የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ደ/ምዕ/አ/አ/ዞን 02/2013 ዓ.ም.
ኢትዮ ቴሌኮም የተለያዩ ብረት እና ብረት ነክ ያልሆኑ/Metallic and Non-Metallic Scrap ባሉበት ሁኔታ ለሕጋዊ ድርጅቶ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ህዳር 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ጠዋት 4፡30 ሰዓት ድረስ ይሆናል፡፡
1/ ስለ አሻሻጡ ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. እስከ ህዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም. ጠዋት 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ከደ/ምዕ/አ/አ/ዞን ኦልድ ኤርፖርት ካርል አደባባይ ቢሮ ቁጥር 209 የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
2/ የተለያዩ ከአገልግሎት የተመለሱ እና የተነቀሉ ብረታ ብረቶች/ Different kinds of dismantled metallic materials ፤ካቢኔቶች ፤ራኮች፣የብረት መጠለያ ንቃይ፤የብረት ሳጥን፤ አሮጌ የእሳት ማጥፊያ ስሊንደሮች ፤በርሜሎች፤ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፤ አልሙኒየም መሰላሎች፤ባትረዎች፤ የቶነር ካርትሪጆች፤ተነቅለው የተሰበሰቡ የእንጨት ምሰሶዎች ፤ምንጣፎች፣ የመብራት ማቀፊያዎች፤ የመጋረጃ ሻተር ማቀፊያዎች፤የሽንት ቤት ባለመቀመጫ እና ወለል ላይ ተለጣፊ ሲንክ፤የእጅ መታጠቢያ ሲንክ ፤ንቃይ የቤት ክዳን ቆርቆሮዎች፤ የእንጨት መዝጊያዎች፤መስኮቶች ፤መቃኖች፤የተለያዩ ቺፕውዶች ፤የጣውላ ንቃዮች ፤ የአጣና ቁርጥራጭ ንቃዮች ፤ግንዲላ እንጨቶች እና ለማገዶ ሊሆኑ የሚችሉ የተለያዩ የጣውላ ንቃዮች እና የሳጥን ንቃዮችን ለማየት ለሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የገዙበትን ደረሰኝና መታወቂያ በመያዝ አየርጤና ጅማ በር አካባቢ በሚገኘው የኢትዮ ቴሌኮም እቃ ግ/ቤት በመገኘት ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. እስከ ህዳር 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ዘወትር በስራ ሰዓት መመልከት ይቻላል፡፡
3/ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የተለያዩ ብረት እና ብረት ነክ ያልሆኑ/Metallic and Non-Metallic Scrap ለመግዛት የሚያቀርቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት ከመቶ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታ ማስከበሪያው ከታወቀ ባንክ ተረጋግጦ በሚቀርብ ሲፒኦ (CPO) መሆን ይኖርበታል፡፡
4/ ተጫራቾች የተለያዩ ብረት እና ብረት ነክ ያልሆኑ/Metallic and Non-Metallic Scrap የሚገዙበትን ዋጋ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ/ፎርም መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን የተለያዩ ብረት እና ብረት ነክ ያልሆኑ/Metallic and Non-Metallic Scrap የሚያሳይ የዋጋ ማስገቢያ ቅጽ/ፎርም፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ኮፒ፣የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ (CPO) ፣ የተጫራቾች አድራሻ መግለጫን በማካተት በታሸገ ኤንቨሎ ሙሉ አድራሻውንና የጨረታውን ቁጥር በመጥቀሰ በኢትዮ ቴሌኮም ደ/ምዕ/አ/አ/ዞን ኦልድ ኤርፖርት ካርል አደባባይ ቢሮ ቁጥር 209 ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. እስከ ህዳር 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት የሚጠበቅ ሲሆን ከዚህ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርብ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም::
5/ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ምዕ/አ/አ/ዞን ኦልድ ኤርፖርት ካርል አደባባይ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 209 ህዳር 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡