ኢትዮ ቴሌኮም በ22 ከተሞች ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት ጀመረ
ኩባንያችን ከፍተኛ የዳታ አጠቃቀም በሚታይባቸው የሀገራችን ከተሞች የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት ለማስፋፋት በያዘው ስትራቴጂያዊ ዕቅድ መሠረት የመጀመሪያውን ዙር የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ማስፋፊያ ፕሮጀክት ሥራውን በ92 ከተሞች አጠናቆ አገልግሎት ማስጀመሩ ይታወሳል፡፡
የመጀመሪያው ዙር የማስፋፊያ ሥራ በተጠናቀቀበት ወቅት እንደተገለፀው በ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት በ2ኛው ዙር የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት ማስፋፊያ ተጠቃሚ የሚሆኑ ከተሞች የዳታ ትራፊክ እድገትና ፍላጎትን መሠረት በማድረግ የተለዩ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ዛሬ ጥቅምት 2 ቀን 2014 ዓ.ም በ22 ከተሞች ማለትም በደደር፣ ዱብቲ፣ ደባርቅ፣ እስቴ ፣ ሸሃዲ፣ ወረታ፣ ጃዊ፣ አዴት፣ ብቸና፣ ደጀን፣ ሞጣ፣ አሰላ፣ ጎባ፣ ሮቤ፣ ሶደሬ፣ ባቱ፣ ሃላባ፣ ዱራሜ፣ ኮንሶ፣ ሳውላ፣ ሺንሺቾ እና ወራቤ የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎትን ማስጀመራችንን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው፡፡ በዚህም መሠረት በአሁኑ ወቅት ጠቅላላ የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት ተጠቃሚ የሀገራችን ከተሞች ብዛት 114 ደርሷል፡፡ በተጨማሪም ከዚህ ቀደም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ከሆኑ ከተሞች መካከል በ10 ሩ (በደሴ፣ ደብረታቦር፣ ጎንደር፣ ባሕርዳር፣ደብረማርቆስ፣ሎጊያ፣ሆሳእና፣ሶዶ፣አርባ፣ምንጭ እና ቡታጅራ) ተጨማሪ የማስፋፊያ ሥራ ተጠናቆ አገልግሎት ላይ ውሏል፡፡
የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት የላቀ ፍጥነትና ባንድዊድዝ እንዲሁም አስተማማኝ የዳታ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ ደንበኞቻችን አገልግሎታቸውን ዲጂታይዝ ለማድረግ፣ ምርታማነታቸውን ለመጨመር እና በአጠቃላይ የቴሌኮም አገልግሎት ላይ ያላቸውን ተሞክሮ በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ ያስችላቸዋል።
በዚህ አጋጣሚም ከላይ በተጠቀሱት የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት በተስፋፋባቸው ከተሞች የምትገኙ ደንበኞች እንኳን ደስ አላችሁ! እያልን በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የኩባንያችን የሽያጭ ማዕከል የ3ጂ ሲም ካርዳችሁን ወደ 4ጂ በነፃ በማሳደግ እንዲሁም በቅናሽ ዋጋ ያቀረብናቸውን 4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎትን መጠቀም የሚያስችሉ የሞባይል ቀፎዎችን በመግዛት እንድትጠቀሙ እየጋበዝን፤ በተጨማሪም እጃችሁ ላይ በሚገኙ 4ጂ በሚቀበሉ ሞባይል፣ ታብሌት ወይም ዶንግል በመጠቀም ወይም በመግዛት እጅግ ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት ማግኘት እንደምትችሉ እንገልጻለን።
በተጨማሪም የቴሌኮም አገልግሎት መጠቀሚያ መሣሪያ (smart phone) እና የይዘት (content) አቅራቢዎች በመረጃ የበለፀገ ማኅበረሰብና ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ እና አሁን የተዘረጋውን ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የሞባይል ኔትወርክ በስፋት ለመጠቀም የሚያስችሉ ዘመናዊ የሞባይል ቀፎዎችና ይዘቶችን ለኅብረተሰቡ በስፋትና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የበኩላችሁን አስተዋጽዖ እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ኩባንያችን በተመሳሳይ መልኩ በቀጣይ በሌሎችም ከተሞች የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ ማስፋፊያዎችን በማከናወን ላይ ሲሆን አጠቃላይ ሥራው እንደተጠናቀቀ የምናሳውቅ ይሆናል።
ጥቅምት 2 ቀን 2014 ዓ.ም
ኢትዮ ቴሌኮም
Ethio Telecom Launches 4G LTE Advanced Service in 22 Towns
It is recalled that we have recently announced the launching of 4G LTE service in 92 towns nationwide and in the capital, Addis Ababa as phase-I 4G LTE service expansion strategic plan for the 2020/21 budget year. Likewise, we also have promised to expand the service in the remaining towns of the country as we have been immensely working on to finalize phase -II network upgrading and expansion to meet the ever-growing data demands of our esteemed customers.
Thus, following our strategic plan to expand 4G LTE service in various cities across the nation where there is high data usage, we are delighted to announce that 4G LTE advanced mobile internet service is launched in 22 towns today on October 12, 2021 specifically in Deder, Dubti, Debark, Este, Shehadi/Genda weha, Woreta, Jawi, Adet, Bichena, Dejen, Mota, Asela, Goba, Robe, Sodere, Batu, Halaba, Durame, Konso, Sawla, Shinshicho and Worabe towns. As a result, the total number of 4G LTE internet service beneficiary towns are reached to 144. In addition to these, taking the high demands of the 4G LTE internet service and uncovered areas into consideration, we have also upgraded the existing 4G LTE service of 10 cities, namely Dessie, Debre Tabor, Gondar, Bahir Dar, Debre Markos, Logiya, Hosaena, Sodo, Arbaminch & Butajira.
It is believed that high band width or high-speed features and reliable data services of 4G LTE will enable and empower our customers to join the digital world, increase productivity and improve their experiences.
In this regard, we would like to call up on players in the ecosystem to use this opportunity in providing useful contents and affordable handsets as well as to join hands in realizing digital inclusion in order to foster the need for digital economy.
We would also like to request our esteemed customers who dwell in those towns where the 4G LTE service is already launched and available to visit our nearby telecom shops and upgrade your 3G SIM cards to 4G for free of charge and buy from the offered highly discounted mobile handsets or using your own 4G supporting mobile device, tablets and modems as to enjoy the benefits of 4G LTE internet service.
Similarly, we are also undertaking massive 4G LTE expansion projects in various parts of the country which we will publicize upon project completion.
October 12, 2021
Ethio telecom