ኢትዮ ቴሌኮም ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን /ማርች 8/ በእቴጌ መነን የሴቶች አዳሪ ት/ቤት ከሚማሩ ሴት ተማሪዎች ጋር አከበረ

በርካታ የማህበረሰባችን ክፍሎች በሴቶች ላይ ባለው አመለካከትና በተዛቡ ግንዛቤዎች ምክንያት ሴቶች ዝቅተኛ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተሳትፎ እንዲኖራቸው እንዲሁም ጦርነትና ግጭቶች ሲፈጠሩ በተለየ መልኩ ለፆታዊ ጥቃትና ለተለያዩ ችግሮች ተጋላጭ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ ይህንን ማህበረሰባዊ ሳንካ በዘላቂነት ለመፍታትና የሴቶች ከወንዶች እኩል የልማት ተሳትፎና ተጠቃሚነት እውን እንዲሆን ለማስቻል በየዓመቱ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን/ ማርች 8 ይከበራል፡፡

የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን /ማርች 8/ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ111ኛ ጊዜ “Gender Equality Today for a Sustainable Tomorrow” የፆታ እኩልነትን ዛሬ ማስፈን ለተሻለ እና ቀጣይነት ላለው ነገአችን በሚል መሪ ሀሳብ ይከበራል፡፡

ኩባንያችን የሴቶችን ሁለንተናዊ እኩልነት ለማረጋገጥ እና ሴቶችን ወደ ቴሌኮም ኢንዱስትሪው እንዲቀላቀሉ ለማድረግ በርካታ አበረታች ስራዎችን አከናውኗል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ያለውን የሴቶች ተዋፅኦ ለማሻሻል የተለያዩ ስትራቴጂዎችን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ በተለይም ለሴቶች ምቹ የሆነ የሥራ ከባቢ ከመፍጠር አንጻር በርካታ አሰራሮችን እየተገበረ ሲሆን ለዘላቂ ተግባራዊነቱም በኩባንያው የኀብረት ስምምነትና የሰው ኃይል ፖሊሲዎች ውስጥ እንዲካተቱ ተደርገዋል፡፡

የሴቶችን ተሳትፎ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማሻሻል ኩባንያችን በማህበረሰቡ ሁለንተናዊ የእድገት እንቅስቃሴ ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ በማድረግ ሀገራዊ አለኝታነቱንና ማህበራዊ ኃላፊነቱን በተግባር እየተወጣ የሚገኝ ሲሆን ለአብነትም ሴቶች የመረጃ እና የዲጂታል ኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለመደገፍ 54.4 ሚሊዮን ብር በሚገመት ወጪ 70 ሺህ የሞባይል ቀፎዎችን ከሲም ካርድ ጋር በአገራችን 846 ወረዳዎች ለሚገኙ ሴቶች በስጦታ ማበርከቱ እንዲሁም ሴት መምህራንን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ተደግፈው በተሰማሩበት የሙያ መስክ ውጤታማ እንዲሆኑ ለመደገፍ 50 ላፕቶና 200 ዘመናዊ የስልክ ቀፎ በመላ ሀገሪቱ ለሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ከፍተኛ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሴት መምህራን ሽልማት መስጠቱ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም የ2014 ዓ.ም ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ በእለቱ ብቻ ተግባራዊ የሚደረግ የሴቶች ጥቅል ያዘጋጀ ሲሆን ይህንን ፓኬጅ በማይ ኢትዮቴል ወይም ቴሌብር መተግበሪያ ወይም በ*999# የገዙ ሴት ደንበኞችን በዕጣ በመለየት 50 ዘመናዊ የሞባይል ቀፎዎችን ሽልማት የሚሸልም ይሆናል፡፡

በተጨማሪም የሴቶችን የዲጂታል አገልግሎት ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንዲቻል በአዲስ አበባ እና በክልል ዋና ከተሞች ለሚገኙ ሴት ደንበኞች ከፍተኛ ቅናሽ የተደረገባቸው እና በአንድ ዓመት ወይም በስድስት ወራት ውስጥ በሚጠናቀቅ ክፍያ 17 አይነት ሞባይሎችን በኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከላት አቅርቧል፡፡ እንዲሁም ኢትዮ ቴሌኮም በሚሰጣቸው ዘርፈ ብዙ የቴሌኮም አገልግሎቶች ከፍተኛ ተጠቃሚ እና ለረጅም ጊዜ ከተቋሙ ጋር ቆይታ የነበራቸው ሴት ደንበኞችን በመለየት ልዩ ስጦታ የሚያበረክት ይሆናል፡፡

ኩባንያችን ዛሬ ታህሳስ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን በዓልን በእቴጌ መነን የሴቶች አዳሪ ት/ቤት ከሚማሩ ሴት ተማሪዎች ጋር ሲያከብርም ለ480 ሴት ተማሪዎች ለአንድ ዓመት የሚሆን የንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት ትምህርት ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ 10 ሴት ተማሪዎች ደግሞ የታብሌት ሽልማት አበርክቷል፡፡

ኩባንያችን ኃላፊቱን የሚወጣ አገር በቀል ግዙፍ የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ ተቋም እንደመሆኑ የሴቶችን ተሳትፎ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋጥ በተለይም በዲጂታል ቴክኖሎጂ ታግዘው የዕለት ከዕለት ተግባራቸውን በቀላሉ እንዲተገብሩ በማገዝ እና የቴክኖሎጂ ትሩፋቶች ተቋዳሽ እንዲሆኑ በማድረግ ራሳቸውንም ሆነ ማህበረሰባቸውን እንዲጠቅሙ የበኩሉን አሰተዋጽኦ እንደሚያበረክት በድጋሚ ያረጋግጣል፡፡

                  ኢትዮ ቴሌኮም

            የካቲት 29/2014 ዓ.ም

Ethio telecom celebrates International Women’s Day (March 8) together with Empress Menen Girls’ Boarding Secondary School Students

Down the years, the women have been making low participation in social, economic and political affairs due to the age-old & deep rooted wrong attitudes towards women by a large number of our community members. They have also been victims of the gender based attacks and are highly vulnerable whenever war and conflicts would occur.

International Women’s Day /March 8/ would be celebrated every year to sustainably resolve the mentioned societal perceptions and to realize the women’s equal opportunity and participation in development with men. This year’s International Women’s Day is celebrated on March 8 for 111th times at global level under the theme of “Gender Equality Today for a Sustainable Tomorrow”.

Ethio telecom has made a number of encouraging efforts to ensure women’s multifaceted equal opportunity so as  to enhance and access them to the fruits of telecom services and products. In line with this, the company has been designing and implementing various strategies in order to improve women’s participation within the company. Specially, it has implemented several working systems to create conducive working environment for women and has incorporated this issue in the collective agreement and human resource policy of the company to assure the implementation on sustainable basis accordingly.

In order to improve women’s participation and equal economic opportunity, our company has made remarkable contribution in discharging its corporate social responsibility, especially in empowering women with digital technology so as to handle their own day to day activities easily and to serve their communities at large. As a case in point, the company has made 54.4 million worth 70,000 handsets donation with SIM card for low income women living in 846 woredas/districts of the country during the previous year.

It is recalled that in the near past years, in connection to the International Women’s Day (March 8) Ethio telecom handed over 200 mobile devices and 50 laptops in honor of  best performing women teachers serving in government high schools across the nation.

As part of marking the Women’s international Day, Ethio telecom has launched a one day Women’s Day package and will draw a lottery among women customers who subscribed the Women’s Day package via My Ethiotel, telebirr App or *999# and will award 50 smart phones.

Moreover, ethio telecom has made a one year or six-month long 17 types of mobile devices instalment-based payment for female customers in Addis Ababa and Regional Cities; the devices will be avail in Ethio telecom shops with affordable price and free packages to create the possibility for women to empower them by reducing the digital divide related with cost of ownership.

Furthermore, our company has made women’s sanitary materials donation to 480 Empress Menen Girls’ Boarding Secondary School students that can be used for one year in connection with the March 8 International Women’s Day; and it has also awarded tablets for top 10 outstanding female students who have performed well in the first semester of the academic year.

Until this very moment, the company has been making remarkable contributions in discharging its corporate social responsibility so as to increase women’s participation in social and economic sectors specially in putting women at the center of digital development and will also strive to ensure women’s equal access and use of digital technology in the years to come.

                 Ethio telecom

                 March 8, 2022

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives