ተማሪዎቻችንን ወደ ትምህርት ገበታቸው በጋራ እንመልስ!

ኢትዮ ቴሌኮም ዘርፈ ብዙ የቴሌኮም መሰረተ ልማት በመገንባት እና የሀገሪቱን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ራዕይ ለማረጋገጥ እያደረገ ከሚገኘው ጥረት ጎን ለጎን በመላ ሃገሪቱ በትምህርት፣ በጤና፣ በሰብአዊ እርዳታ፣ በአካባቢ ጥበቃ እንዲሁም በአረንጓዴ ልማት በመሳተፍ ማህበራዊ ሀላፊነቱን በብቃት እየተወጣ የሚገኝ ሕዝባዊ ተቋም መሆኑ ይታወቃል፡፡

የትምህርቱ ዘርፍ ለሀገራችን ሁለገብ የልማት እንቅስቃሴ ያለውን ፈርጀ-ብዙ ሚና ከግንዛቤ በማስገባት በእውቀት የታነጹ እና ብቁ ተማሪዎችን ለማፍራት በሃገራችን ከዘመናዊ ትምህርት ጅማሮ አንስቶ በልዩ ትኩረት የበኩሉን ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በተለይም በቴክኖሎጂ የተደገፈና ጥራት ያለው ትምህርት በቀጥታ ስርጭት (በፕላዝማ ቴሌቪዥን) መስጠት ከታሰበበት ጊዜ ጀምሮ ትምህርት ተቋማትን ከፍተኛ አቅም ባላቸው የገመድ እና የሳተላይት መገናኛ አማራጮችን የማገናኘት (ስኩል ኔት) እና የኢንተርኔት አገልግሎቶችን በነጻ እንዲሁም እስከ 86 በመቶ በሚደርስ ቅናሽ በማቅረብ በትምህርቱ ዘርፍ ከ4.8 ቢሊዮን ብር በላይ በሚሆን ወጪ ልዩ የሆነ ድጋፍ አድርጓል፡፡ በተጓዳኝ የትምህርት ስርጭቱ የመቆራረጥ ችግር እንዳይገጥመው ተገቢውን የጥገና እና የክትትል ስራዎች በነጻ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

ኩባንያችን በተጨማሪም ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው በተለያየ ደረጃ ለሚገኙ ተማሪዎች በትምህርት፣ በምገባ መርሃ-ግብር እና በገንዘብ ድጋፍ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን በያዝነው የትምህርት ዓመት መጀመሪያም “ተማሪዎችን በትምህርት ግብአት ማስታጠቅ ትውልድን መገንባት ነው” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ በ665 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ ተማሪዎች 16.5 ሚሊየን ብር የሚገመት 50,000 ደርዘን የመማሪያ ደብተሮችን የለገሰበት መርሀ ግብር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። ከዚሁ ጎን ለጎን 250 ለሚሆኑ ትጉህ ሴት መምህራን የሞባይል ቀፎ እና የላፕቶፕ ድጋፍ ማድረጉም ለትምህርቱ ዘርፍ ያለውን ቁርጠኛ አቋም የሚያሳይ ነው፡፡

ኩባንያችን በቅርቡ በሃገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ተከስቶ በነበረው ጦርነት ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ውድመት ያጋጠመው ቢሆንም በተመሳሳይ ችግር ጉዳት የደረሰባቸውን የትምህርት ተቋማት መልሶ ለማቋቋም እና ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ በትምህርት ሚኒስቴር የሚደገረውን የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር ለመደገፍ በአጭር የጽሁፍ መልእክት ወደ 9222 ወይም በቴሌብር በ9222 የመለያ ቁጥር፣ እንዲሁም በውጪ ሃገራት የሚኖሩ ድጋፍ ሰጪዎች ደግሞ በቴሌብር ዓለም አቀፍ ሃዋላ ወደ 993161616 አቅማቸው የፈቀደውን የገንዘብ መጠን በመላክ ድጋፍ ማድረግ የሚችሉበትን አገልግሎት ማቅረቡን ይገልጻል፡፡

በተጨማሪም በቅርቡ ከፍተኛ ቅናሽ የተደረገበት እና ለተማሪዎች ብቻ የተዘጋጀ የተማሪዎች ጥቅል የሚያቀርብ መሆኑን እያስታወቀ እንደ አንድ ሀገራዊ ተቋም የትምህርት ዘርፉን በመደገፍ እና የተሻለ ትውልድ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ እንዲሁም በማህበረሰቡ ሁለንተናዊ የእድገት እንቅስቃሴ ላይ በቀጥታ በመሳተፍ እና ሀገራዊ አለኝታነቱንና ማህበራዊ ኃላፊነቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያረጋግጣል፡፡

 

 ኢትዮ ቴሌኮም

 የካቲት 3 ቀን 2014 ዓ.ም

Let Us Stand Together to Bring Our Students Back to School!

 Ethio telecom, apart from its prior engagement in building a multifaceted telecom infrastructure and realizing the country’s digital transformation vision, is taking part in a major considerable social responsibility program such as in education, health, humanitarian aid, environmental protection and green legacy initiatives countrywide.

Considering the multifaceted role of the education sector in the overall growth of the nation, the company has been giving a special emphasis to the development of knowledgeable and competent students since the advent of modern education in the history of this country. So far, the company has invested more than 4.8 billion birr in the education sector, especially since the introduction of technology supported online education (plasma TV) by connecting educational institutions with high speed fixed broadband internet and satellite communication options (School net) and provided free and up to 86 percent service fee discount. Furthermore, the company has been providing free maintenance service to assure reliable connectivity.

The company has also been providing support to students at different levels with special needs through education, school feeding programs.  In the year 2021 G.C alone, the company discharges its corporate social responsibility by donating 50,000 dozen of exercise books for the primary school students enrolled in 665 schools countrywide which worth over 16.5 M ETB under the motto “Equipping students is building generation”. Similarly, the company has donated mobile phones and laptops for 250 hardworking female teachers which is one of the manifestations of its commitment and dedication to the betterment of education sector.  

It is noted that our company has encountered with severe telecom infrastructure damage due to the recent security related crisis in various parts of the country; and it has lost a huge amount of revenue which it has intended to collect.  In the midst of this challenges, the company is providing a number of donations to support the crisis victim community.

Among these, Ethio telecom has made a significant contribution today on February 10, 2022,  to the Ministry of Education in its major effort to restore the destroyed and looted educational institutions in the crisis ravaged areas so as to get students back to school and resuming learning.

To this effect,Ethio telecom has allocated a short code SMS and telebirr channels where local customers can contribute any amount by sending SMS to 9222, via telebirr App or dialing on *127# and entering 9222 as a merchant number and oversea donors can donate via 993161616 international remittance telebirr payment number.

In not the distant future, the company will also disclose the launch of a discounted student-only package. As a nationwide responsible telecom operator, it is committed to support the education sector and building a better generation by directly participating in the overall development of the community, demonstrating its national commitment and corporate social responsibility; would like to assure it will continue to strengthen its support in the education sector in the future.

 Ethio telecom

 10 February 2022

                     

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives