚታወቅ ሲሆን አሁን ደግሞ ደንበኞች ክፍያውን በ12 ወራት ውስጥ መክፈል የሚችሉበት አዲስ አሰራር ዘርግቷል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ደንበኞች የባለገመድ ብሮባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ሲያስገቡ መኖሪያ ቤት ወይም ድርጅታቸው ከኢትዮ ቴሌኮም ዋናው መስመር እስከ 500 ሜትር ርቀት ከሆነ ኩባንያው ወጪውን እንደሚሸፍን የሚታወቅ ሲሆን አሁን በተደረገው ማሻሻያ ከተጠቀሰው ርቀት በላይ ያለውን ክፍያ ደንበኞች በ12 ወራት ውስጥ መክፈል የሚችሉበት አሰራር ማመቻቸቱን አስታውቋል፡፡
የብሮድባንድ ኢንትርኔት አገልግሎት የአንድ ሀገር የኢኮኖሚን በማሳደግና የቢዝነስ መስኮችን በማስፋት የቴክኖሎጂና ማህበራዊ ትስስርን በግለሰብ፣ በቢዝነስና በመንግስት ደረጃ በማምጣት ረገድ የማይተካ ሚና እንዳለው የሚታወቅ ሲሆን የብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ስርፀት በ10 በመቶ ማደግ የአንድን ታዳጊ ሀገር አጠቃላይ ሀገራዊ ምርት በ1.38 በመቶ እንደሚያሳደግ የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያመላክቱ ተገልéDል፡፡
ኩባንያው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የዳታ እና ኢንተርኔት አገልግሎት ፍላጎት ለማርካት በአዲስ አበባ ከተማ በቅርቡ ተግባራዊ ካደረገው የ4ጂ ኤል. ቲ. ኢ አገልግሎት ማስፋፊያ አንዲሁም ከፍተኛ የኢንተርኔት አጠቃቀም ባለባቸው የከተማው አካባቢዎች ካደረገው የኤል. ቲ. አድቫንስድ (LTE Advanced) አገልግሎት በተጨማሪ የግለሰብ ደንበኞች በኦፕቲክ ፋይበር አማካኝነት በመኖሪያ ቤታቸው (Fiber to the home) ከፍተኛ ፍጥነት ያለው አገልግሎት በስፋት ለማዳረስ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡
በቀጣይም ኩባንያው የሀገራችንን እድገት ለመደገፍና የህዝባችንን አኗኗር ለማሻሻል የሚስችሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችና አሠራሮችን በመተግበር የመሠረተ ልማትና የአገልግሎት ተደራሽነት በማረጋገጥ ጥራት ያለው የብሮድባንድ አገልግሎት ለማስፋፋት በትጋት የሚሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡
የተሸሻለውን ታሪፍ ዝርዝር ለመመልከት እዚህ ይጫኑ
ኢትዮ ቴሌኮም
የካቲት 19 ቀን 2012 ዓ.ም
Ethio telecom Announces Service Improvement and Major Tariff Reduction on Fixed Broadband Internet Services
Ethio telecom announced service improvement and major tariff reduction on its Fixed Broadband services today February 27, 2020 in the presence of invited customers, partners and stakeholders.
In line with the Ethiopian government’s commitment to ensure economic development by creating favorable business environment with its ‘ease of doing business’ initiative, ethio telecom developed a three year BRIDGE strategy containing various service improvements and tariff reductions.
This fixed broadband service improvement and tariff reduction is derived from this Ethio telecom’s three years’ strategy, which pursues product and technology excellence to meet and excel customer expectation and uplift Ethiopia’s status in broadband penetration thereby harvesting all the benefits arising out of broadband service penetration and use to the best of our country.
The service improvement on fixed broadband services includes; improving the existing broadband infrastructure capacity, deploying new infrastructure, introducing easy and convenient service delivery, expanding reliable and secure broadband service options for enterprise customers, introducing new technology and services, and making massive tariff reduction.
With the the tariff reduction, existing fixed broadband internet service subscribers will be upgraded to a minimum of 3 times higher than the current internet speed. To this effect, the company has developed several offers and solutions which will have significant impact on the broadband service penetration and quality.
Thre will be up to 69% tariff reduction has been made for residential fixed broadband internet service. Hence, a 1 Mbps internet service monthly fee which was previously Birr
978 has been reduced to Birr 499. In addition, a 2 Mbps internet monthly fee which was previously Birr 1768 has been reduced to Birr 699. While, the Birr 3191 monthly fee for 4 Mbps internet service has been reduced to Birr 1099. Furthermore, the previously 10 Mbps maximum internet service limit that residential customers could subscribe to has been increased to 50 Mbps.
Likewise, up to 65% tariff reduction has been made for Enterprise fixed broadband internet customers. Hence, a 1 Mbps internet service monthly fee which was previously Birr 1369 has been reduced to Birr 709. In addition, a 2 Mbps internet monthly fee which was previously Birr 2475 has been reduced to Birr 999. While, the Birr 4468 monthly fee for 4 Mbps internet service has been reduced to Birr 1575.
Also, up to 72% tariff reduction has been made for Enterprise broadband VPN internet customers. Hence, a 1 Mbps internet service monthly fee which was previously Birr 1809 has been reduced to Birr 499. In addition, a 2 Mbps internet monthly fee which was previously Birr 2846 has been reduced to 899 Birr. While, the Birr 5137 monthly fee for 4 Mbps internet service has been reduced to Birr 1439.
In addition, the service subscription fee as well as the deposit requirement for new customers has been removed, while reconnection fee for existing customers has also been made free of charge. As part of the service improvement, customers can now apply for the service online via https://onlineservices.ethiotelecom.et at their convenience.
Moreover, it is known that the company has been offering fixed broadband internet devices with an affordable price. Now, the company has facilitated mechanisms which enable customers to buy devices with twelve months installment payment. Similarly, Ethio telecom has also introduced a twelve months installment based payment for installation related costs for those customers whose premises are located at a distance more than 500 meters from the ethio telecom’s connection point.
Telecom services in general and broadband internet services in particular have paramount impact on economic development, livelihood improvement of a nation and its citizens. Broadband is an indispensable driver of economic development and diversification for technological and social transformation at the individual, business and government levels. Different studies have concluded that a 10% increase in fixed broadband penetration would result in an increase of 1.38% GDP growth in developing countries.
To satisfy the increasing demand for high speed data and internet services, ethio telecom has recently made 4G LTE service network expansion all over Addis Ababa as well launched LTE Advanced mobile service in selected parts of Addis where data usage trend is very high. In line with this, the company has also completed its preparation to expand a high speed broadband internet service via optical fiber to its residential customers (Fiber-to-the-Home).
Finally, to support the country’s effort towards development, the company has expressed its commitment towards the deployment of advanced telecom infrastructure that enables it to offer quality and reachable broadband internet service.
To see the new tariff details click here
Ethio telecom
27 February 2020